Noma’lum dan repost
.ለወንድም መሀመድ ስንዴው
ባረከሏሁ ለከ ወባረከ አለይከ ወጀመአ በይነኩማ ፊ ኸይር ብያለሁ
#ደስታህ_ነው_ደስታችን_l!!
-------------------=--------------
አሏህ በፈቃዱ በኢስላም ላይ ፈጥሮን፡
በርሱ ላይ አፅንቶ ሐቅ ላይ አኑሮን፡
በውብ ሰገነት ላይ በምቾት አስፍሮን፡
ደብዳቤውን ልኮ በቃሉ አነጋግሮን፡
በማይላላ ገመድ በሱና አስተሳስሮን፡
በእምነት ወንድምነት አስውቦ አሳምሮን፡
በመንሀጀ ሰለፍ ነፃነት ለግሶን፡
በቁርአን ተአምር አንድ ህግ አቋድሶን፡
የነብዩ ጥሪ ለኔም ላንተም ደርሶን፡
ከጥመት አውጥቶ በሱናው አድሶን፡
ደስታህን ሰማሁኝ ዛሬ እዚህ አድርሶን፡
-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-
ደስታህን በአካል ባልካፈልህም፡
ሀሳቤ ካንተ ነው ወላሒ አልዋሽህም፡
የሰማሁኝ ጌዜ ብስራት የደስታህን፡
የሀላሉን ተግባር ቅዱስ ጋብቻህን፡
ተደሳሁኝ ባንተ ድጋሜ እንደገና፡
እንኳን ሀይ አደረክ የነብዩን ሱና፡
ሌሎች ሳይፈትኑህ ሳያውቅህ ብልግና፡
ቀጥታ ከዘመትክ ወደ ብልፅግና፡
እንኳን ተሳካልህ እሰይ የኔ ጀግና፡
#ልመርቅ_አሚን_በል፡
#ዱዐየን_ተቀበል__!!
--+-----------------------------
ምኞትህ ይሳካ ትዳር ይስመርልህ፡
ደስታን የሚያጣጥም ስኬት ይሁንልህ፡
ዱንያ ታገልግልህ ከሱና ሳትወጣ፡
ማሯ ይፍሰስብህ ሬት ሳታጠጣ፡
በእውነተኛ ፍቅር ትዳርህ ይወደስ፡
ሞደል ሁን ለሌሎች ወንድሜ ተቀደስ፡
ቤትህ ሰፊ ይሁን መቆለፍ የሌለው፡
ሚስኪን እየመጣ ይውሰድ በሚችለው፡
በደስታ ተሞላ ማንም ይውሰድብህ፡
ብቻ ምንም ይሁን ካንተ አይጉደልብህ፡
በረካ አላህ ይስጥህ በሐላል ገንዘብህ፡
በሁለቱም ሀገር ፊትና አይድረስብህ፡
#አሚንበል!!
ባለቤትህ ትሁን የተውሒድ አርበኛ፡
የቢዲአ ጠላት የሱና ዘበኛ፡
እንደዚህች ያለች ልጅ ኢማኗ የሞላ፡
ለአለሙ ጌታ የገባች መሀላ፡
አንተን ለማስደሰት የማታጣ መላ፡
ከአርሹ ባለቤት የተሰጠች ሲሳይ፡
እውነተኛ ፍቅሯን ላንተ የምታሳይ፡
ሰላም የሞላበት ይሁንልህ ንፁህ፡
ፍቅርና ፀባይ ተባብረው ያንፁህ፡
#አሚን_በል__!!
ይህንን ፀሎቴን በደስታ ተቀበል፡
እኔ ልመርቅህ አንተ ብቻ አሚን በል፡
በሁለቱም ሀገር ትሁን ባለቤትህ፡
ጀግና ልጆች ውለድ ከውድቷ ሚስትህ፡
ጊዜውን ጠብቆ ናፍቆት ሳያሳሳን፡
ምን ሆነብን እያልን ስጋት ሳያከሳን፡
በጥበብ ተሞልቶ ሆኖ ግሩም ልሳን፡
ደስታ ተሸክሞ ፈጥኖ ይምጣ ሀሳን፡
#አሚን_በል__!!
የነብር አለጋ እንደ አንበሳ ግልገል፡
ለተውሒድ ለሱና ሳትደክም ታገል፡
አንተም ባለቤትህ ሁኑልን አበባ፡
ጣፋጭ ፍሬም ሁኑ የሌለው ገለባ፡
የውደታችሁ ልክ የፍቅራችሁ ማማር፡
ሁሌም ጣፋጭ ሁኑ እንደ ወለላ ማር፡
#አሚን_በል__!!
#ለማንኛውም___!!
ማሻ አሏህ ብለናል ደስታህ ነው ደስታችን፡
-------------------------------------------------
መሀመድ ሰንዴው
እና ሀውለት
ጥምረት እስከ ............ጀነት !
