G.C construction solutions p.l.c 🏘🔲


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ
🏢ዲዛይን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
👷‍♂እናማክራለን
We specialize in building construction, civil engineering 🏛️, waterproofing 💧, delivering quality & affordable solution.

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


የመፅሀፋ ርእስ -ህይወቴ እና በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መሰረተ ልማት አውታሮች ዕድገት ትውስታዬ
ደራሲ- ዘርኦም ገ|ክርስቶስ(አርኪቴክት.)
የገፅ ብዛት - 247
የመፅሀፋ መገኛ - ዶ|ር ውብሸት ዥቅአለ ቢሮ (ቴሌ ጋራዥ ፊት ለፊት ፣አለሙ ወ|ፃዲቅ ህንፃ፣3ኛ ፍቆ ቢሮ ቁ 17)
የደራሲው ስልክ-0911113696


🌟ፎርምወርክ/Formwork

⭐️በምን ያህል ቀን ማፍረስ ይቻላል?

✅ለቌሚ ፎርምወርክ 16ሰዓት
✅ለወለል እና ደረጃ /ሶሌታ/ ፎርምወረክ 21 ቀን
✅ተጨማሪ ለቢም/beam/ እና ወለል/slab/ ድጋፍ የሚገባ
14ቀን

🎁 የፎርም ወርክ አለካክን በተመለከተ ባትኮዳ/Batcoda/ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች ይጠቅሳል።

💱. ከ 0.25ካ.ሜ በታች የሆነ ክፍት/opening/ ፎርሞርክ ክፍያ ላይ ሊቀነስ አይገባም።
💱በተለየ ሁኔታ ካልተጠቀሰ በስተቀር በካ. ሜ ሊለካ ይገባል።
🤑የወለል ጠርዝ፣ የደረጃ መወጣጫ እና የጎን ፎርምወረክ ጥልቀቱን በመጥቀስ በሜትር ሊለኩ ይገባል።


@gghabesha


🔨📊 የግንባታ ግብአት ዋጋ ጥናት – የየካቲት 2017 🏠📈

Check out the latest construction material prices as of February 1, 2025! All prices are up-to-date and accurately reflect current market trends in Ethiopia.

🔗 Click here for details
https://constructionproxy.com/construction-materials-price-as-of-february-01-2025/


❤️ ለጠቅላላ ግንዛቤ !!
የግንባታ ዲዛይን ከተሰራ በኋላ የሚመለከተው የመንግሥት ቢሮ ዲዛይኖቹን (All drawings, details and BOQ) አይቶ እስከማረጋገጥ (መርምሮ አስተያየት ከመስጠት እስከማጽቀድ) የሚወስድበት ጊዜ በመመሪያ የተደነገገ ሲሆን ከፍተኛው ውስብስብነት እና ግዝፈት ላላቸው ሕንጻዎች (ምድብ ሐ) የሚወስደው ጊዜ 21 ቀን ነው።

✅አንድ የግንባታ ፍቃድ ከ21 ቀን በላይ የማጽደቂያ ጊዜ ሊራዘምበት አይገባም።

✅የህንጻ መመሪያና ስታንዳርድ  ቁጥር 3/2015  (4.8)

✉️https://t.me/gccon1
@gghabesha


❤️በአሜሪካ ኬንቲኪ Grace Farms ውስጥ በወንዝ አምሳያ የተገነባው  "River building" ጥልፍልፍ ሕንፃ በምህንድስና ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ያለው እንደሆነ የተመሠከረለት ነው‼️

ለተጨማሪ መረጃ
subscribe ❤️ https://t.me/gccon1

@gghabesha


💫የውሃ ማፍሰሻ (Drainage) ንድፍ የሲቪል ምህንድስና፣ የከተማ ፕላን እና የመሬት ገጽታ አርክቴክቸር ወሳኝ ገጽታ ነው።

የውኃ ፍሰትን በተለይም የዝናብ ውሃን፣የጎርፍ መጥለቅለቅን፣የአፈር መሸርሸርን እና የውሃ መቆራረጥን ለመከላከል ስርዓቶችን ማቀድ እና መተግበርን ያካትታል።

