🙏🙏🙏እነሆ የ 3 ቀን እድሜ ያለውን ግጥሜን ጋበዝኳችሁ፡፡🙏🙏🙏
የተፈጥሮ
የማየው ሰው ሁሉ አንቺን መሰሉብኝ
የፈገግታሽ መንፈስ በኔ ተጋብቶብኝ
ያስፈነድቀኛል እንደ ህፃናቱ
በውበትሽ ገለሽ አሸነፍሽኝ እቱ፡፡
የመዐዛሽ ጠረን ከሽቶሽ አይደለም
ጠቋራ ፀጉርሽም ያልተቀባ ቀለም
እጅሽ ለስላሳ ነው ህመም የሚያስረሳ
እጅግ በጣም አምሮ ለመንካት ሚያሳሳ፡፡
አይንሽማ ውዴ ከሁሉም ይለያል
በነጣ ወተት ላይ ያለ ቡና ይመስላል
የወገብሽ ቅጥነት ከዳሌሽ ተዳምሮ
ውብ አርጎ ፈጥሮሻል ፈጣሪ ቀምሮ፡፡
ደጋግሜ ባይሽ ትሆኛለሽ አዲስ
እንደገና መጣች በፀሃይ ወጋገን
ከወዲያኛው አድማስ
በዝግታ እየሄድሽ መሬቱን እረግጠሽ
እኔም ሳፈጥብሽ አንቺም ፈገግ እያልሽ፡፡
@gitmeyisdaw
✍✍✍ @yisdaw1
የተፈጥሮ
የማየው ሰው ሁሉ አንቺን መሰሉብኝ
የፈገግታሽ መንፈስ በኔ ተጋብቶብኝ
ያስፈነድቀኛል እንደ ህፃናቱ
በውበትሽ ገለሽ አሸነፍሽኝ እቱ፡፡
የመዐዛሽ ጠረን ከሽቶሽ አይደለም
ጠቋራ ፀጉርሽም ያልተቀባ ቀለም
እጅሽ ለስላሳ ነው ህመም የሚያስረሳ
እጅግ በጣም አምሮ ለመንካት ሚያሳሳ፡፡
አይንሽማ ውዴ ከሁሉም ይለያል
በነጣ ወተት ላይ ያለ ቡና ይመስላል
የወገብሽ ቅጥነት ከዳሌሽ ተዳምሮ
ውብ አርጎ ፈጥሮሻል ፈጣሪ ቀምሮ፡፡
ደጋግሜ ባይሽ ትሆኛለሽ አዲስ
እንደገና መጣች በፀሃይ ወጋገን
ከወዲያኛው አድማስ
በዝግታ እየሄድሽ መሬቱን እረግጠሽ
እኔም ሳፈጥብሽ አንቺም ፈገግ እያልሽ፡፡
@gitmeyisdaw
✍✍✍ @yisdaw1