✨ የጓዳችንን የሚያውቅ፣ በአደባባይ የሚያከብር አምላክ!
እግዚአብሔር በአደባባይ በሚታየው ጨዋነታችን አይታለልም፤ የጓዳችንን ድክመትና ምስጢር ጠንቅቆ ያውቃልና።
ነገር ግን የጓዳችንን ነውር ማወቁ እኛን እንዲንቀን ወይም ተስፋ እንዲቆርጥብን አያደርገውም። ይልቁንም፦
• በጓዳ ደብቆ ይገሥፃል
• በፍቅር ይመክራል
• በትዕግሥት ያስተምራል
• በምሕረቱ በደልን ሽሮ፣ በጸጋው የቅድስና ኀይልን ያስታጥቃል። ከዚያም በአደባባይ በእውነተኛ ክብር ያከብራል!
የእግዚአብሔር ፍቅር ድክመታችንን አጋልጦ የሚያዋርድ ሳይሆን፣ በጓዳ አርሞና አቅንቶ በአደባባይ ለክብር የሚያበቃ ነው።
መልካም ጊዜ! 🕊️
(ለወዳጅዎ #share ያድርጉት)
@GOSP_EL