የአጠቃላይ ዩኒቨርስቲዎች ማህበር ምሥረታ የመክፈቻ ጉባዔ በዛሬው እለት በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተጀመረ።
-------
የማህበሩ መክፈቻ ስነስርዓት ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የአጠቃላይ ዘርፍ ዩኒቨርሲቲዎች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ ያሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ባላቸው የትኩረት መስክ ልየታ (differentiation ) መሠረት በአራት ምድብ የተመደቡ ሲሆን ከምድቦች አንዱ የአጠቃላይ ዩኒቨርስቲዎች (comprhensi ve) ነው።
በዚህ ምድብ 21 ዩኒቨርስቲዎች የታቀፉ ሲሆን እንጅባራ ዩኒቨርሲቲም ከአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ሲሆን ዩኒቨርስቲዎች ከተሰጣቸው ተልዕኮ አንፃር በየጊዜው እየተገናኙ በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመምከር እና ሀሳብ ለመለዋወጥ በዛሬው ዕለት በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማህበሩን በይፋ መስርተዋል።
በዚህ ምስረታ እንጅባራ፣ መደወላቡ፣ መቱ፣ ጋምቤላ፣ ራያ፣ ደብረ ታቦር ፣ ቦረና ፣ ዋቻሞ ፣ ሚዛን ቴፒ ፣ ቡሌ ሆራ፣ ጅንካ፣ ሰላሌ፣ ወራቤ፣ ደምቢ ዶሎ ፣ ደባርቅ ፣ ቦንጋ ፣ አዲግራት ፣ መቅደላ አምባ ፣ ወልድያ የማህበሩ አባል ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ምስረታ የአስተዳደርና ልማት ም/ ፕሬዚዳንት የሆኑት ወሀቤ ብርሃን ( ዶ/ር ) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን በመወከል እየተሳተፉ ይገኛሉ።
መጋቢት 1/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