INSA - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር - INSA


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


Official INSA Telegram Channel
በእዚህ የቴሌግራም ቻናል የሳይበርና የኢንፎርሜሽን መረጃዎች፤ የስራና ጨረታ ማስታወቂያዎች ያገኛሉ፡፡
ይከተሉን/Join Us On:
YouTube: https://www.youtube.com/@cyberigna1003/fe
Facebook: https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
Twitter ፡ https://x.com/INSAEthio

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


የሀገር የደም ስር የሆነው የትራንስፖርት ዘርፍ እና የሳይበር ደህንነት ዝግጁነት
 
የትራንስፖርት ዘርፍ የህዝብንና የሸቀጦችን እንቅስቃሴ በማሳለጥ የሀገርን ኢኮኖሚ ህያው የሚያደርግ ዋና የደም ስር በመሆኑ፣ በከፍተኛ ደረጃ ለሳይበር ጥቃት ከተጋለጡ 12ቱ የቁልፍ መሠረተ ልማት (Critical Infrastructure) ዘርፎች መካከል አንዱ ነው።
 
በአዲሱ የቁልፍ መሠረተ ልማት የሳይበር ደህንነት አዋጅ ቁጥር 1426/2018 መሠረት በዘርፉ የሚገኙ ተቋማት (አቪዬሽን፣ ምድር ባቡር፣ የባህርና ወደብ፣ የየብስ ትራንስፖርትና የሎጅስቲክስ ወ.ዘ.ተ ተቋማት) ህጋዊ ግዴታቸውን ተረድተው ወደ ሙሉ ትግበራ ከመገበታቸው በፊት በቂ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
 
ዓለም አቀፍ እውነታዎች እና በዘርፉ የተደቀኑ የሳይበር ሥጋቶች ምን ይመስላሉ?
በዲጂታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት ምክንያት በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶች ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የ48% እድገት አሳይተዋል። ዘርፉን ለጥቃት ተጋላጭ የሚያደርጉት በከፍተኛ ሁኔታ አውቶሜት የተደረጉ የቁጥጥር ሲስተሞች (Traffic Management & Signaling Systems)፣ የአየር መንገድና የባቡር ትኬት መቁረጫ፣ የራዳርና የትራፊክ መከታተያዎች፣ የወደብ ኮንቴይነር ማኔጅመንት እና የሎጅስቲክስ ኔትወርኮች ወ.ዘ.ተ የሚጠቀሱ ናቸው።
 
በዘርፉ በስፋት የሚቃጡ የጥቃት አይነቶች፡-
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


ጉግል ለሳይበር ደህንነት ጥበቃ የላቀ አስተዋጽኦ የሚያበረክት “ጄሚናይ 4 አርጎን” የተባለ የኤአይ/AI ሞዴልን ይፋ አደረገ

ጉግል የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን ደህንነት ለማጠናከር እና ጥቃቶችን በቅድሚያ ለመግታት የሚያስችል “ጄሚናይ 4 አርጎን” (Gemini 4 Argon) የተሰኘ አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴል ይፋ አደረገ። ሞዴሉ በተለይም ለተከላካይ የሳይበር ደህንነት (Defensive Cybersecurity) ስራዎች ተስፋ ሰጪ አቅም ይዞ የቀረበ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ውጤት በሶፍትዌሮች እና በስርዓቶች ላይ የሚታዩ ወሳኝ የደህንነት ክፍተቶችን በራሱ የመለየት፣ የማረጋገጥ እና ወዲያውኑ የመጠገን ከፍተኛ አቅም አለው። ይህም ተቋማት ሊሰነዘሩባቸው የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን ቅድመ-መከላከል እንዲችሉ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

“ጄሚናይ 4 አርጎን” ከሳይበር ደህንነት ተከላካይነቱ ባሻገር፣ ውስብስብ የኮዲንግ እና የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ስራዎችን ማከናወን የሚችል እና፤ ረጅም ቪዲዮዎችን፣ ምስሎችን እና ዳታዎችን በጥልቀት የመተንተን አቅም እንዳለዉ ተገልጿል።


የብሔራዊ ደህንነት አዲሱ ግንባር - የጸጥታና ደህንነት ዘርፍ እና የሳይበር ደህንነት ዝግጁነት
 
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሀገራችንን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችለውን የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ ቁጥር 1426/2018 በሐምሌ 2018 ዓ.ም ማውጣቱ ይታወቃል። አዋጁ የሀገር ህልውና እና ብሔራዊ ደህንነትን የሚያረጋግጡ 12 ዋና ዋና ዘርፎችን በቁልፍ መሰረተ ልማትነት የለየ ሲሆን፣ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወደ ሕግ ትግበራ ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት የቅድመ ዝግጅት ጊዜ (Grace Period) ተሰጥቷቸዋል።
 
