ውዱ መልዕክተኛችን ﷺ በአንድ ሐዲሳቸው ላይ: «የኾነ ጊዜ ይመጣል ከኡመቶቼ መካከል 5 ነገርን የሚወዱ፤ አምስት ነገርን ደግሞ የሚረሱ ሰዎች ይመጣሉ። እነዚህ ሰዎች፦ይህንን ዱንያ ይወዳሉ፤ አኺራን ይረሳሉ። ገንዘብን ይወዳሉ የሒሳቡን ቀን ደግሞ ይዘነጋሉ። ፍጡርን ይወዳሉ ፈጣሪን ይረሳሉ። ሐጢያትን ይወዳሉ ተውበት ማድረግን ይረሳሉ። ቤተመንግስቶችን ይወዳሉ መቃብሮችን ደግሞ ይረሳሉ።» በማለት ተናገሩ።
سيأتي زمان على أمتي يحبون خمسا وينسون خمسا، و يحبون الدنيا و ينسون الآخرة، ويحبون المال وينسون الحساب، ويحبون الخلق وينسون الخالق، ويحبون الذنوب وينسون التوبة، ويحبون القصور وينسون المقبرة
#Category_1: «ዱንያን ይወዳሉ፤ አኺራን ይረሳሉ።»
አላህ «መጨረሻይቱም ዓለም ከመጀመራያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት።» እያለን አይ እኔ ዱንያ ትበጀኛለች ብለን ሳናስተውለው በዚህ ምርጫ ውስጥ የሰጠምን አለን። መጨረሻይቱ ዓለም ሩቅ ይመስለንና የቅርቢትዋን ዓለም አጥብቀን እንይዛለን። የዘላለሙን ዓለም መምረጥ የሚያስከፍለውን መስዋዕትነት ብሎም ህመሙን መክፈል ይከብደንና የጊዜያዊው ዓለም ያስቀመጠልንን አቋራጭ እንመርጣለን። አላህ ከእነዚህ ጎራ ከሚሆኑት አያድርገን
#Category_2: «ገንዘብን ይወዳሉ፤ የሒሳቡን ቀን ይዘነጋሉ።»
ገንዘብ ከሒሳብ ጋር ይተሳሰራል። በተሰማራንበት ዘርፍ ላይ ቀን በቀን ወጪ እና ገቢያችንን እንተሳሰባለን፤ በፍቅሩም እንሰክራለን። ጌታችን ሱረቱል ፈጅር ላይ «ወቱሂቡነል ማለ ሁበን ጀማ: ገንዘብንም ብዙ መውደድ ትወዳላችሁ።» እንደሚለን እጅጉኑ ገንዘብ ያውረናል። ገንዘቡን በሐላል መንገድ ያላገኘነው እንደሆነ ብሎም አላህ ፊት የምንቆምበትን የሒሳብ ቀን የማንፈራ እንደሆነ የሰው ሐቅ መውሰድ ላይ ፤ ስራ አሰርቶ አለመክፈል ላይ፤ ማጭበርበር እና ሚዛን ማጓደል ላይ ብርቱ እንሆናለን። ጌታችን ፊት የምንቀርብበት ጊዜ ሩቅ ይሆንብናል፤ ከዘንጊዎቹም እንሆናለን። የምንገነዘበው የውመል አኺር ስንሄድ ነው። የምንገዘብበትን moment ጌታችን በዚህ መልክ ይገልፀዋል
وَجِيءَ يَوْمَئِذٍ بِجَهَنَّمَ ۚ يَوْمَئِذٍ يَتَذَكَّرُ الْإِنسَانُ وَأَنَّىٰ لَهُ الذِّكْرَىٰ
«ገሐነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ በዚያ ቀን ሰው (ጥፋቱን) ይገነዘባል፡፡ መገንዘብም ለእርሱ ከየቱ?» ... አላህ ከዚህ ጎራ ከመሆን ይጠብቀን!
#Category_3: «ፍጡርን ይወዳሉ፤ ፈጣሪን ይረሳሉ።»
የሰዎችን attention፤ የሰዎችን ውዴታ crave በሚያደርጉት ልክ የፈጣሪያቸውን ውዴታ ለማግኘት አይቻኮሉም። አንድ ወንድ ወይም ሴት ለሚወዳት/ ለምትወደው ሰው ሲሉ እራሳቸውን አሳልፈው እንደሚሰጡት ሁሉ ለፈጠራቸው አምላክ ብዙ መስዋዕትነት የማይጠይቀውን አምልኮ ተግባር ላይ ለማዋል ይሰስታሉ። ቪው ለማግኘትና ፎሎወር ለማብዛት መከራ በሚበላበት ተጨባጭ የአል ወዱድ'ን እይታ እንዘነጋለን። ጌታችን ሲወደን መላዕኮችን ሁሉ "እገሌን ውደደው" ብሎ የማይተመኑ ፎሎወሮችን እንደሚሰጠን እንዘነጋለን።
አላህ ያስረዳን!
