እግዚአብሔር ላስደስት ብሎ ያስከፋው ጸሎተኛ ሰው ታሪክ!
ከቤተሰቦቹ ስር መሠረት ጀምሮ እግዚአብሔርን አክባሪና አምላኪ ከሆነ ቤተሰብ የተገኘ አንድ በጣም ጸሎተኛ ሰው ነበረ
- ሁል ጊዜ ይጾማል
- ሁል ጊዜ ይሰግዳል
- ሁል ጊዜ ያስቀድሳል
- ሁል ጊዜ ቤተክርስቲያን ይሄዳል
- ሁል ጊዜ እንግዳ ይቀበላል (በሃይማኖት የሚመስሉትን)
ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን አንድ ሽማግሌ ከበሩ ላይ ቆሞ ከመንገድ ላይ እንደመሸበት እና ማደርያ እንዳጣ እናም ሰዎች እርሱ ያሳድርኻል ደግ ሰው ነው ብለው ወደርሱ ቤት እንደ ጠቆሙት ያስረዳዋል።
ይሄ ሃይማኖተኛ ሰውም እውነት ነው ቤት የእግዚአብሔር ነው እኔም እግዚአብሔር በፈቀደልኝ መጠን መልካም ሥራ እሰራለሁ ነገርግን የተወሰነ ጥያቄ እጠይቅሃለሁ አለው ።
መንገደኛውም ደክሞት ስለነበረ ላቡን በክንዱ ግንባሩን እየጠረገ ይችላሉ ጌታዬ ይጠይቁ እነሆ እመልሳለሁ በማለት ጎንበስ አለ።
ቀጥሎም ጸሎተኛው ሰው ሃይማኖትህ ምነው አለው...
መንገደኛው ሰውም እንግዳ ስሜት ተሰምቶት እእ... ሃይማኖት የለኝም አለ
ሃይማኖተኛው ሰውም ጠይቄውን ቀጥሎ ዕድሜህ ስንት ነው ሲለው 58 ዓመቴ ነው አለው ጸሎተኛው ሰውም አሰብ አድርጎ...
ይቅርታ በእግዚአብሔር የማያምን ሰው ወደ ቤቴ አይገባም ብሎ መለሰውና
ወደቤቱ ገብቶ ጸሎት ሲጀምር ጌታ ሆይ ዛሬ በቤቴ ለማደር አንድ ሃይማኖት አልባ ሰው ከቤቴ ደጃፍ መጥቶ እንዳሳድረው ቢጠይቀኝ አባረርኩት አንተን ከማያምን ሰው ጋር ከምተኛ ሞቴን እመርጣለሁ አለ።
እግዚአብሔርም
ይህ ሰው ዕድሜው ስንት ነው በማለት ለጸሎተኛው ሰው ጥያቄ አቀረበለት...
ሃይማኖተኛው ሰውም 58 ዕድሜው ነው እግዚአብሔር ሆይ ሲል ተናገረ እግዚአብሔርም መለሰ...
እኔ 58 ዓመት ሙሉ ሃይማኖት ሳይኖረው ያሻውን ሲከውን ሲበድል ሲያጠፋ እያየሁ በምህረት ይህን ሁሉ እድሜ ተሸክሜው ከኖርኩኝ አንተ እንደምን በጣም ጥቂት ለሆነች ሰዓት ያህል የእግዚአብሔርን እንግዳ "ከቤቴ ሂድ" በማለት አባረርህ ?!
በል አሁን በከተማው ከእንዲህ አይነት ዛፍ ስር ተኝቶ ታገኘዋለህና ሄደህ ከቤትህ አምጥተህ እግሩን አጥበህ ምግብ ሰጥተህ በክብር አሳድረህ ጠዋት ላይ ወደ ሚሄድበት ቦታ ሸኘው አለው።
ጸሎተኛው ሰውም እግዚአብሔርን አስደስታለሁ ብዬ አስከፋሁ እያለ በራሱ እያዘነ ፈጣሪ ያዘዘውን ከወነ እግዚአብሔርም ይቅርታን አደረገለት ።
መንገደኛውም በተደረገለት ነገር በጣም ተደንቆ ቅድም እንድሄድ ነግረኸኝ አሁን ግን ካለሁበት ፈልገኸኝ መጥተህ ስለምን እንዲህ ባለ እንክብካቤ አሳደርኸኝ ብሎ ቢጠይቀው የተደረገውን በሙሉ ሲነግረው ልቡ ተነክቶ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ተጠምቆ በክርስትና መኖር ጀመረ።
ከዚህ ታሪክ የምንረዳው ኢየሱስ ክርስቶስ የተራበን አብሉ ሲል ሌላ መስፈርት አላስቀመጠም
በእኔ ያመኑትን አብሉ
በእኔ ያመኑትን አጠጡ
በእኔ ያመኑትን የታሰሩትን ጠይቁ
በእኔ ያመኑትን የታረዙትን አልብሱ
በእኔ ያመኑትን የታመሙትን ጠይቁ
በእኔ ያመኑትን እንግዶች ተቀበሉ አላለም በአጠቃላይ በአምሳሌ የፈጠርኩትን ትእዛዜን ፈጽሙላቸው አለ እንጂ እኛም የምናደርገውን መልካም ስራ በዘር በእምነት ሳንለይ እናድርግ የዛኔ አሕዛቡ በአምላካችን ትእዛዝ ልቡ ተሰብሮ ወደ እግዚአብሔር መንገድ ይመለሳልና መልካሙን ነገር ከሰው ሰው ለይተን አንተግብር።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
✍🏾 መርጌታ ዘራብሩክ ጥላሁን
#በተለያዮ_ጉዳዮች_እኔን_ለማማከር_ለምትፈልጉ
0933464314
0933464314 ☎️
👉መድሀኒቱን ባሉበት እንልካለን ጥበብ ታላቆን ታከብራለች
መልእክቱን #ሼርር በማድረግ መፍትሔውን ሌላው ያድርሱ
#ከፈጣሪ በታች ችግሩን እንፈታዋለን
( ምንሰራው በሰለሞን ጥበብ )