የፍሳሽ ማስወገጃ ንድፍ አጠቃላይ ሂደቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል

❤️1. የፕሮጀክት ምዘና እና መረጃ ማሰባሰብ

    - የሳይት ዳሰሳ፡ የመሬት አቀማመጥን፣ ተዳፋትን እና የተፈጥሮ ፍሳሽን ሁኔታ ለመረዳት የመሬት አቀማመጥ ዳሰሳ ያካሂዱ።
    - የሃይድሮሎጂካል መረጃ፡ የዝናብ መረጃን ይሰብስቡ፣ የዝናብ መጠን፣ የቆይታ ጊዜ እና የአውሎ ነፋሶች ብዛት (ለምሳሌ ታሪካዊ የአየር ሁኔታ መረጃን በመጠቀም)።
    - የአፈር ባህሪያት፡ የአፈር አይነት፣ የመተላለፊያ አቅም እና የሰርጎ መግባት መጠንን ይተንትኑ።
    - የመሬት አጠቃቀም፡ የውሃ ፍሳሽን ለመገመት ነባሩን እና የታቀደውን የመሬት አጠቃቀም (ለምሳሌ የመኖሪያ፣ የንግድ፣ የግብርና) ይለዩ።
    - የቁጥጥር መስፈርቶች *: የአካባቢ ደንቦችን, ኮዶችን እና የአካባቢ መመሪያዎችን ይከልሱ።

⭐️2. የንድፍ መስፈርቶችን ይወስኑ

- Design Storm፡ በፕሮጀክቱ አስፈላጊነት እና አደጋ ላይ በመመስረት ተገቢውን የአውሎ ነፋስ መመለሻ ጊዜ (ለምሳሌ፡ 10-አመት፣ 25-አመት፣ ወይም 100-አመት አውሎ ነፋስ) ይምረጡ።
    - Runoff Coefficient *: በመሬት አጠቃቀም፣ በአፈር አይነት እና በገፀ ምድር ባህሪያት ላይ በመመስረት የፍሳሹን መጠን (C) አስላ።
    - ከፍተኛ ፍሰት መጠን *: ከፍተኛ ፍሰት መጠኖችን ለመገመት እንደ ምክንያታዊ ዘዴ ወይም ሃይድሮሎጂካል ሞዴሎችን ይጠቀሙ።
    - የፍጥነት ገደቦች፡ የአፈር መሸርሸርን ወይም ደለልን ለመከላከል የፍሰት ፍጥነቶች ተቀባይነት ባለው ገደብ ውስጥ መሆናቸውን ያረጋግጡ።

🤖3. ሀይድሮሎጂካል ትንተና
   
- Run off Estimation፡ እንደ ምክንያታዊ ዘዴ፣ የኤስ.ሲ.ኤስ ከርቭ ቁጥር ዘዴ ወይም የሃይድሮሎጂ ሞዴሊንግ ሶፍትዌር (ለምሳሌ HEC-HMS፣ SWMM) ያሉ ዘዴዎችን ተጠቀም።
    - Time of Concentration*: ውሃ ከተፋሰሱ ከሩቅ ቦታ ወደ መውጫው ለመጓዝ የሚፈጀውን ጊዜ ያሰሉ ።
    - የፍሰት መንገዶች፡ ጅረቶችን፣ ስዋሎችን እና ያሉትን የፍሳሽ ማስወገጃ ዘዴዎችን ጨምሮ የተፈጥሮ እና አርቲፊሻል ፍሰት መንገዶችን ይለዩ።

🌟4. የሃይድሮሊክ ዲዛይን
  
- የቧንቧ መጠን *: ቧንቧዎችን ፣ ቧንቧዎችን እና ሰርጦችን ለመለካት የማኒንግ እኩልታ ወይም ሌላ የሃይድሮሊክ ቀመሮችን ይጠቀሙ።
    - ግራዲየንት እና ተዳፋት: ከመጠን በላይ ፍጥነቶችን በማስወገድ ትክክለኛ ተዳፋትን ለስበት ኃይል ፍሰት ያረጋግጡ።
    - መግቢያዎች እና መውጫዎች *: ውሃን በብቃት ለመሰብሰብ እና ለማውጣት የመግቢያ እና መውጫ መዋቅሮችን ይንደፉ።
    - የማጠራቀሚያ ተቋማት *፡ ከፍተኛ ፍሰቶችን ለመቆጣጠር እና የታችኛው ተፋሰስ ተፅእኖዎችን ለመቀነስ አስፈላጊ ከሆነ ማቆያ ወይም ማቆያ ገንዳዎችን ዲዛይን ያድርጉ።