#Category_4: «ሐጢዓትን ይወዳሉ፤ ተውበት ማድረግን ይረሳሉ።»
ሰዎች ሐጢዓትን እንወዳለን ብለው ላይናገሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሐጢዓት'ን የመስራት መንገድ ቀላል ሆኖብን የተውበት መንገድ ሲከብደን ማዕሲያ'ን እንላመዳለን። "ምን ችግር አለው?" ወደሚል ድፍረት'ም ያደርሳል። አላህን ሐያዕ ማድረግ ይቀራል። proudly መጥፎ ስራዎችን publicly ማሳየትን Normalize እናደርጋለን። አንዳንዶች ደግሞ ዝሙትን እንደፈለጉ exercise ለማድረግ የእስልምና ህግጋቶች'ን ሽፋን ማድረግ ላይ ብልጥ ለመሆን ይሞክራሉ። ሐጢዓት ላይ መለከፍ፤ የተውበትን መንገድ መርሳት ማለት ይሄ ነው። 😢... አላህ ከዚህም ጎራ ከመመደብ ይጠብቀን!
#Category_5: «ቤተመንግስቶችን ይወዳሉ፤ መቃብሮችን ደግሞ ይረሳሉ።»
Fancy የሆኑ፤ የተንጣለሉ ንብረቶችን እንደምንመኘው ሁሉ መቃብር ስፍራዎችን መጎብኘት ሩቅ ይሆንብናል። የታመመ መጠየቅን በጊዜ ሂደት እንረሳለን። ቁስ ሟሟላት ላይ በተለይም ውድ የሆኑ ንብረቶችን own ማድረግ እንደምንወደው ሁሉ ከዚህ ከልክ ያለ ፍቅርን የሚያስታግስልንን ሞት እጅጉኑ እንዘነጋለን። "እገሌ ሞተ" የሚል ዜና ብዙም አያስደነግጠንም። ይልቁኑ በብዛት መፎካከር ላይ እናተኩራለን፤ አላህ እራሱ ሱረቱል ተካሱር ላይ: «በብዛት መፎካከር ጌታችሁን ከመገዛት አዘናጋችሁ» ካለ በኃላ "ሐታ ዙርቱሙል መቃቢር: መቃብሮችን እስከ ጎበኛችሁ ድረስ።" የሚለውን ያስከትላል።
እገሌ የሆነ ብራንድ ልብስ ለበሰ እኛም እንደ እገሌ ወይም ከሱ የተሻለውን ለመልበስ እንሽቀዳደማለን። እገሊት የሆነ ፀዴ ቤት ገዛች እኛም እሷን ለመምሰል ወይም በልጦ ለመገኘት የፉክክር ሜዳ ውስጥ እንዘፈቃለን። we can talk about smart phones, brand bags , car and others.... መሐል ላይ ግን ሁሉን ያስገኘውን አምላክ ማመስገን ይረሳል። የሰጠውን በሰከንድ ልዩነቶች ውስጥ መውሰድና ማውደም የሚችለውን ጌታ ይዘነጋል። ሐብቱ delusion ውስጥ ከቶን አላህን ከመገዛት ያዘናጋናል።
ሰሐቢዩ ዑበይ ኢቢን ካዕብ ረዲየሏሁ አንህ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የቁርኣን አያህ እስኪመስለን ድረስ በብዙ አጋጣሚ ላይ እንዲህ ይሉን ነበር ይላሉ።
لو أن لابن آدم وادياً من ذهب أحب أن يكون له واديان
«የአደም ልጅ የወርቅ ሸለቆ ቢኖረው እንኳን፤ የተሰጠውን አይነት ሌላ ይመኛል።» አሉን፤ ይህ ንግግራቸው'ም ሱረቱል ተካሱር ከወረደ በኃላ ገባን ይላሉ ዑበይ። 🤎
ፉክክሩ ደግሞ ቀብር እስክንገባ የሚከተለን ነው። ምክንያቱም እነዛ ዘመናችንን የተፎካከርንባቸው ሐብቶች፤ ከጌታችን ያዘናጋን ንብረት ስንሞት ዋጋ አይኖረውም። መቃብር ይዘነው የምንገባው ስራችንን እና ስራችንን ብቻ ይሆናል። አላህ ከእነዚህ ምድቦች ውስጥ እንዳንሆን ይጠብቀን! አሚይንን
Nadia Biya
@highlight