በዛሬው ሦስተኛ ጽሁፋችን የሀገርን ሰላምና ሉዓላዊነት የሚያስከብሩ የፖሊስ፣ የደህንነት፣ የድንበር ጥበቃ እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ተቋማት የሚገኙበትን “የጸጥታና ደህንነት” ዘርፍ ዝግጁነት እንመለከታለን።
 
በዓለም አቀፍ ደረጃ በጸጥታ፣ መከላከያ እና የመንግስት ደህንነት ተቋማት ላይ በየቀኑ ከአስር ሺዎች በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች ይደረጋሉ። በዘርፉ በስፋት የሚታዩት የሳይበር ጥቃት አይነቶች፤ የመንግስት ሚስጥሮችን የመስረቅ (Cyber Espionage)፣ የኔትወርክ አገልግሎት ማቋረጥ (DDoS)፣ የመረጃ ማገቻ (Ransomware) እና የመቆጣጠሪያ ሲስተሞችን የመጥለፍ ጥቃቶች ናቸው።
 
በዘርፉ የደረሱ የሚጠቀሱ ዓለም አቀፍ ጥቃቶች
የአልባኒያ የፖሊስና ድንበር ቁጥጥር ስርአት ጥቃት (እ.ኤ.አ. 2022)፦ በሀገሪቱ የፖሊስ፣ የምዝገባና የድንበር ቁጥጥር (TIMS) ዳታቤዝ ላይ በተፈጸመ የሳይበር ጥቃት የድንበር ኬላዎች ስራ አቁመው የነበረ ሲሆን ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ደቅኖ ነበር።
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
🎬 ታላቅ የአጭር ፊልም ውድድር! 🏆

​ጥበብዎን ለሀገር ደኅንነት ያውሉ፤ ማህበረሰባችንን ከሳይበር ጥቃት ይታደጉ! 🛡

​በ7ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደኅንነት ወር ምክንያት በተዘጋጀው ልዩ የአጭር ፊልም ውድድር ላይ በመሳተፍ ድንቅ የፈጠራ ችሎታዎን ያሳዩ! ጥበብን መሣሪያ በማድረግ የሳይበር ጥቃትን የሚከላከል እና ሀገራዊ ግንዛቤ የሚፈጥር አጭር ፊልም በማዘጋጀት የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያበርክቱ።

​🌟 ለምን ይሳተፋሉ?
​
· የፊልም ስራ ችሎታዎን ለሰፊው ተመልካች ለማሳየት፣
·  ማህበረሰቡን ከሳይበር አደጋዎች የሚታደግ ትርጉም ያለው ሀገራዊ መልእክት ለማስተላለፍ፣
·  እንዲሁም ለአሸናፊዎች የተዘጋጁትን ማራኪ የገንዘብ ሽልማቶች 💰 ለማሸነፍ!

​የፈጠራ ክህሎትዎን ተጠቅመው ሀገርዎን ይጠብቁ፤ ተወዳድረው ያሸንፉ!
#7NationalCyberSecurityMonth #INSA


300 እጥፍ የጥቃት ሥጋት፤ የ1 ዓመት የጊዜ ገደብ እና አዲሱ "የፋይናንስ ዘርፍ የሳይበር ደህንነት ፎረም” - የፋይናንስ ተቋሞቻችን ለአዋጅ ቁጥር 1426/2018 ትግበራ ምን ያህል ዝግጁ ናቸው?
 
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሀገራችንን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ያወጣው የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት አዋጅ ቁጥር 1426/2018 በሐምሌ 2018 ዓ.ም. በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ መውጣቱ ይታወቃል። አዋጁ በሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ሚና ያላቸውን 12 ዋና ዋና ዘርፎች በቁልፍ መሠረተ ልማትነት የለየ ሲሆን፣ የሀገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው የፋይናንስ ዘርፍ (ባንኮች፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች፣ የክፍያ ሲስተም ኦፕሬተሮች፣ ማይክሮፋይናንሶች ወ.ዘ.ተ) የቀዳሚነት ስፍራውን ይይዛል።
 
