Bahiru Teka dan repost
👉 የሚሊኒየም ፕሮግራምና የበዋና ሐዲስ
አንዳንድ ወንድሞች የሚሊኒየሙ ፕሮግራም ከሸሪዓ ጋር ይጋጫል እየተባለ ነው መረጃው ደግሞ የበዋና ሐዲስ ነው እየተባለነው የሚል ጥያቄ እያቀረቡ ስለሆነ የተወሰነ ነገር ለማለት ተገደድኩ ።
በመጀመሪያ ደረጃ አንድን ነገር ይቻላል አይቻልም ወይም ከሸሪዓ ጋር ይጋጫል አይጋጭም ለማለት ስለዛ ነገር ማወቅ ግድ ነው ። በመሆኑም ስለሚሊኒየሙ ፕሮግራምና የበዋና ሐዲስን ለማገናኘት ስለነዚህ ማወቅ የግድ ይሆናል ።
🔹 የበዋና ሐዲስ ማለት ብዙዎቻችን ኪታቡ ተውሒድ ውስጥ " ባቡ ላዩዝበሑ ሊላህ ቢመካኒን ዩዝበሑ ፊሂ ሊጘይሪላህ " ( ከአላህ ውጪ ላለ ነገር በሚታረድበት ቦታ ለአላህ አይታረድም ) በሚለው ባብ እንደምናውቀው አንድ ሰው መጥቶ ለነብዩ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም – በዋና በሚባል ቦታ ግመል ለማረድ ስለት አድርጌያለሁና ልረድ ወይ ብሎ ጠየቃች ።
የአላህ መልእክኛ ዞር ብለው ለባል ደረቦቻቸው ይህ የተባለው ቦታ የመሀይማን ህዝቦች ከሚያመልኳቸው ጣኦታቶች ውስጥ ነበረበትን ? አሉ ። አይ አልነበረበትም አሏቸው ። ሁለተኛ ጥያቄ እንዲህ ብለው አቀረቡ " ከመሀይማን ህዝቦች ዒድ ይከበርበት ነበርን ? ( በተወሰነ ጊዜ እየተመላለሱ ዒዳቸውን ያከብሩ ነበርን ) አሉ ። አይ አሏቸው ። ወደ ሰውየው ዞረው ስለትህን ሙላ ( እረድ ) አሉት ።
🔹 ከሐዲሱ የምንረዳው : –
አንደኛ – አንድ ሰው የሚያጠራጥረውነገር ሲኖር የእውቀት ባልተቤቶችን መጠየቅ እንዳለበት ።
ሁለተኛ – ስለአንድ ነገር የተጠየቀ ሰው የተጠየቀው ነገር ባህሪይ ወይም ሁኔታ ዝርዝር ነገር ማወቅ የሚያስፈልገው ከሆነ ስለዛ ነገር መልስ ከመስጠቱ በፊት ዝርዝር ሁኔታውን መጠየቅ እንዳለበት ።
ሶስተኛ – አንድ ከአላህ ውጪ ያለ ነገር ሊመለክበት በተዘጋጀ ቦታ ላይ ንያው ቢለያይም ተመሳሳይ የዒባዳ አይነት መስራት እንደማይቻል ና የመሳሰሉት ይገኙበታል ።
🔹 የሚሊኒየም አዳራሽ ሁኔታ
ብዙዎቻችን ሚሊኒየም አዳራሽ ሲባል አእምሯችን ላይ የሚመጣው ፈሳድ የሚሰራበት ቦታ መሆኑ ነው ። ምክንያቱ አንዳንድ ጊዜ የምንሰማቸው የፕሮግራሞች ማስታወቂያዎች ሊሆን ይችላል ።
ነገር ግን ሚሊኒየም አዳራሽ ማለት ለክራይ የተሰሩ ብዙ አይነት አዳራሾች ያሉበት ቦታ ነው ። ስለዚህ ሚሊኒየም የተዘጋጀው ለአምልኮ ወይም ለበአል ማክበሪያ ተብሎ ሳይሆን ለኪራይ ነው ማለት ነው ። የተከራየው ሰው የፈለገውን ነገር ይሰራበታል ። በውስጡ 5ሺህ, 3 ሺህ, 2ሺህ, 1ሺህ ሰው የሚዙ የተለያዩ አዳራሾች ያሉበት ሲሆን ዋናውና የሚሊኒየም አዳራሽ በመባል የሚታወቀው 5 ሺህ ሰው የሚዝ ሲሆን የቀን ኪራዩ ወደ ሁለት ሚሊየን ብር አካባቢ ይጠጋል ። ውድ ከመሆኑ የተነሳ በአብዛኛው ትላልቅ የመንግስት ተቋማቶች ስብሰባ ነው የሚደረግበት ። አንዳንዴ የሀብታሞች ሰርግና የሙዚቃ ዝግጅት ሊደረግበት ይችላል ። ሌሎቹ አዳራሾች ከዚኛው በብዙ ነገር አይገናኙም ኪራያቸውም ዝቅ ያለ ነው ። ነገር ግን ሁሉም ለኪራይ የተዘጋጁ የንግድ አዳራሾች ናቸው ።
🔹 የኛ ኮንፈረንስ ከበዋና ሐዲስ ጋር ምን ያገናኘዋል ከተባለ መጀመሪያ ስለ አዳራሹ ዝርዝር መረጃ ቦታው ሄደን ጠየቅን ። ቀጥሎ ከመሻኢኾቻችን ጋር በሸሪዓ እይታ ተነጋገርን ። ማለትም ዑለሞችን በዚህ ቦታ ላይ ፕሮግራም ስለማዘጋጀት ምን እንደሚሉ ጠየቅን ውጤቱ ልክ እንደ ቦዋና ሚሊኒየም የጣኦት ማምለኪያም ይሁን የከሀዲያን ዒድ ቦታ ስላልሆነና የኛ ፕሮግራም በባህሪይ ከየትኛውም ሌላ ፕሮግራም ጋር ስለማይገናኝ ሸሪዓዊ ክልከላ የለበትም ይካሄድ የሚል መልስ አግኝተን ነው የጀመርነው ።
በመሆኑም የበዋና ሐዲስ መረጃነቱ ቀጥሉ ለሚለው እንጂ ተከልከሉ ለሚለው አይደለም ማለት ነው ።
የሚሊኒየምን አዳራሾች ምሳሌ በሌሎች ኪራይ ቤቶችም ማየት ይቻላል ። ለምሳሌ አንድ ሰው ለኪራይ ብሎ ቤት ሰራና መጀመሪያ ዘፋኝ ተከራየው በሙዚቃ አካባቢውን ሲቀውጥና ሲለማመድበት ቀይቶ ለቆት ሄደ ። ቀጥሎ ሌላ ሰው ተከራየውና እየሱስ ጌታ ነው እያለ የተወሰነ ጊዜ ቆይቶ ወጣ ። ከዛ ሙስሊም ተከራይቶት ይቀራበት ፣ ይሰገድበት ፣ ዳዕዋ ይደረግበት ጀመር እንደማለት ነው ።
ውድ ወንድሞች በእንደነዚህ አይነት ትላልቅ ጉዳዮች ላይ የምናውቀውን ሐዲስ ወይም ቁርኣን በራሳችን ግንዛቤ መረጃ አድርገን ብይን ከመስጠታችን በፊት ከኛ በላይ ያሉ ዑለሞችን መጠየቅ ይኖርብናል እላለሁ ።
አላህ በሐቅ ላይ ከሚመካከሩ ባሮቹ ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka