በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ሙሉ በሙ ካሳለፉ አምስት ትምህርት ቤቶች ሦስቱ በአማራ ክልል የሚገኙ ናቸው።
ሦስቱ ትምህርት ቤቶች፦
- ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት፣
- ሐዲስ ዓለማየሁ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት፣
- ባሕር ዳር ስቴም ትምህርት ቤት ናቸው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በማኅበራዊ ሳይንስ ከፍተኛውን ውጤት ያስመዘገበው ተማሪም የሐዲስ ዓለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ነው።
እንደ አማራ ክልል ትምህርት ቢሮ መረጃ በሐዲስ ዓለማየሁ አዳሪ ትምህርት ቤት እና በደሴ ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት በድምሩ 32 ተማሪዎች 600 እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡
አማራ ክልል በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ክልሎች ባለፉት ዓመታት በሰላም እጦት ክፉኛ እየተጎዳ ቢሆንም መሰል ውጤቶች መመዝገባቸው ለቀጣይ ተስፋ ሰጪ ነው ብሏል።
የአማራ ክልል ተማሪዎች የጥይት ድምጽ እየሰሙ ተምረዋል፤ የጥይት ድምጽ እየሰሙ ተፈትነዋል፡፡ አብዘኛዎቹ የክልሉ ተማሪዎች በጦርነት ምክንያት በወደሙ እና በተዘረፉ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተገደዋል፡፡ በፈተና ወቅት በተፈጠረ አለመረጋጋት ፈተናውን አቋርጠው የወጡ ተማሪዎች እንደነበሩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
በአዳሪ ትምህርት ቤቶች እየተመዘገበ ያለው ውጤት ትምህርት ሰጭ መሆኑን የገለጸው ቢሮው፤ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ማስፋት ያስፈጋል ብሏል። #አሚኮ
🙏Share share🙏
👇👇ለተጨማሪ መረጃ👇👇
https://t.me/grade12_results