ትላንትና (መስከረም 19/2019 ዓ/ም) በብሔራዊ ባንክ አዘጋጅነት በተካሄደው 2ኛው የፋይናንስ ፎረም ላይ "የፋይናንስ ዘርፍ የሳይበር ደህንነት ፎረም" በይፋ መመስረቱ ይታወሳል። ይህ የፎረም ምሥረታ በአዋጅ ቁጥር 1426/2018 አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 1(ረ) ላይ ኢመደአ በቁልፍ መሠረተ ልማቶች ደህንነትና አይበገሬነትን ለመፍጠር ሀገራዊና ዘርፍ-ተኮር የሳይበር ደህንነት ፎረሞችን እንደሚያቋቁምና እንደሚያስተዳድር የተቀመጠውን ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በተግባር ማረጋገጫ ነው።
 
በዘርፉ የተደቀኑ ዓለም አቀፍ የሳይበር ሥጋቶች፣ የጥቃት ዓይነቶች እና ታሪካዊ ክስተቶች ምን ይመስላሉ?
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


የፋይናንስ ዘርፍ የሳይበር ደህንነት ፎረም በይፋ ተመሰረተ
 
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 ዓ/ም:- በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው በኢትዮጵያ የፋይናንስ ፎረም (Ethiopian Finance Forum 2026) ላይ ይፋ የተደረገው ይህ ፎረም፤ የሀገራችን ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እና የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ መሰረት የሆነውን የፋይናንስ ዘርፍ ከሳይበር ጥቃት የመጠበቅ እና አይበገሬ የዲጂታል ፋይናንስ ሥነ-ምህዳር  የመፍጠር ዓላማ ያለው ነው።
 
የፎረሙን መመስረት አስመልክቶ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ክቡር ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡  
 
ፎረሙ ባለፈው ሰኔ 2018 ዓ.ም የጸደቀውን የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅን መሠረት በማድረግ፤ በዘርፉ የሳይበር ደህንነት እርምጃዎችን በመከታተል ክፍተቶችንና የአሠራር ማነቆዎችን የሚፈታ ፎረም እንደሆነ ተገልጿል፡፡
 
በምስረታው መርሃ ግብር ላይ ማብራሪያ ያደረጉት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፤ ፎረሙ በሀገራችን የፋይናንስ ዘርፍ ላይ የሳይበር ጥቃቶች ሲደርሱ መረጃ የምንለዋወጥባእትና ሊደርሱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን በጋራ የምንከላከልበት ነው ብለዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም፤
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


የሳምንቱ የሳይበር ደህንነት መረጃዎች (ከመስከረም 11 እስከ መስከረም 17/2018 ዓ.ም)
 
ውድ የገጻችን ተከታታዮች፣ ዘወትር ሰኞ ወደ እናንተ የምናደርሰው “ሳምንቱ በሳይበር” የተሰኘው የሳይበር ደህንነት ዳሰሳችን እነሆ ብለናል። በዛሬው ዳሰሳችን ከመስከረም 11 እስከ መስከረም 17/2019 ዓ.ም. ድረስ በዲጂታሉ ዓለም የተመዘገቡ አበይት ዜናዎችን፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ስጋቶችን፣ በአህጉራችን የተከሰቱ ወቅታዊ ክስተቶችን እና የመፍትሔ ሃሳቦችን አካተን እንደሚከተለው አቅርበናል።
 
1. ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት መረጃ
የብሔራዊ ቁልፍ መሠረተ ልማት ማዕቀፍ ሽግግር፡- በቅርቡ የጸደቀውን የቁልፍ መሠረተ ልማት የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 1426/2018 ተከትሎ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር  የተለዩትን 12 ቁልፍ የመሰረተ ልማት ዘርፎች ለአዲሱ አሰራር ዝግጁ የማድረግ ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚሁም መሰረት ተቋማቱ ህጉ በሚፈቅደው የአንድ ዓመት የሽግግር ጊዜ ውስጥ የተረጋገጠ የሳይበር ደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከል (SOC) ለመገንባት እና ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ስርዓት ለመዘርጋት የተጣሉባቸውን ግዴታዎች በመገምገምና ወደ ተግባር በመግባት ላይ ይገኛሉ።
 
2. አህጉራዊ የሳይበር ደህንነት መረጃ
· የተባበሩት መንግስታት ስብሰባ እና የሳይበር ደህንነት፡- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይም በላይቤሪያ መሪነት፣ የአፍሪካ ሀገራት በ-AI የሚመሩ የሳይበር ስጋቶች በቀጥታ ከግጭት መከላከል እና ከቀጣናዊ ሰላም ጋር እንደሚገናኙ በማሳሰብ ዓለም አቀፍ የቁጥጥር ማዕቀፎች እንዲተገበሩ ጠይቀዋል።
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


