ልብ የሚሰብር ዜና
ታላቁ ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ አረፈ።
ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ በዓለማየሁ እሸቴ ቤት ሆኖ አሁን ለዘ-ሐበሻ እንደገለጸው ዓለማየሁ ቀኑን ሙሉ ከጓደኞቹ ጋር ሥለሥራ ጉዳይ ሲያወራ የዋለ ሲሆን ቤቱ በሰላም ከገባ በኋላ ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ የህመም ስሜት ተሰማኝ በማለት ከቤት ራሱ እየተራመደ ወጥቶ በታክሲ ወደ አይሲ ኤምሲ (iCMC General Hospital) ሆስፒታል ሄደ። በዚያ በህክምና እየተረዳ እያለ ነው ሕይወቱ ያለፈው። ዓለማየሁ ለኢትዮጵያ ብዙ ያደረገ ባለሙያ ነው። ሃገር ወዳድም ነው። ይህ ታላቅ አርቲስት በክብር እንዲሸኝ እና እንዲቀበር ዘ-ሐበሻ ጥሪውን ያቀርባል። ዓለማየሁ ከዚህ ቀደም የልብ ህመም ህክምናውን በተለያዩ ሃገራትና በሃገር ውስጥ ሲከታተል እንደነበር ይታወቃል።
ማዲንጎ አፈወርቅ፣ ኃይልዬ ታደሰ፣ ግርማ ተፈራ፣ መሳፍንት አወቀ፣ መሐመድ ኮይስ እና ሌሎችም የሙያ ባልደረቦቹ የዓለማየሁ ሕልፈት እንደተሰማ በቤቱ በመገኘት ቤተሰብ እያጽናኑ ይገኛሉ።
ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን። ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመጣለን።