ለባንጃ ወረዳ ግብርና ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ።
----
ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
ስልጠናው በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ሽግግርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እና በባንጃ ወረዳ
ግብርና ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት በመስኖ ውሃ አጠቃቀምና አያያዝ፣ ድህረ ምርት አሰባሰብ እና ቴክኖሎጂ፣ የመስኖ ስንዴ ክላስትር አደረጃጀት እንዲሁም የአፈር ጨዋማነት እና አሲዳማነት ዙሪያ ላይ አተኩሮ ለ2 ቀናት በእንጅባራ ከተማ ተሰጥቷል።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ ዲን ሀብታሙ አድማስ (ዶ/ር) ምርት እና ምርታማነትን
ለማሳደግ የግብርና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ስልጠናው የባለሙያዎችን አቅም እንደሚያሳድግ ተናግረዋል፡፡፡ ዶ/ር ሀብታሙ አያይዘውም በመስኖ መሬት የአፈር ጨዋማነትና አሲዳማነት ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሣደረ በመሆኑ ይህን በተመለከተ የመሬት አሲዳማነትን እንዴት መከላከልና ማከም እንደሚቻል ለግብርና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የእርሻ ስራዎች አስተባባሪ የሆኑት አማረ አለምነው(ዶ/ር) በበኩላቸው ወቅቱ የበጋ መስኖ የሚሰራበት ጊዜ በመሆኑ ባለሙያዎች የወሰዱትን ሰልጠና ተግባራዊ እንዲያደርጉና አስፈላጊ የሆኑ ሙያዊ ድጋፎችን ለማድረግም መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid033DDthscJsQW1ffeHeW4ST7A94EHgBMxnauuoVfZvU3xpKT3Cp8eMZ5W2Zm9JLEql/?app=fbl