ስለዚህ ጉዳይ እንዲብራራ በጠየቃችሁት መሰረት ነገሩን ይበልጥ ለማብራራት እና ረዘም ባለ ጽሁፍም ለማቅረብ ስሞክር ነበር፣ እና የደረስኩበት ነገር ቢኖር ጉዳዩ የተወሳሰበ መሆኑን ነው። በዚህ ቻናልም በኩል ርዕሱን በማስረዳት በኩል ስህተት ተፈጥሯል ስለዚህም ይቅርታ ለመጠየቅ እወዳለሁ።
እንዲሁም ከላይ ሼር የተደረገው ቪድዮ ላይ ያለው ጥንተ አብሶ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ አይደለም የሚለው ሙሉ በሙሉ ትክክል አይደለም። ጥንተ አብሶ ማለት በአጭሩ የቀደመው በደል፣ አዳም እና ሄዋን የሰሩት ሃጢአት ነው። ነገር ግን በነሱ ሃጢአት ምክንያት እኛ ልጆቻቸው የሃጢአቱን ፍዳ ወረስን ወይስ ሃጢአቱንም ጭምር ወረስን የሚለው ጋ ነው ልዩነቱ። በዚህም ካቶሊኮች ሃጢአቱንም ጭምር በውርስ እንደተቀበልን ያስተምራሉ። ይህን አስተምህሮአቸውን ዋና አነሳሽ የሆነው ደግሞ አውግስጢኖስ ነው። ነገር ግን ከአውግስጢኖስ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ወይም ከርሱ በፊት የነበሩት እና ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ቅዱስ ቄርሎስ እና ቅዱስ ጎርጎርዮስን ስንመለከት የቀደመው የአዳም ሃጢአት እኛን የወደቀ የተዋረደ ባህሪ እንድንላበስ አደረገን ይላሉ እንጂ የአዳም ሃጢአት እኛም እንዳለብን ወይም እኛ እንደሰራነው ይቆጠራል፣ ወይም እኛም እንጠየቅበታለን አይሉም።
የኛ ቤተክርስቲያን እና የኢርትራ ቤትክርስቲያን አባቶች ስለ ጉዳዩ ምን ይላሉ የሚለውን የተለያዩ ጽሁፎች እንዳየሁት የሚሉት በአዳም እና ሄዋን ሃጢአት ምክንያት እኛ የሃጢአታቸው መዘዝ የሆነው ሞት፣ እና ለሃጢአት የሚያደላው የወደቀው ባህሪ ወረስን የሚለውን አቋም ነው የሚይዙት። ስለዚህ ያ ነው ከካቶሊኮች የሚለየን። ጉዳዩን ይበልጥ ከመዘዝነው ሌላም ብዙ ነገር አብሮት ይነሳል። ለምሳሌ immaculate conception የሚባለው ድንግል ማርያም ያለዚህ የውርስ ሃጢአት ነው የተወለደችው የሚለውን ያነሳሉ።
ነገር ግን ይህ አስተምህሮ በኛ ቤትክርስቲያን ስነ መለኮታዊ አስተምህሮ ውስጥ የሚገኝ አይሆንም። ምክንያቱም መጀመርያም እኛ የአዳምን ሃጢአት ወርሰናል ብለን አናምንም። ይልቁንም ስለ ድንግል ማርያም መወለድ የምናምነው ነገር ቢኖር እኛ ያለንን የጎሰቆለ ባህርይ ይዛ አልተወለደችም፣ እንዲሁም በህግ እና በስርአት፣ ያለ ዝሙት ወይም ስጋ ፈቃድ ተወለደች እንጂ።