48 ሰዓት፣ 1 ዓመት፣ 2 ሚሊዮን ብር - የአይሲቲ ዘርፍ ተቋማት ሊያውቋቸው የሚገቡ አራቱ የሕግና የቴክኒክ ቁጥሮች
 
በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት አዋጅ ቁጥር 1426/2018 የሀገራችንን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማስከበር የተጣለ አዲስ ስትራቴጂካዊ መሠረት ነው።
የአይሲቲ እና የኮሙኒኬሽን ዘርፍ (የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪዎች፣ የዳታ ማዕከላት እና የደመና/Cloud አገልግሎት አቅራቢዎች ወ.ዘ.ተ) የሌሎች መሠረተ ልማቶች ሁሉ ዲጂታል የጀርባ አጥንት በመሆናቸው ለሳይበር ጥቃት ያላቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ ነው።
 
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየቀኑ ከ44,000 በላይ የDDoS ጥቃቶች በዚሁ ዘርፍ ላይ ይሰነዘራሉ። ከዘርፉ እርስ በርስ መተሰሳር፣ ውስብስብነት እና ከፍተኛ መረጃን የማስተናገድ ልዩ ባሕሪ አኳያ፣ በስፋት የሚሰነዘሩት ዋነኛ የጥቃት ዓይነቶች፤ አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ የሚያቋርጡ ግዙፍ የDDoS (Hyper-Volumetric DDoS) ጥቃቶች፣ የሶስተኛ ወገን ክፍተትን የሚጠቀሙ የአቅርቦት ሰንሰለት (Supply Chain) ጥቃቶች፣ የኢንተርኔት ትራፊክ መጥለፍ (BGP እና DNS Hijacking) ፣ እንዲሁም ራንሰምዌር እና በክላውድ/API ማከማቻዎች ላይ የሚፈጸሙ የመረጃ ስርቆቶች ናቸው።
 
እነዚህን ሥጋቶች በተግባር የሚያሳዩ እና በዘርፉ ከፍተኛ ውድመት ያስከተሉ ታሪካዊ ጥቃቶች በቅርብ ዓመታት ተስተውለዋል፤ ከእነዚህም መካከል እ.ኤ.አ. በ2024 የተጋለጠውና ከ109 ሚሊዮን በላይ የAT&T (አሜሪካ) ደንበኞችን መረጃ የሰረቀው የክላውድ ጥቃት፤ እ.ኤ.አ. በ2023 የ24 ሚሊዮን የዩክሬን Kyivstar ቴሌኮም ደንበኞችን ስልክና ኢንተርኔት ያቋረጠው ጥቃት፤ እንዲሁም
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/I


የሚኒስትሮች ምክር ቤት የብሔራዊ ዳታ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 59ኛ መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ የዳታ አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ላይ በሰፊው ተወያይቶ እና ግብአቶችን በማከል ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግቦችን ለማሳካት፣ የዳታ ደህንነትንና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ፣ የዳታ መጋራትን፣ የዳታ ተናባቢነትንና የዳታ መልሶ አጠቃቀምን በማጠናከር የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማዘመን፣ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምርና የፈጠራ አቅምን ለማጎልበት፣ የኢኖቬሽንና የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን እና በዳታ የተመራ የኢኮኖሚ ልማት ሥርዓት ለመገንባት እንዲያስችል ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቁ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
• ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et
• ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
• ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/@insa_et?_t=8qBKkyp092r&_r=1
• ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/@cyberigna1003/featured
• ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet
• ትዊተር (X) ፦ https://twitter.com/INSAEthio
• ሊንክድኢን:- https://www.linkedin.com/.../information-network.../
• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት፡- ነጻ የስልክ መስመር 933


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለአስተዳደሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ለመላው ህዝበ ክርስቲያን እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን በመግለጽ ፤ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ እና የአብሮነት እንዲሆን ይመኛል፡፡


የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ እና የተቋማት ዝግጁነት ምን ይመስላል?
 