🍟5. የስርዓት አቀማመጥ

    - የአውታረ መረብ ንድፍ *: የቧንቧዎችን, የሰርጦችን እና ሌሎች የፍሳሽ ክፍሎችን አቀማመጥ ያቅዱ.
    - ከነባር ስርዓቶች ጋር ውህደት *: አሁን ካለው የፍሳሽ መሠረተ ልማት ጋር ተኳሃኝነትን ያረጋግጡ።
    - አካባቢያዊ ጉዳዮች፡ ዘላቂነትን ለማጎልበት አረንጓዴ መሠረተ ልማትን (ለምሳሌ የዝናብ ጓሮዎች፣ ተላላፊ መንገዶችን) ማካተት።

🔶6. መዋቅራዊ ንድፍ

    - የቁሳቁሶች ምርጫ *: ለቧንቧዎች, ለቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች እና ለሌሎች መዋቅሮች (ለምሳሌ, ኮንክሪት, HDPE, ቆርቆሮ ብረት) ተስማሚ ቁሳቁሶችን ይምረጡ.
    - የጭነት ትንተና : የአፈርን ግፊት እና የትራፊክ ጭነቶችን ጨምሮ መዋቅሮች የሚጠበቁ ሸክሞችን መቋቋም እንደሚችሉ ያረጋግጡ.
    - የአፈር መሸርሸርን መቆጣጠር *: እንደ መሸርሸር, ጋቢን ወይም እፅዋትን የመሳሰሉ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የንድፍ እርምጃዎች.

⭐️7. ሞዴሊንግ እና ማስመሰል

    - የሶፍትዌር መሳሪያዎች *: በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ የስርዓት አፈፃፀምን ለማስመሰል የውሃ ማፍሰሻ ሞዴሊንግ ሶፍትዌርን ይጠቀሙ (ለምሳሌ ፣ SWMM ፣ Civil 3D ፣ AutoCAD)።
    - የትዕይንት ትንተና * ስርዓቱን በተለያዩ አውሎ ነፋሶች እና ውድቀት ሁኔታዎች ውስጥ ይሞክሩት።

🔷8. የግንባታ ሰነድ

    - ድሮዊንግ *: እቅዶችን, መገለጫዎችን እና መስቀሎችን ጨምሮ ዝርዝር የግንባታ ንድፎችን ያዘጋጁ.
    - መግለጫዎች *: የቁሳቁስ እና የግንባታ ዝርዝሮችን ያቅርቡ.
    - የወጪ ግምት *: የውሃ መውረጃ ስርዓት ወጪ ግምት ያዘጋጁ.

✉️9. አተገባበር እና ጥገና

    - የግንባታ ቁጥጥር *: የፍሳሽ ማስወገጃ ክፍሎችን በትክክል መጫኑን ያረጋግጡ.
    - ፍተሻ እና ሙከራ *: የስርዓት አፈፃፀምን ለማረጋገጥ ምርመራዎችን እና ሙከራዎችን ያካሂዱ።
    - የጥገና እቅድ *: የረጅም ጊዜ ተግባራትን ለማረጋገጥ የጥገና እቅድ ማዘጋጀት, ማጽዳትን, ጥገናዎችን እና ማሻሻያዎችን ያካትታል.

Ⓜ️10. ክትትልና ግምገማ

    - የአፈጻጸም ክትትል *: ስርዓቱን በማዕበል ጊዜ እና በኋላ ይቆጣጠሩ ውጤታማነቱን ለመገምገም.
    - ተስማሚ አስተዳደር *: በታዩ አፈጻጸም እና በተለዋዋጭ ሁኔታዎች ላይ በመመስረት ማስተካከያዎችን ያድርጉ።

🍏ቁልፍ ጉዳዮች

- ዘላቂነት *: ዘላቂ የፍሳሽ ማስወገጃ ዘዴዎችን (SuDS) ወይም ዝቅተኛ-ተፅእኖ ልማት (LID) ልምዶችን ማካተት።
- የአየር ንብረት ለውጥ *: በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በዝናብ መጠን ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦችን ግምት ውስጥ ያስገቡ።
- የህዝብ ደህንነት፡ ስርዓቱ እንደ ጎርፍ ወይም መዋቅራዊ ውድቀት ባሉ የህዝብ ደህንነት ላይ አደጋዎችን እንደማይፈጥር ያረጋግጡ።

🪙💎*️⃣እነዚህን ቅደም ተከተሎች በመከተል, መሐንዲሶች እና ዲዛይነሮች ሁለቱንም ተግባራዊ እና አካባቢያዊ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ውጤታማ እና ተከላካይ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓቶችን መፍጠር ይችላሉ።
Subscribe my channel

✉️https://t.me/gccon1

✉️@gghabesha


ኮንትራክተር ለመሆን ምን ያስፈልጋል?

👉What we need to have to be
contractor?
🇪🇹

1.የንግድ ስያሜ በ ዌብሳቱ 👇👇 በመግባት መመዝገብ እና የ ድርጅቱን መዋቅር መወሰን
https://www.business.gov.et

ሀ. Sole proprietorship/ አንድ ግለሰብ ብቻ ባለቤት የሆነበት

ለ. PLC ( private limited company)/ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

ሐ.SC(share company)/ አክሲዮን ማህበር


2. ውል እና ማስረጃ ( document authentication) በመሄድ መመስረቻ እና መተዳደሪያ ማፀደቅ

3.ክፍለከተማ ንግድ ቢሮ በመሄድ በባንክ ዝግ አካውንት በማሳየት ካፒታል ማፀደቅ

4. ሰነዶች ማረጋገጫ በመሄድ በ ቤት ኪራይ ውል ማዘጋጀት

5. በአቅራቢያ ባለው ገቢዎች TIN number ማውጣት

6.የንግድ ምዝገባ እና ንግድ ፈቃድ
https://www.business.gov.et በዚ ዌብ ሳይት በመግባት ማውጣት

7. ደረሰኝ ማሳተም

8. ኮንስራክሽን ቢሮ በመሄድ ደረጃ ማውጣት

➡️ባላችሁ ብቃት (ልምድ ፣የሰው ሀይል፣ማሽን) የደረጃ እርከን ይወጣላችኋል!


2017 2nd QUARTER CONSTRUCTION WORKS (ONLY DIRECT COST).pdf
20.0Mb
☑️የ2017 2ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ


⭐️የ "Site Diary" ጥቅምና ይዘት
{The importance and Format of Site Diary}


በግንባታ ሂደት ውስጥ የምናገኛቸው የተለያየ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰነዶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፦ የውል ሰነድ (contract document)፣ የሥራ ፍቃድ (Work Permit/order)፣ የግንባታ ፍቃድ (Building Permit)፣ የሥራ ምዘና መዝገብ (Checklists)፣ የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary)፣ ንድፎች (Drawings) ... የመሳሰሉት ይገኙበታል። በሀገራችን የውል ፈጻሚዎች (አሠሪ፣ ተቋራጭ እና አማካሪ) ግጭት ውስጥ ለመግባታቸው አንዱና ዋነኛው ምክንያት እነዚህ ሰነዶች በግንባታ ሥራ አለመሟላታቸው መሆኑን የተጠኑ ጥናቶችም ጠቁመዋል።

😀ከእነዚህ ውስጥ  አንዱ የሆነውን የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary) እንመለከታለን።

ብዙ ጊዜ ስለዚህ ሰነድ ያለን ትኩረት ለዘብ ያለ ሆኖ የሚስተዋል ቢሆንም ብዙ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና አሠሪዎች ከስረውበታል።  


