አውደ Tibeb dan repost
በተስፋ ይሆናል
✍ሄኖክ ክበበው
በህልም ዓለም ቅዠት በቀን ድንዛዜ፤
ደስታን እየሻቱ በመኖር አባዜ..
መዳኅ መራመድ መሯሯጥ ሁልጊዜ፤
ለነገ ብርሃን ነው ለህይወት አዋዜ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
መፈራረቃቸው ብርድና ሀሩሩ፣
ማኀለቅት አልባው ጉዞ መራዘም ማጠሩ፣
አዕምሯችን ከንፎ ያለ ልክ መብረሩ፣
ሁሉንም ለማግኘት መቸኮል መጣሩ፣
የዚ ሁሉ ክሥተት የሁነት ምሥጢሩ፣
መጓዝ ሆነና ነው የህይወት ቀመሩ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
ርቀት ይመስላል መድረሻ መንገዱ፤
ያደክምም ይሆናል ዓልመው ሲነጉዱ፤
ግና ....
ህልምን አሻግሮ አይቶ፣
በተስፋ ተመልቶ፣
ተግባርን አጉልቶ፣
በአምላክ ተመክቶ፤
መኳተን መፈለግ መመኘት መቋመጥ፣
ጥቂቱን ህልም አሳድጎ ሌተ ቀን መሯሯጥ፣
በሰዎች ህይወት ያመጣል ትልቅ ለውጥ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
የህይወት ጥጓ ሞት የሞት ጥግ ዘላለም፤
በዘላለም ኑሮ ...
በዕረፍት በፍስሃ አለያም በሀዘን ማዝገም፤
ቢሆንም እንኳ የመጨረሻው መጨረሻ፤
ማለሙ አይከፋም ቀድሞ ከመነሻ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
መልካም ነገር ሁሉ...
በአዕምሮ ታስቦ በልብ ይሰነቃል፤
በተስፋ ይሆናል በእምነት ይፀናል፤
በፈጣሪ ፈቃድ ሁሉም ይከወናል።
✍ሄኖክ ክበበው መጋቢት 8 2013
https://telegram.me/felege_tibeb
ፈለገ ጥበብ Felege tibeb በሄኖክ ክበበው
✍ሄኖክ ክበበው
በህልም ዓለም ቅዠት በቀን ድንዛዜ፤
ደስታን እየሻቱ በመኖር አባዜ..
መዳኅ መራመድ መሯሯጥ ሁልጊዜ፤
ለነገ ብርሃን ነው ለህይወት አዋዜ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
መፈራረቃቸው ብርድና ሀሩሩ፣
ማኀለቅት አልባው ጉዞ መራዘም ማጠሩ፣
አዕምሯችን ከንፎ ያለ ልክ መብረሩ፣
ሁሉንም ለማግኘት መቸኮል መጣሩ፣
የዚ ሁሉ ክሥተት የሁነት ምሥጢሩ፣
መጓዝ ሆነና ነው የህይወት ቀመሩ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
ርቀት ይመስላል መድረሻ መንገዱ፤
ያደክምም ይሆናል ዓልመው ሲነጉዱ፤
ግና ....
ህልምን አሻግሮ አይቶ፣
በተስፋ ተመልቶ፣
ተግባርን አጉልቶ፣
በአምላክ ተመክቶ፤
መኳተን መፈለግ መመኘት መቋመጥ፣
ጥቂቱን ህልም አሳድጎ ሌተ ቀን መሯሯጥ፣
በሰዎች ህይወት ያመጣል ትልቅ ለውጥ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
የህይወት ጥጓ ሞት የሞት ጥግ ዘላለም፤
በዘላለም ኑሮ ...
በዕረፍት በፍስሃ አለያም በሀዘን ማዝገም፤
ቢሆንም እንኳ የመጨረሻው መጨረሻ፤
ማለሙ አይከፋም ቀድሞ ከመነሻ።
❤በተስፋ ይሆናል❤
መልካም ነገር ሁሉ...
በአዕምሮ ታስቦ በልብ ይሰነቃል፤
በተስፋ ይሆናል በእምነት ይፀናል፤
በፈጣሪ ፈቃድ ሁሉም ይከወናል።
✍ሄኖክ ክበበው መጋቢት 8 2013
https://telegram.me/felege_tibeb
ፈለገ ጥበብ Felege tibeb በሄኖክ ክበበው