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሀገራችንን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ እና የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን ከሳይበር ጥቃት ለመጠበቅ የሚያስችለውን የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት አዋጅ ቁጥር 1426/2018 ማውጣቱ ይታወቃል።
ይህ አዋጅ በሀገራችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ሚና ያላቸውንና የጥቃት ሰለባ ቢሆኑ በሀገር ህልውና፣ በብሔራዊ ደህንነት እንዲሁም በሰላምና መረጋጋት ላይ ከባድ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ 12 ዋና ዋና ዘርፎችን በቁልፍ መሰረተ ልማትነት ለይቷል።
እነዚህም የተለዩት ዘርፎች፦ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ኮሙኒኬሽን፤ የፋይናንስ፤ የፀጥታና ደህንነት፤ የትራንስፖርት፤ የትምህርት፤ የጤና፤ የውሃና ኢነርጂ፤ የመንግሥት አገልግሎቶች፤ የአደጋ መከላከል አገልግሎቶች፤ ግብርና፤ ንግድ፤ እና ኢንዱስትሪ ናቸው።
 
አዋጁ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የ1 ዓመት የቅድመ ዝግጅት ጊዜ (Grace Period) የተሰጠ በመሆኑ፣ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወደ ሕግ ትግበራ ከመገባቱ በፊት በቂ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በመሆኑም በእያንዳንዱ የቁልፍ መሰረተ ልማት ዘርፍ ላይ ያተኮረ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሁፎችን በገጻችን ማቅረብ እንጀምራለን።
 
በእነዚህ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሁፎች ውስጥ የምንዳስሳቸው ጉዳዮች፦
🔹 የዘርፎቹ ልዩ የሳይበር ባህሪና ተጋላጭነት፦ እያንዳንዱ ዘርፍ ያለው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የተሳሰሩ የኔትወርክ መዋቅሮች እና የሚጋረጡበት ልዩ የሳይበር ስጋቶች፤
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


የትምህርት ተቋሞቻችን ከሳይበር ጥቃት ምን ያህል የተጠበቁ ናቸው?
 
የትምህርት እና የምርምር ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጋለጡት የሥራ ዘርፎች መካከል አንዱ ነው። በቅርቡ የወጣው የ "Check Point" የ2025 ጥናት እንደሚያሳየው፣ የትምህርት ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሳምንት በአማካይ 4,356 የሳይበር ጥቃቶችን ያስተናግዳሉ።
 
ለመሆኑ ትምህርት ቤቶች ለምን የጥቃት ዒላማ ይሆናሉ?
የትምህርት ተቋማት፣ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ሰፊና ክፍት የሆኑ የዲጂታል መረቦችን (networks) መጠቀማቸው፣ እንዲሁም ለሳይበር ደህንነት የሚመድቡት በጀት አነስተኛ መሆን ለጥቃት ተጋላጭ አድርጓቸዋል።
 
የጥቃቱ ስፋት ሲታይ
በመደበኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፡ የትምህርት ቤቶች አገልግሎት መቋረጥ ሊያጋጥም የሚችል ሲሆን፤ የተማሪዎች ውጤት፣ የጤና መረጃዎች፣ እንዲሁም የመምህራን ግላዊ መረጃዎች የጥቃት ኢላማ ይሆናሉ።
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፡ ፕሮፌሰሮችና ተመራማሪዎች ለዓመታት የደከሙባቸው አእምሯዊ ንብረቶች (Intellectual Property) እና ወሳኝ የጥናትና ምርምር መረጃዎች የመሰረቅ ከፍተኛ ስጋት ይደቀንባቸዋል።
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


የሀገራት የመረጃ ልውውጥ ወሳኝነት - ለሳይበር ደህንነት
 
የአውሮፓ ኦዲተሮች ፍርድ ቤት (The European ‌Court of Auditors - ECA) ባሳለፍነው ሰኞ እንዳስታወቀው፤ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በሳይበር ጥቃቶች ዙሪያ በቂ መረጃ አለመለዋወጣቸው የህብረቱን የሳይበር ደህንነት የጋራ መከላከያ ጥረቶች እያዳከመው ይገኛል።
 
27ቱ የአውሮፓ ህብረት ሀገራት ስብስብ ለሳይበር ደህንነት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በተያዘው የፈረንጆቹ 2026 በጀት አመት 1.4 ቢሊዮን ዩሮ (1.61 ቢሊዮን ዶላር) የመደበ ሲሆን፣ ትብብርን ለማሻሻል ጥረት እያደረገ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ውጤታማ መሆን እንዳልቻለ ገልጿል። የሪፖርቱ አዘጋጆች "ደካማ የመረጃ ልውውጥ የመላው የደህንነት ስርዓቱ ዋነኛ ደካማ ጎን (Achilles heel) ሆኗል" ብለዋል።
 
