[እኔ አለሁ እንዳለሁ
እንዴት ነሽ እመ?]
ከጦርነት ቀጠና ወጥቼ አዲስ አበባ እንደገባሁ የመጀመሪያው ስራየ ስራቦታ ጎራ ማለትና ቤት መፈለግ ነበር። እውነት ለመናገር ከሆነ አዲስ በብዙ ግልምጫዎችና በሰቃዥ የኑሮ ውድነት የታጀበች እጅግ ባይተዋር ከተማ ሆና ነው የጠበቀችኝ።
አዲስ አበባ ቁመት ሙሉ እንባ ስጋ ሙሉ ኧረወይለሊቴ ሆናለች ወገን።
“ጃክሮስ ቆንጆ ቤት አግኝቼልሀለሁ” ደላላው ነበር
ሄድኩ
ቤቷ ሁለት በሶስት ናት። ጭራሽ መሀከሉ ላይ እንደሰፊው ህዝብ መድረሻ ያጣ የሚመስል ኮለን ተገትሯል።
“ኧኸ እንዴት ነው ወደድሻት? 3500 ናት”
ምን ነካህ ደላላ!? ይሄኮ እንኳን አልጋ ሊያዘረጋ ጠረንጴዛና ወንበር ሊይዝ ፍራሽ እንኳን ካላጠፍኩት አያስነጥፈኝም።
😳
የውሻውን ቤት ነው እንዴ ልታከራዮኝ ያሰባችሁት🤔
“ውሻውማ የተሻለ አግኝቶ ስለወጣ ነው እምናከራይህ” አከራዩዋ
እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴
ደግሞ ሌላ ቤት መስቀል ፍላወር
“ድርድር የለውም። 6 ክፈል” ሸምገል ያሉ ናቸው አከራዮ
ቆንጀት ያለ ቤት ነው እሺ እከፍላለሁ
“ታመሻለህ?”
አዎ አንዳንዴ ሚቲንግ ሲኖረኝ እስከ 4 ምናምን ላመሽ እችላለሁ
“አይሆንም አይሆንም እስከ 2 ልፍቀድልህ”
እንዴ ልጅዎ አደረጉኝ እንዴ!
“ምን አልክ? ይሄንም እኔ ሆኜ ነው”
እንዴ ትራንስፖርቱ ራሱ ያስመሻል እኮ። ቁልፍ ካለ ይስጡኝ ላስቀርጸው።
“ቁልፍ? ለምንድን ነው ቁልፍ እምሰጥህ? አምሽተህ እየገባህ ልታዘርፈኝ!”
እ😳
“ተወው ለሌላ አከራየዋለሁ። በዚያ በኩል ውጣ”
እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴
ከሰአቱን ድክም ሲለኝ ልረፍ ምሳም ልብላ ብየ የሆነ ሆቴል ገባሁ
ቅቅል ተፈርሾ አምጪልኝ።
By the way ቅቅል ኢዝ ማይ ተወዳጅ ምግብ
በድንች፣ በካሮት እና በሆኑ ቅጠላቅጠሎች የታጀቡ 3 ግድንግድየ ቅልጥሞች መረቅ ደፍቀው መጡ
ተጠራጠራጠርኩ
ሂሳብ ስንት ነው እናት?