ክፍል አንድ  ዋና ዋና ጥቅሙ፦

1ኛ). የዕለት ተግባራትን መመዝገቢያ፡ ይህ የማስታወሻ ጥራዝ ወይም ሰነድ በየቀኑ በግንባታ ቦታው ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን እንመዘግብበታለን። የተሰሩ ሥራዎችን፣ ግንባታው ያለበትን ደረጃ፣ በዕለቱ ያለውን የአየር ሁኔታ፣ ለግንባታ ሥራው የተሳተፉ ባለሙያዎችንና የጉልበት ሰራተኞችን ብዛት፣ የገጠሙ ችግሮችን፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችን፣ በባለድርሻ አካላት የታዘዙ ልዩ ትእዛዞች (ካሉ) እነዚህ መረጃዎች የምንመዘግብበት የሁሉም የግንባታ ስራዎች አጠቃላይ ዕለታዊ መዝገብ ሆኖ ያገለግላል። ይህ ሰነድ የፕሮጀክቱን እድገት ለመከታተል ወሳኝ ሲሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ ግልፅነትን ያረጋግጣል፣ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ስለቦታው ሁኔታ እንዲያውቁ ያግዛል።

2ኛ). ቅሬታ ወይም የክርክር የሚፈታበት ነው፦  በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መጓተትን፣ የአቅም ለውጥን ወይም የሥራ ጥራትን በተመለከተ አለመግባባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በመሆኑም የዕለት ክስተት ማስታወሻው ሰነድ በቦታው ላይ ስለ ሁነቶች እና ሁኔታዎች ማስረጃ የሚያቀርብ ህጋዊ የግንባታ ሰነድ ሆኖ የሚቆጠር ስለሆነ በየትኛውም የፍትህ መንገድ ቅቡልነት አለው። ለምሳሌ ያህል፦ የጊዜ መጓተት የሚፈጥሩ ክስተቶች ካሉ (ለአብነት) ቀኑን ሙሉ ዝናብ ቢውል ወይም አካባቢው ረብሻ ቢሆን እነዚህ ክስተቶች የወሰዱትን ጊዜ (ሰዓት፣ ቀን፣ ወር) በቁጥር የምናሰላው ከ'Site Diary ላይ ለቅመን ስለሆነ ክስተቶቹ ባስተጓጎሉት የጊዜ መጠን ልክ በውሉ ላይ የነበረውን ግንባታ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ያግዛል። በሌላም በኩል (ለምሳሌ) የግንባታ ግብአት ማቅረብ የአሠሪው (Client/employer) ድርሻ ቢሆን እና የግንባታ ጊዜ በዚህ የተነሳ ቢጓተትበት ሥራ ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ እና የሠራተኞች ያለሥራ የቆዩበትን ክፍያ አሠሪው እንዲከፍል ሊጠይቅበት የሚችለው በ'Site Diary ላይ በአግባቡ የተቀመጠ መዝገብ ካለ ነው።

3ኛ) ጥራትን ለመቆጣጠር ማረጋገጫ ይሆናል፦ site diary መያዝ የጥራት ቁጥጥር እርምጃዎችን እና ፍተሻዎችን ለመመዝገብ ያስችላል። ለምሳሌ፦ በዕለቱ የተሠራው ሥራ የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት  ነው ብለን ብናስብ ለእያንዳንዱ ስትራክቸር የተጠቀምንው የፌሮ ብረት አይነትና ብዛት፣ የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ብዛት፣ የተከናወኑ የቤተሙከራ ሥራዎችና ውጤቶቻቸው እና የተስተዋሉ ያልተሟሉ ጉዳዮችን የምንመዘግብበት ስለሆነ የግንባታ ሥራ በዲዛይኑ መሰረት ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልቶ እየተከናወነ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ ጥራቱን እንድንቆጣጠር፣ የሚፈለገውን ደረጃና መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና አጠቃላይ የፕሮጀክት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛል።


ስለ Field Hammer Test

በአሁኑ ሰዓት ያለው የኮንክሬት ቅይጥ አተገባበር (Concrete Mixing Methodology) የተሻሻለ እየሆነ ቢመጣም አንዳድን ችግሮች ይስተዋላሉ

