🔴 አዛውንቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ 2000 ፓውንድ የሚመዝን ቦምብ ለወራሪዋ እስራኤል ለመላክ አሜሪካ ዝግጁ መሆኗንና ቀጣይ ሳምንት ጉዞ ወንደሚጀምር ተናግሯል።
"ቦምቦች ወደ እስራኤል እንዳይላኩ በባይደን የተጣለውን እገዳ እንዲያነሳ አዝዣለሁ። በባይደን ዘመን ክፍያ የተፈፀመባቸው የመሳርያ ግዥ ውሎች ሁሉ ተፈፃሚ ይሆናሉ" ብሏል።
አክሎም
"ፍልስጤማውያን ስደተኞችን ከጋዛ ሰርጥ እንዲቀበል የዮርዳኖሱን መሪ አሳውቄዋለሁ። ግብፅም ስደተኞችን እንድትቀበል እፈልጋለሁ። የግብፁን ፕሬዝዳንት ሲሲንም አነጋግራለሁ" ብሏል
🔴 ይህን ተከትሎ የወራሪዋ እስራኤል ብሔራዊ ደህንነት ሚኒስትር የነበረው ኋላ መልቀቂያ ያስገባው ቢን-ገቪር
"የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትራምፕ የጋዛን ህዝብ ወደ ዮርዳኖስና ግብፅ እንዲሰደዱ ለማድረግ ባላቸው ተነሳሽነት እንኳን ደስ አላችሁ" ሲል ተደምጧል።
አክሎም "ከኔታንያሁ ከምንጠይቀው አንዱ በራስ ተነሳሽነት መሰደድ የሚፈልጉትን እንዲያበረታታ ነው" ብሏል
🔴 የሐማስን ቃል አቀባይ ሀዚም ቃሲም በበኩላቸው
የትራምፕ መግለጫ አደገኛ ከእስራኤሉ የቀኝ ክንፍ ጋር የሚጣጣም ነው። ህዝባችን እንዲሰደድ እየተደረገ ያለውን ጥረት እናወግዛለን። ሀሳቡን የትኛውም ፍልስጤማዊም አይቀበለውም።
ፍልስጤማዊያን ወደ ሰሜን ጋዛ ሰርጥ እንዳይመለሱ ወራሪዋ መከልከሏ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በግልፅ መጣስ ነው።
በእስር ላይ የምትገኘው ኤርቢል አይሁድ በህይወት እንዳለች ማረጋገጫ ብንልክም ስምምነቱን ወራሪዋ አልተገበረችም
ፍልስጤማዊያን ወደ ጋዛ ሰርጥ ሙሉ በሙሉ እንዲመለሱ ረአደራዳሪዎች ይህንንም እንዲያስፈፅሙ እንጠይቃለን ብለዋል።
🔴 ወራሪዋ እስራኤል በበኩሏ ኤርቢል አይሁድ ከእስር ካልተፈታች ወደ ጋዛ ሰርጥ የሚያደርሰውን የኔትዛሪም መንገድ አንከፍትም ብላለች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Mahi Mahisho
@islam_in_school