ከሚወድህ ወንድምህ
አቡ ሰውዳህ ሀምዛ አስሰለፍይ
ባረከሏሁ ለከ ወባረከ አለይከ ወጀመአ በይነኩማ ፊ ኸይር ብያለሁ
#ደስታህ_ነው_ደስታችን_l!!
-------------------=--------------
አሏህ በፈቃዱ በኢስላም ላይ ፈጥሮን፡
በርሱ ላይ አፅንቶ ሐቅ ላይ አኑሮን፡
በውብ ሰገነት ላይ በምቾት አስፍሮን፡
ደብዳቤውን ልኮ በቃሉ አነጋግሮን፡
በማይላላ ገመድ በሱና አስተሳስሮን፡
በእምነት ወንድምነት አስውቦ አሳምሮን፡
በመንሀጀ ሰለፍ ነፃነት ለግሶን፡
በቁርአን ተአምር አንድ ህግ አቋድሶን፡
የነብዩ ጥሪ ለኔም ላንተም ደርሶን፡
ከጥመት አውጥቶ በሱናው አድሶን፡
ደስታህን ሰማሁኝ ዛሬ እዚህ አድርሶን፡
-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-
ደስታህን በአካል ባልካፈልህም፡
ሀሳቤ ካንተ ነው ወላሒ አልዋሽህም፡
የሰማሁኝ ጌዜ ብስራት የደስታህን፡
የሀላሉን ተግባር ቅዱስ ጋብቻህን፡
ተደሳሁኝ ባንተ ድጋሜ እንደገና፡
እንኳን ሀይ አደረክ የነብዩን ሱና፡
ሌሎች ሳይፈትኑህ ሳያውቅህ ብልግና፡
ቀጥታ ከዘመትክ ወደ ብልፅግና፡
እንኳን ተሳካልህ እሰይ የኔ ጀግና፡
#ልመርቅ_አሚን_በል፡
#ዱዐየን_ተቀበል__!!
--+-----------------------------
ምኞትህ ይሳካ ትዳር ይስመርልህ፡
ደስታን የሚያጣጥም ስኬት ይሁንልህ፡
ዱንያ ታገልግልህ ከሱና ሳትወጣ፡
ማሯ ይፍሰስብህ ሬት ሳታጠጣ፡
በእውነተኛ ፍቅር ትዳርህ ይወደስ፡
ሞደል ሁን ለሌሎች ወንድሜ ተቀደስ፡
ቤትህ ሰፊ ይሁን መቆለፍ የሌለው፡
ሚስኪን እየመጣ ይውሰድ በሚችለው፡
በደስታ ተሞላ ማንም ይውሰድብህ፡
ብቻ ምንም ይሁን ካንተ አይጉደልብህ፡
በረካ አላህ ይስጥህ በሐላል ገንዘብህ፡
በሁለቱም ሀገር ፊትና አይድረስብህ፡
#አሚንበል!!
ባለቤትህ ትሁን የተውሒድ አርበኛ፡
የቢዲአ ጠላት የሱና ዘበኛ፡
እንደዚህች ያለች ልጅ ኢማኗ የሞላ፡
ለአለሙ ጌታ የገባች መሀላ፡
አንተን ለማስደሰት የማታጣ መላ፡
ከአርሹ ባለቤት የተሰጠች ሲሳይ፡
እውነተኛ ፍቅሯን ላንተ የምታሳይ፡
ሰላም የሞላበት ይሁንልህ ንፁህ፡
ፍቅርና ፀባይ ተባብረው ያንፁህ፡
#አሚን_በል__!!
ይህንን ፀሎቴን በደስታ ተቀበል፡
እኔ ልመርቅህ አንተ ብቻ አሚን በል፡
በሁለቱም ሀገር ትሁን ባለቤትህ፡
ጀግና ልጆች ውለድ ከውድቷ ሚስትህ፡
ጊዜውን ጠብቆ ናፍቆት ሳያሳሳን፡
ምን ሆነብን እያልን ስጋት ሳያከሳን፡
በጥበብ ተሞልቶ ሆኖ ግሩም ልሳን፡
ደስታ ተሸክሞ ፈጥኖ ይምጣ ሀሳን፡
#አሚን_በል__!!
የነብር አለጋ እንደ አንበሳ ግልገል፡
ለተውሒድ ለሱና ሳትደክም ታገል፡
አንተም ባለቤትህ ሁኑልን አበባ፡
ጣፋጭ ፍሬም ሁኑ የሌለው ገለባ፡
የውደታችሁ ልክ የፍቅራችሁ ማማር፡
ሁሌም ጣፋጭ ሁኑ እንደ ወለላ ማር፡
#አሚን_በል__!!
#ለማንኛውም___!!
ማሻ አሏህ ብለናል ደስታህ ነው ደስታችን፡
-------------------------------------------------
መሀመድ ሰንዴው
እና ሀውለት
ጥምረት እስከ ............ጀነት !
ከሚወድህ ወንድምህ
አቡ ሰውዳህ ሀምዛ አስሰለፍይ