🏷ለምሳሌ ያህል፦ ወጥ የሆነ የጠጠር እና የአሸዋ አይነት አለመጠቀም፣ በቤተሙከራ የቅይጥ ምጥጥን (Mix Design Ratio) ሳይወሰንላቸው የተለያዩ የሲሚንቶ ምርት አይነቶች መጠቀን፣ ሌላ ቦታ ተቀይጦ የሚመጣ እና የኮንክሬት grade ለባለቤቱ በውል ያልተገለጸ አርማታን ለሙሌት መጠቀም (ready mix concrete) የመሳሰሉት ይገኙበታል።

እነዚህ ሂደቶች ለሕንጻው ወይም ለአርማታ መዋቅሩ ስትራክቸራል ፍላጎት አለመሟላት ሊያስከትል ይችላል።

በመሆኑም በሳይት ላይ የምንጠቀማቸው ሙከራዎች ያሉ ሲሆን በዋናነት ሐመር ቴስት (Hammer
⭐️በተለምዶ የመዶሻ ሙከራ በመባል የሚታወቀው Hammer Test ኮንክሪት ከተሞላ በኋላ ባሉት በ7ኛ እና በ28ኛ ቀናት ውስጥ ሊከናወን ይችላል (በእርግጥ በመካከል ባሉ ቀናት እና ከ28ኛ ቀን በኋላም እስከ 3 ወር ድረስ የሚተገብሩ ሀገራት አሉ)።

ይህ Non-Destructive Test ምድብ የሆነ የሙከራ ዘዴ የኮንክሪት ጥንካሬን የሚለካ ሲሆን ይህም ከአርማታ ውቅሩ ጥንካሬ ጋር የተያያዘ ምዘና ነው። በመሆኑም፦

1ኛ) በ7ኛ ቀን፦ የ7ኛ ቀን የመዶሻ ሙከራው የአርማታው መዋቅር (Concrete Structure) ያጎለበተውን የጥንካሬ እድገት የምለካበት ሲሆን እስከ 7ኛ ቀን ድረስ ከሚጠበቀው ዝቅተኛ ጥንካሬ (Minimum Compressive strength) ውስጥ ከ60% - 70% ድረስ ማጎልበት ይኖርበታል። 

2ኛ) በ28ኛ ቀን፦ በ28ኛ ቀን የሚደረግ ሙከራ የአርማታ ውቅሩ የሚጠበቅበትን 100% ጥንካሬ ማጎልበቱን የምናረጋግጥበት የሜዳ ሙከራ (Field Test) ነው።

⚡️ልብ ሊባል የሚገባው ይህ የሐመር ቴስት የኮንክሪት ጥንካሬን ለመወሰን ብቸኛው ዘዴ ሳይሆን እንደ ተጨማሪ ዘዴ መጠቀም የምንችለው መሆኑን ነው። ለበለጠ ውጤት ደግሞ Core Sampling፣ Cylinder test የመሳሰሉትን የጥንካሬ መፈተሻዎችን መጠቀም አለብን።


የሐመር ቴስት ትግበራ ጥንቃቄ (Cautions during field Hammer test)፦
~ ቢያንስ 10 ቦታዎች ላይ መሞከርና ማንበብ
~ እያንዳንዱ ናሙና እርስ በእርሱ ቢያንስ 2.5ሴ.ሜ ተራራቁ መሆን አለባቸው
~ ከኮንክሬት መዋቅሩ ጠርዝ ቢያንስ 10ሴ.ሜ መራቅ
~ ሐመር ቴስት መሳሪያው የሚመታበትን አንግል ማወቅ (90° ቢሆም ይመረጣል)
~ የአሥሩን ናሙናዎች አማካኝ ማስላትና እና የመጣውን አማካኝ (Average) ውጤት ለውሳኔ መጠቀም ናቸው።