አደገኛ የሳይበር ጥቃት በሚያጋጥምበት ጊዜ ፈጣን እና ተግባራዊ ሊደረግ የሚችል መረጃ መለዋወጥ ወሳኝ ነው፤ ይህ ካልሆነ ኔትወርኮች እና የደህንነት ስርዓቶች እሴታቸውን ያጣሉ ሲል ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል። ለአብነትም በመስከረም 2025 በለንደን፣ ብራስልስ፣ በርሊን እና ደብሊን አውሮፕላን ማረፊያዎች ላይ የተፈጠረውን የራንሰምዌር (Ransomware) ጥቃት ጠቅሶ፣ የትኛውም ጥቃቱ የደረሰበት ሀገር ለአውሮፓ የሳይበር ደህንነት ኤጀንሲ ሪፖርት አለማድረጉን ገልጿል።
 
ባለፈው ሐምሌ ወር፣ የአውሮፓ ኮሚሽን የሳይበር ደህንነት መረጃ ልውውጥን በተመለከተ የህብረቱን ህጎች ከራሳቸው ብሄራዊ ህግ ጋር ባለማጣጣማቸው ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኔዘርላንድስ እና ስፔንን በአውሮፓ ህብረት የፍትህ ፍርድ ቤት መክሰሱ ይታወሳል።
 
🌍 የአፍሪካ ሀገራት ከዚህ ምን ይማራሉ?
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


ከክፍል ውስጥ እስከ ሳይበር ምህዳር፡ የዘመኑ መምህር የዲጂታል ክህሎት እና የሳይበር ደህንነት
 
🎓 ለመላው የሀገራችን አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም የኮሌጅ እና ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሙሉ፤ እንኳን ለአዲሱ የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!
 
አዲሱን የትምህርት ዘመን ሲጀምሩ የዲጂታል ክህሎትዎን ማሳደግ እና የሳይበር ደህንነትዎን (Cyber Hygiene) መጠበቅ የዕቅድዎ ዋነኛ አካል ሊሆን ይገባል፡፡ አሁን ባለንበት የዲጂታል ሽግግር እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዘመን፣ ቴክኖሎጂን ከማስተማር ስራ ጋር ማስተሳሰር ጊዜን ለመቆጠብ፣ ተማሪዎችን በንቃት ለማሳተፍ እና ትምህርትን ይበልጥ ማራኪ ለማድረግ እጅግ ወሳኝ ነው፡፡
 
ይሁንና ኢንተርኔት ለትምህርት የሚያስገኘው ጥቅም የጎላ እንደሆነ ሁሉ፣ ተቋማዊ እና የግል መረጃዎችን ለሳይበር ጥቃት የመጋለጥ እድልንም ይዞ ይመጣል። ስለዚህ ስኬታማ፣ ዲጂታል ክህሎት ያለው እና የሳይበር ደህንነቱ የተጠበቀ መምህር ለመሆን ምን ማድረግ አለብዎት?
 
📌 የኤአይ (AI) ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም፦ የ AI መሳሪያዎችን በመጠቀም የወረቀት ስራዎችን ማቃለል እና የትምህርት አሰጣጡን ማዘመን ይችላሉ። ነገር ግን ተማሪዎች በራሳቸው የማሰብ አቅማቸውን እንዳይዘነጉ ቴክኖሎጂውን በሃላፊነት እንዲጠቀሙበት አቅጣጫ ማሳየት እና መምራት ይገባዎታል።
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


የሳምንቱ የሳይበር ደህንነት መረጃዎች (ከመስከረም 4 እስከ 10/2019 ዓ.ም)
 
ሰላም!
በየሳምንቱ ሰኞ ይዘንላችሁ የምንቀርበውን “ሳምንቱ በሳይበር” ሳምንታዊ የሳይበር ደህንነት መረጃዎች፤ በዲጂታሉ ዓለም የተመዘገቡ አበይት ዜናዎችን፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ስጋቶችን እና የመፍትሔ ሃሳቦችን እንዲሁም ሳምንታዊ የመጽሐፍ እና ዘጋቢ ፊልም ጥቆማ አካተን እነሆ ብለናል::
 
1.    ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት መረጃ
የቁልፍ መሠረተ ልማት ተቋማት የ1 ዓመት የዝግጅት ጊዜ መቆጠር ጀምሯል—አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቁ!
በቅርቡ በነጋሪት ጋዜጣ የታወጀውን የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አዋጅ (ቁጥር 1426/2018) ተከትሎ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አዋጁን ወደ ሙሉ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል። በአዋጁ መሠረት የተለዩ 12 የቁልፍ መሰረተ ልማት ዘርፎች (የፋይናንስ፣ የቴሌኮም፣ የጤና፣ የትራንስፖርት፣ የኃይል አቅርቦት እና ሌሎችም) ውስጥ የሚመደቡ የቁልፍ መሠረተ ልማት ባለቤቶችና ኦፕሬተሮች አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የ1 ዓመት የዝግጅት ጊዜ ተሰጥቷቸዋል። ይህ የተሰጠው የ1 ዓመት ጊዜ ተቋማት በአዋጁ ላይ የተዘረዘሩትን 18 ዋና ዋና የሳይበር ደህንነት ግዴታዎች ለማሟላት የሚዘጋጁበት ወሳኝ ምዕራፍ ነው።በመሆኑም ሁሉም የቁልፍ መሠረተ ልማት ተቋማት ይህ የጊዜ ገደብ ከማብቃቱ በፊት የውስጥ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲዎቻቸውን እንዲቀርጹ፣ የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ አቅማቸውን እንዲገነቡ፣ እንዲሁም አስተዳደራችን ከሚያደርገው የደህንነት ኦዲትና ክትትል ጋር ራሳቸውን እንዲያጣጥሙ ጥሪ እናስተላልፋለን።
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


ተቋምዎ የሲስኮ (Cisco) ሲስተምን ይጠቀማል? እንግዲያውስ ይህ የሳይበር ደህንነት መረጃ እርስዎን ይመለከታል!
 
የሲስኮ (Cisco) ኩባንያ በ “Cisco Identity Services Engine (ISE)” ምርቱ ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ እና ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል የደህንነት ክፍተት (Vulnerability) መገኘቱን አስታውቋል።
 
ይህ የደህንነት ክፍተት (CVE-2026-76460) በቴክኖሎጂው አለም ከፍተኛው የሆነውን (CVSS 10.0) ደረጃ የተሰጠው ነው። የሳይበር ጥቃት አድራሾች ምንም አይነት የይለፍ ቃል ወይም ህጋዊ ፈቃድ ሳያስፈልጋቸው የተበላሸውን የ “API endpoint” ክፍተት በመጠቀም ወደ ተቋማት ሲስተም ሰብረው በመግባት ሙሉ ቁጥጥር (Root Privilege) እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። የሲስኮ ISE ሲስተም በተቋማት ውስጥ የኔትወርክ (Wired, Wireless እና VPN) መዳረሻዎችን የሚቆጣጠር ማዕከላዊ የደህንነት መድረክ በመሆኑ ክፍተቱ አደጋውን የከፋ ያደርገዋል።
 
ተቋማት ምን ማድረግ አለባቸው?
ሶፍትዌሩን ማዘመን (Update)፡ ሲስኮ ለችግሩ መፍትሄ የሚሆን የሶፍትዌር ማሻሻያ አውጥቷል። በመሆኑም 'Cisco ISE' እና 'Cisco ISE-PIC' የምትጠቀሙ ተቋማት ያለምንም መዘግየት ሲስተማችሁን አፕዴት (Update) እንድታደርጉ ይመከራል።
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


አዳዲስ የሳይበር ታለንቶችን ፍለጋ በጅማ… 🔍💻
 
ወጣቶች ያላቸውን የቴክኖሎጂ ፍላጎት፣ እውቀት እና ልዩ ተሰጥኦ ለማሳደግ ብዙ ርቀቶችን ቢሄዱም ህልማቸውን እውን ማድረግ ቀላል አልነበረም፡፡
በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA "ኢትዮ ሳይበር ታለንት" የተለኮሰው የእውቀት ፋኖስ አድማሱን በማስፋት፣ በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሰመር ካምፕ ፕሮግራሙን አንድ ብሎ ካስጀመረበት 2013 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች ማስተማር እና ማብቃት ችሏል፡፡
ይህንን ወርቃማ እድል ተሰጥኦ ላላቸው ወጣቶች በሙሉ ከደጃፋቸው ለማድረስ ፕሮግራሙ በ 2018 ዓ/ም በሀገራችን በሚገኙ 6 ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄደ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ጅማ ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነበር፡፡
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደውን የ5ኛውን ዙር የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ስልጠና፣ የተማሪዎቹን የውድድር መንፈስ እና የቆይታ ሁኔታ "ሳይበርኛ" የቴሌቪዥን ፕሮግራም በልዩ ዝግጅት ዳስሶታል።
👇 ሙሉ ፕሮግራሙን ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ፡ 🔗 https://youtu.be/U6a1u4I0Y4E?si=Kv0356M63ORaCLKr
#INSA #EthioCyberTalent #Cyberigna #JimmaUniversity #CyberSecurity #DigitalEthiopia2030


