የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የስድስት ወር የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሔደ።
ጥር 20/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወር የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የተቋሙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በተገኙበት ተገምግሟል።
ውይይቱን የመሩት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ( ዶ/ር) ሲሆኑ የአፈጻጸም ሪፖርቱ የዩኒቨርሲቲውን ቁልፍ የውጤት አመላካች አካቶ መዘጋጀቱ በጥንካሬ የሚነሳ ነው ብለዋል። ሁሉም የሥራ ክፍል በትኩረት በመያዝ የቁልፍ አመላካች(KPI) መሠረት በማድረግ የተግባራትን ሪፖርት ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ማድረግና ሰንዶ ማስቀመጥ እንደሚገባም አስረድተዋል። የሪፖርት ግምገማ መድረኩ የቀረበውን የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በጥንካሬና በድክመት ከመወያየት ባሻገር ሪፖርቱን ማበልፀግ በመሆኑ በሪፓርቱ መካተት የነበረባቸው ዋናዋና ጉዳዮችንና የሪፖርት መዋቅር ምን መምሰል እንዳለበት ለቀጣይ በሥራ ክፍሎች በኩል ተጠናክረው እንዲቀርቡ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ መ/ር ልንገረው አትንኩት ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርት ላይ ከተሳታፊዎች አስተያየትና ጥያቄ ተነስቶ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
በግምገማ መድረኩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና የካውንስል አባላት ተገኝተዋል።