https://t.me/gccon1


በ አርክቴክት Yohannes Mekonnen

⚡️ጎንደር ቤተ መንግሥት አዲስ መልክ

የጎንደር ቤተ መንግሥት ጥገና ህዝቡን እያሳሰበ ነው። ቢጫ ቀለም ያለው ይመስል የነበረው ቤተ መንግሥት አሁን በጣም ነጭ ሆኖ ይታያል እናም ብዙዎች ለምን እንደሆነ ይጠይቃሉ።
ቤተ መንግሥቱን ብዙ ጊዜ ጎብኝቼዋለሁ እና በአአዩ የኤምኤስሲ ተማሪዎቼ በቤተ መንግሥቱ ላይ በርካታ የጥበቃ ጥናቶችን በማስተባበር ተሳትፌያለሁ።
ከባለሙያ አንጻር ሲታይ የሚከተሉት ነጥቦች አሉ፡
* በጥገናው ወቅት አዲስ የኖራ ኮንክሪት መጠቀም በአጠቃላይ ነጭ ቀለም እንዲፈጠር አድርጓል፣ ይህም ቀስ በቀስ ወደ ቀላል ቢጫነት ይለወጣል።
* ከጥገናው በፊት አልጌ እና ላይከን ያጨለሙት የድንጋይ ገጽታዎች በጥገናው ወቅት ተጠርገዋል፣ ይህም አዲስ ነጭ መልክ አስገኝቷል።
* የብርሃን ልዩነት - በተለያየ ጊዜ እና በተለያየ ብርሃን የተነሱ ፎቶግራፎች የቀለም ለውጥን በእጅጉ ሊያመጡ ይችላሉ።
የኖራ ድንጋይ ሕንጻዎች እርጥበት እና አየር ሲጋለጡ የብረት ቆሻሻዎች ኦክሳይድ ስለሚሆኑ ከጊዜ በኋላ ቢጫ ይሆናሉ።


☑️https://t.me/gccon1


በሀገራችን_በህንጻ መዋቅር ጥናት ውስጥ ጥቂት ስለ Seismic (Earthquake) ታሳቢነት

ይህ ጽሁፍ የተዘጋጀው  ወቅታዊው የመሬት መንቀጥቀት ያሳደረብንን ስጋት አንጻር ጥቂት ለማለት ነው።

በሀገራችን ራሱን የቻለ የዲዛይን ኮድ አለን ካሉን የዲዛይን ኮዶች መካከል አንዱ ስለ Seismic Design የሚንመራበት ES EN 1998-1:2015 Design of Structures for Earthquake Resistance የሚለው ይገኝበታል።

የመዋቅር ዲዛይን የሚሰራው ባለሙያም ዲዛይኑን የሚያጸድቀውም መኮንን በዚሁ  መሰረት ዲዛይን ተሰርቶ ወደ ግንባታ እንዲገባ ፈርመው ይሰጣሉ።

ገንቢውም በዚህ ተመስርቶ እንዲገነባ ይጠበቅበታል።

የህንጻ መዋቅር ዲዛይን ታሳቢዎች
በመዋቅር ዲዛይን ታሳቢ የሚደረጉ ጭነቶች (Action loads) መካከል መሰረታዊ የሚባሉት Dead load, Live load Wind Load እና Seismic actions ሲሆኑ እንደ ሁኔታው እየታየ የተዘረዘሩት loadዎች በጋራ የሚያመጡት ጉዳት ከግንዛቤ የሚያስገባ እንደ አስፈላጊነቱ ከ 100 load combination ይሰራል።

ወደ መሬት መንቀጥቀጡ ስንገባ ለህንጻ ዲዛይንም በሬክተር ስኬል እየተለካ ሳይሆን ቀድሞ በተጠና አካባቢያዊ ተጠባቂ ሁኔታ የተከፋፈሉ ዞኖችን ታሳቢ አድርጎ በዚያ አካባቢ የሚጠበቀውን ከፍተኛ የምድር እንቅስቃሴ (Peak Ground Acceleration)  ታሳቢ በማድረግ በተሰሩ ቀመሮችና ለመቀመሪያ በተዘጋጁ Software በመታገዝ ነው።

ወደ ዲዛይን ታሳቢዎች ስንገባ

፩) ህንጻው የሚገባበት አካባቢ ለመሬት መንቀጥቀጥ ያለው ተጋላጭነትን ያገናዘበ ዞን (Seismic Zone) ( አዲስ አበባ ዞን 3 ሲሆን የሰሞኑ የአብዛኛው መሬት መንቀጥቀጥ መነሻ አፋር ክልል ብዙው ዞን 5 ነው)