“550”
እ😳
እንስቷ እንባዋ ደርሶ ግጥም አለ🥴
ከጎጃም በእግርና በባጃጅ ያስወጣኸኝ አንድየ አንተ ታውቃለህ ብየ በላሁት
ሂሳብ ከፍየ ስወጣ ከጀርባየ የሆነ ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል አስተጋጇ እጇን እያውለበለበች
“ዌል ካም ቱ አዲስ የዝቅተኛው ማህበረሰብ አባል” ስትለኝ ደረስኩ
እስኪ ሆዴ ቻለው ቻለው ቻለው እያልኩ ወደስራ ቦታየ ወክ አደርግ ጀመር
አለም ሲኒማን እልፍ ስትሉ ባስ መጠበቂያው አለአይደል፣ አንድ በግምት 60 ዎቹ አካባቢ የሆነ ሰውየ እግሩን አጥፎ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ አይኑን ጨፍኖ
“ኦም…ኦ….ም…. ኦ….ም” ይላል
ሆዴ ቦጭ ቦጭ አለ
ዝርዝር የአምስት ብር ሳንቲሞች መፀወትኩት
ሰውየው ግን አንድ አይኑን ገልጦ
“ወንድም ዮጋ እየሰራሁ እንጂ እየለመንኩ አይደለም። አዲስ አበባ መቆየት ከቻልክ ይጠቅምሀል ገንዘብህን ያዝ” አለኝ
አደነጋገጤ😳
ህዝቤ እንዳለ ለቆ ነው🤔
ቢሮ ልደርስ አካባቢ የሆነ ሙዚቃ ሰመቼ ዞር ስል የሬሳ ሳጥን የሚሸጥበት ሱቅ ላይ ሁለት ወጣቶች እየቃሙ በትንሽየ ስፒከር
“ጉርምርሜ ና ጉርምርሜ ያሆ መሌ ያሆ መሌ ና ጉርምርምርሜ” የሚል ሙዚቃ ያዳምጣሉ
ጆሮየ ፕራንክ ነው በለኝ😳
እውነት ለመናገር የሬሳ ሳጥን መሸጫ ውስጥ ሙዚቃ ስሰማ ይህ የመጀመሪያየ ነው
“የኔ ልጅ ተውው አሽሙር ነው። መንገድህን ቀጥል” አሉኝ በአጠገቤ ሲያልፉ የነበሩ እናት
ወይ አዲስ አበባ እንዲህ ሁሉን ነገር ድብልቅልቅ አደርጋ ትጠብቀኝ። ታክሲዎች ትንሽ መንገድ አምቦራችተውህ 10 ብር አምጣ ይሉሀል። ከመሸብህ ይሄ ብር ሁለት እጥፍ ሁሉ ሊሆን ይችላል። ራይድ ልያዝ ካልክ happy textile road bruh በሶስት ቀን ሆድህ ፈርደሀል ማለት ነው!
ደግሞ ሰው ምንድን ነው እንዲህ የተፈራራው🤔ለንደን ያለህ ይመስል ማንም ሰላም ሊልህ አይፈልግም። ሰላምታ ብታቀርብም አበጀህ የሚልህ የለም።
ወንድም ሰአት ስንት ነ..?
“እግዜር ይስጥልኝ እኔ ራሱ የታክሲ ብቻ ነው የቀረኝ። እህል ከቀመስኩ ዛሬ ሁለት ወሬን ደፈንኩ”
እ😳
“ተወኝ በቃ እኔ የትኛውንም ፖለቲካ ፓርቲ አልደግፍም። የሁሉም ባንክ አካውንት አለኝ”
ዋ ኧረ ምንጉድ ነው ብየ ወደ ጎዳናየ ተመለስኩ
ወገን እንግዲህ አዲስ ጥይት አልተተኮሰባትም እንጂ ጦርነት ላይ ናት የሚባለው ነገር እውነት ነው መሰል…
ቢጨንቀኝ
እመ ጋ ደወልኩና
“እመ ለካንስ ይሆን መስሎኝ እንዲያው ሳላውቀው ከሞት ሸሽቼ ወደ ሞት ነው የመጣሁት” አልኳት
እመ ግን ሳግ በሚተናነቀው ድምፅ
ምን አለችኝ?
“ልጅ ታምሩ ምን የሚያጓጓ ህይወት ኖሮህ ነው ሞት የሚያስፈራህ!”
እንባየ ደርሶ ግጥም አለ🥴
@wegoch@wegoch@paappiiBy Tamiru Temesgen