አሁን ያለው ዝግጅታችን በቂ አይደለም! — ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ለአስቸኳይ የሳይበር መከላከል ጥሪ አቀረቡ
 
በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የሆኑ የቴክኖሎጂ ተቋማት የሳይበር ጥቃቶችን፤ በተለይም ደግሞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዙ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት የተቀናጀና የጋራ የሳይበር መከላከል እርምጃ (Defensive Surge) መወሰድ እንዳለበት አሳሰቡ።
 
ማይክሮሶፍት (Microsoft)፣ ኦፕንኤአይ (OpenAI)፣ አልፋቤት (Alphabet)፣ አንትሮፒክ (Anthropic) እና አማዞን (Amazon) ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማት በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተፈጸሙ የሚገኙ የሳይበር ጥቃቶች ስፋትና ረቂቅነት እየጨመረ እንደሚሄድ በማስጠንቀቅ ጥቃቶቹን በጋራ ለመመከት የሚያስችሉ ሦስት ምክረ ሃሳቦችን አቅርበዋል፦
አሁን ያለው አደረጃጀትና ዝግጅት በቂ አለመሆኑን መገንዘብ፦ ነባሩ የደህንነት አሰራር እየተወሳሰቡ የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት በቂ አለመሆኑን አምኖ መቀበል።
የመከላከል አቅምን በ-AI ቴክኖሎጂ ማብቃት፦ የሳይበር ደህንነት ጠባቂዎችንና ተቋማትን በዘመናዊ የ-AI የመከላከል አቅም ማስታጠቅ።
የተቀናጀና የጋራ ምላሽ መስጠት፦ በሁሉም እርከኖች የተቀናጀ የመከላከል ምላሽ መፍጠር።
 
ኩባንያዎቹ ወደፊት ሊወሰዱ ይገባል ያሏቸውን 4 ዋና ዋና እርምጃዎችም ጠቁመዋል፦
ተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA


በአዲስ መንፈስ ወደ ትምህርት ቤት፡ የዲጂታል ዘመን ተማሪዎች ማወቅ ያለባቸው 5 የሳይበር ጥንቃቄዎች
 
ለውድ የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣት ተማሪዎች፤ እንኳን ለ2019 የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ!
 አዲሱ ዓመት አዲስ እቅድ የምናወጣበት፣ አሮጌ ልማዶቻችንን ትተን በታደሰ መንፈስ ወደ ትምህርታችን የምንመለስበት ውብ ወቅት ነው። ዛሬ ትምህርታችን ከቴክኖሎጂ እና ከኢንተርኔት ጋር እጅግ የተቆራኘ ነው። የትምህርት መረጃዎችን ለማግኘት፣ የምርምር ስራዎችን ለመስራት እና አዳዲስ ክህሎቶችን ለመቅሰም ኢንተርኔት የማይተካ ሚና አለው። ይሁን እንጂ የዲጂታል ዓለም ከጥቅሙ ጎን ለጎን የተለያዩ የሳይበር አደጋዎችን ይዞ እንደሚመጣ ልብ ማለት ይገባል።
 
በሀገራችን የኢንተርኔት ተደራሽነት እየሰፋ በሄደ ቁጥር፣ ህጻናት እና ወጣቶች (ተማሪዎች) የሳይበር አጥቂዎች ቀዳሚ ዒላማ እየሆኑ መጥተዋል። ስለዚህ የ2019 የትምህርት ዓመት ስንጀምር የሚከተሉትን የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል ንቃት እቅዶች በማውጣት ራሳችንን እንጠብቅ፡
 
ኢንተርኔትን ለዕውቀት ብቻ ተጠቀሙ: አዲሱን ዓመት ዲጂታል አሻራችንን ለትምህርት ብቻ እንድናውለው እናቅድ። ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለጥናት እና ለአእምሮ ማበልጸጊያ እንጂ ትምህርታችንን እንዲያዘናጋን አንፍቀድ።
ተጨማሪተጨማሪውን ለማንበብ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.