ዎላይታ ሶዶ በአራቱም ማዕዘን መንገድ ዳር ላይ አንድ ተመሳሳይ ድምፅ ይሰማል
"ዘራ የአይጥ መርዝ"
ምን ማለት ነው አልን ከወዳጄ ጋር ደማችን ፈልቶ። "ይህኮ ፖለቲካ ነው" አለ ወዳጄ በንዴት የግንባሩ ደም ስር ተገትሮ
"እውነትህን ነው ይህንን መርዝ ያመጣ ሰው ጀርባ ይጠና" አልኩ ጥርሴን እያንቀጨቀጭኩ
"ሙሉ ከተማውን ዘራ የአይጥ መርዝ በሚል ስፒከር ያጨናነቁት የዎላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ከአይጥ ጋር ነው ውሏቸው የሚል ፖለቲካኮ ነው" አለ
"ና እንጠይቃቸው" ብለን ከፊታችን ወዳለው ሻጭ በወታደር እርምጃ ደረስን
ስልኬ ጮኸ። ከቤት ነው የተደወለልኝ
"ሄሎ ምን አልሽኝ?"
"ይኸው ዛሬም መከራ እያሳዩኝ ነው አይጦች። ከተማ ውስጥ ከሆንክ የአይጥ መርዝ ይዘህ ና"
"ቆይ ቆይ መርዙማ አይገዛም የጀርባ አጀንዳው መጠናት አለበት"
"ባክህ አትቀልድ ይኸው ባለፈው ሳምንት የገዛኸው ሱሪም መሀሉ ተበላኮ"
"ምን??? በዚህ ኑሮ ውድነት የገዛሁት ለዛውም ዕሁድ ቸርች ስሄድ አደርጋለሁ ብዬ ያስቀመጥኩት ሱሪዬዬዬዬ?"
"አው"
"ማነህ አንተ ዘራ መርዝ አንድ ደርዘን ስጠኝ"😊
✍ጥላሁን ሁሴን🤝
@getmnaleloch