፪) እያንዳንዱ ህንጻ ስንመለከተው በአርማታ በመሰራቱ ግትር ቢሆንም የመሬት መንቀጥቀጥን ለመከላከል እንዲችል የተወሰነ ያክል ተለማጭ እንዲሆን የሚያስችል ስሌት (Elastic Analysis) ይሰራለታል።

፫) የህንጻው መሰረት የሚያርፍበት የመሬት (አፈር/አለት)
ሁኔታ ( Ground Type) ታሳቢ ይደረጋል።

፬) የሚገነባው ህንጻ መዋቅር ዓይነት ( Structural Type and Behavioral Factor) የጥናቱ አካል ነው።

፭) የህንጻው ቅርጽና ቁመና (Structural Regularity) ከግምት ውስጥ ይገባል።

፮) የህንጻው መዋቅር አካላት Beam, Slab, Column, Wall, Number of Story, Number of Bays እና Foundation Types በልዩ ሁኔታ ታሳቢ ይደረጋሉ።

፯) ለግንባታ የምንጠቀማቸው ቁሶችና ጥራታቸው ( በተለይ የአርማታ የብረት ) በየመስፈሪያቸው የዲዛይኑ ግብዓት ሆነው ያገለግላሉ።

⭐️ከላይ የተዘረዘሩትና ሌሎችም ታሳቢዎች ታክለው በተሰራው የኮምፒውተር ሞዴል በሚሰጣቸው ከመቶ በላይ load combinations የከፋ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉትን እንዲቋቋም ተደርጎ ፣ የተለያዩ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው Modifier Factors ተካተው፣ የ Stability Check ተደርጎ የስትራክቸራል ዲዛይን ድሮዊንግ ይሰራል።

ለምን እንንቀጠቀጣለን?

⏺እንዲህ ተሰርቶ ለምን እንንቀጠቀጣለን? ለሚለው መልሱ ከላይ የዘረዘርኩት ማስረጃዎችን ታሳቢ ተደርጎ ከተሰራ ዲዛይን ላይ ሶስት ሞዴሎች ተያይዘዋልና ተመልከቷቸው።

⏺እንቅስቃሴዎቹ በተለያዩ load combinations ህንጻው ራሱን ሲከላከል የሚያሳይ የትክክለኛ ዲዛይን animation ነው።

⏺ይህ እንቅስቃሴ በአይናችን ልናየው ባንችልም የተሰቀሉ መብራቶች ሲንቀሳቀሱ፣የተቀመጠ ዕቃ ሲወድቅ፣ የተከፈተ መስኮት/በር ሲዘጋ...እንመለከታለን እኛም ህንጻው ላይ እንደተቀመጡት ዕቃዎች ንዝረቱ ይሰማናል እንጂ የህንጻውን እንቅስቃሴ ልንመለከት አንችልም ግን እየተንቀሳቀሰ ነው።

⏺ህንጻው ተንቀሳቀሰ ማለት ዲዛይኑ ትክክል አይደለም ማለት ወይም ይፈርሳል ማለት አይደለም። ዲዛይን በተደረገው ሞዴል መሰረት እራሱን እየተከላከለ ነው።

💫ምን ያሰጋናል?

፩) የግንባታ ጥራት
፪) ከዲዛይን ውጪ የተጨመሩ ወለሎች ያሏቸው ህንጻዎች
፫) የመሬት መንቀጥቀጥ የሚነሳባቸው አካባቢ ያሉ ቤቶች
፬) ሳይት ላይ መዋቅሮች የተደረጉ ማሻሻያዎች
፭) በተኛንበት ወይም በተቀመጥንበት የተንጠለጠሉ ቁሶች አናታችን ላይ ወድቀውብን አደጋ እንዳያደርሱብን!

Via ደሳለኝ ከበደ ህንጻ መሀንዲስ፣ ገንቢ፣ ሪል ስቴት አማካሪ




✌️



13 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.