•
የፍቅርሽ መጋኛ
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
አዳም ያልከፈተው ንፋስ ያላገኘው
ጎራም ያላሉበት ማንም ያልጎበኘው
እዳው ላንተ ቢለኝ!•••••
ቅደም ስባል ካላይ ፊተኛው ቢያረገኝ
ከማላውቀው ልቧ ከኦናው ሰደደኝ
አንጃለት ነገሬ በጠራራ ፀሃይ
ይበርደኝ ጀምሯል!
ልቤም እየደቃ እንቅጥቅጡም ንሯል
ጠበል አያሽረው የሌለው መፍትሄ
በቀረብኝ ነሮ.........
ልቤን ባላሳትፍ ከልቧ ጉባኤ
አልችለው ብል ፍቅሯን እያንገበገበኝ
ውልብኝ እንደበላ እያውለበለበኝ
ቆማ ከደጃፏ ፈዛ እያየችኝ
ምነው ምን ባጠፋው?
በፍቅሯ መጋኛ ጨክና አስመታችኝ
መቼም ሆኖልሻል.......
እኔነቴ ሞላው ተንበርክኮልሻል
ሳይቸግር ሲያቀብጠኝ ውስጥሽ ተነክሬ
መላ አጣው መውጫውን ከዳኝ ጥንካሬ
ልቤ ነጋሪቱን ሲደልቅ ይውላል
በይ መተሽ አቁሚው መፈንዳት ከጅሏል
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel
የፍቅርሽ መጋኛ
#ገጣሚ ብሩክ የገኒ ልጅ (ብሩኬ)
አዳም ያልከፈተው ንፋስ ያላገኘው
ጎራም ያላሉበት ማንም ያልጎበኘው
እዳው ላንተ ቢለኝ!•••••
ቅደም ስባል ካላይ ፊተኛው ቢያረገኝ
ከማላውቀው ልቧ ከኦናው ሰደደኝ
አንጃለት ነገሬ በጠራራ ፀሃይ
ይበርደኝ ጀምሯል!
ልቤም እየደቃ እንቅጥቅጡም ንሯል
ጠበል አያሽረው የሌለው መፍትሄ
በቀረብኝ ነሮ.........
ልቤን ባላሳትፍ ከልቧ ጉባኤ
አልችለው ብል ፍቅሯን እያንገበገበኝ
ውልብኝ እንደበላ እያውለበለበኝ
ቆማ ከደጃፏ ፈዛ እያየችኝ
ምነው ምን ባጠፋው?
በፍቅሯ መጋኛ ጨክና አስመታችኝ
መቼም ሆኖልሻል.......
እኔነቴ ሞላው ተንበርክኮልሻል
ሳይቸግር ሲያቀብጠኝ ውስጥሽ ተነክሬ
መላ አጣው መውጫውን ከዳኝ ጥንካሬ
ልቤ ነጋሪቱን ሲደልቅ ይውላል
በይ መተሽ አቁሚው መፈንዳት ከጅሏል
°
°
JOIN US👇👇
@getem_besamuel
@getem_besamuel