ፍካሬ ዓለም
_____
(እሳት ወይ በረዶ)
የዓለምን ፍፃሜ.. ቀድመውን ያሰሉ
ትንቢት ተናጋሪ.. ብዙ ፃፎች አሉ፣
ምድር የምትጠፋው
በእሳት ነው የሚሉ።
ሌሎች በፊናቸው.. ጥልቅ የመረመሩ
የእሳቱን ፍፃሜ.. የተጠራጠሩ፣
የምድሪቱን መጥፊያ.. በውል ሲቀምሩ
በረዶ ይላሉ።
በፍካሬ ዓለም.. እጅግ ተመስጬ
ልመርጥ ብሞክር.. መፅሐፍ ገልጬ...
አንዴ በነበልባል... ደግሞ በአመዳይ፣
ምድር ስትከፈን.. ሲደረመስ ሠማይ፣
በትኩስ ቀዝቃዛው.. ዓለሙ ተንዶ...
መጥፊያችን ቸገረኝ... እሳት ወይ በረዶ?
ካየሁት ከማውቀው፣
ነገሩን ሳስበው....
ከነበልባል ስሜት.. ምኞት ካልተገራ፣
ከሚንቀለቀለው... የቁጣ ገሞራ፣
ከደምፍላት ግልቢያው
ልጓም ካላበጀ
እየገነፈለ ሀገሩን ከፈጀ... ፣
ካየሁ ከሰማሁት..
ነገሩን ሳስበው...
አላወላውልም እመሠክራለሁ፣
እሳት ኃይለኛ ነው!
በእሳት ትጠፋለች ዓለም በፍፃሜ፣
ከሚሉትም ጋራ ይሠምራል አቋሜ።
ነገር ግን ምድሪቱ
የምትጠፋበቱ፣
ሁለቴ ደጋግሞ ይሁን ከተባለ፣
ለመጥፊያ፣ ለመጥፊያ...
ሌላም መንገድ አለ፦
በቀዘቀዘ ልብ... ጥላቻ ሲነግስ...
በቀል ሲያንሠራራ.. ቂሙ ሲወራረስ...፣
ጥላቻ በርክቶ.. ማዕበል ሲያስነሳ
ሰውን ሰው ሲበላ፣ ዘመንን ሲነሳ...
ይህንም አውቃለሁ...
እመሠክራለሁ...፣
ለመቅሰፍት ለመቅሰፍት..
ለመጥፊያ ለመጥፊያ፣
በረዶም በቂ ነው
ዓለምን ለማጥፊያ
እንደ እሳት ቋያ።
— ሮበርት ፍሮስት፣ Fire and Ice (1920)፣
/ዝርው ትርጉም የራሴ/
@getem
@getem
@paappii
_____
(እሳት ወይ በረዶ)
የዓለምን ፍፃሜ.. ቀድመውን ያሰሉ
ትንቢት ተናጋሪ.. ብዙ ፃፎች አሉ፣
ምድር የምትጠፋው
በእሳት ነው የሚሉ።
ሌሎች በፊናቸው.. ጥልቅ የመረመሩ
የእሳቱን ፍፃሜ.. የተጠራጠሩ፣
የምድሪቱን መጥፊያ.. በውል ሲቀምሩ
በረዶ ይላሉ።
በፍካሬ ዓለም.. እጅግ ተመስጬ
ልመርጥ ብሞክር.. መፅሐፍ ገልጬ...
አንዴ በነበልባል... ደግሞ በአመዳይ፣
ምድር ስትከፈን.. ሲደረመስ ሠማይ፣
በትኩስ ቀዝቃዛው.. ዓለሙ ተንዶ...
መጥፊያችን ቸገረኝ... እሳት ወይ በረዶ?
ካየሁት ከማውቀው፣
ነገሩን ሳስበው....
ከነበልባል ስሜት.. ምኞት ካልተገራ፣
ከሚንቀለቀለው... የቁጣ ገሞራ፣
ከደምፍላት ግልቢያው
ልጓም ካላበጀ
እየገነፈለ ሀገሩን ከፈጀ... ፣
ካየሁ ከሰማሁት..
ነገሩን ሳስበው...
አላወላውልም እመሠክራለሁ፣
እሳት ኃይለኛ ነው!
በእሳት ትጠፋለች ዓለም በፍፃሜ፣
ከሚሉትም ጋራ ይሠምራል አቋሜ።
ነገር ግን ምድሪቱ
የምትጠፋበቱ፣
ሁለቴ ደጋግሞ ይሁን ከተባለ፣
ለመጥፊያ፣ ለመጥፊያ...
ሌላም መንገድ አለ፦
በቀዘቀዘ ልብ... ጥላቻ ሲነግስ...
በቀል ሲያንሠራራ.. ቂሙ ሲወራረስ...፣
ጥላቻ በርክቶ.. ማዕበል ሲያስነሳ
ሰውን ሰው ሲበላ፣ ዘመንን ሲነሳ...
ይህንም አውቃለሁ...
እመሠክራለሁ...፣
ለመቅሰፍት ለመቅሰፍት..
ለመጥፊያ ለመጥፊያ፣
በረዶም በቂ ነው
ዓለምን ለማጥፊያ
እንደ እሳት ቋያ።
— ሮበርት ፍሮስት፣ Fire and Ice (1920)፣
/ዝርው ትርጉም የራሴ/
@getem
@getem
@paappii