የሠ/መ/ቁጥር 205068 ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ/ም
ስራ መሪ ትርጓሜ ስያሜ ስራን መሪን በመወሰን ረገድ ያለው አግባብነት
የአንድ የሥራ መደብ መጠሪያ ሥራ አሥኪያጅ የሚል መጠሪያ መያዙ ብቻዉን በመደቡ ላይ ተመድቦ የሚሰራዉን ሰዉ የሥራ መሪ ስለማያሰኘዉ የሥራ መዘርዝሩ ላይ የተሰጠዉን ተግባርና ኃላፊነት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 2/10 ስር ለሥራ መሪ ከተሰጠዉ ትርጓሜ ጋር አገናዝቦ መመርመር ያስፈልጋል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት የሥራ መሪ የሚባለዉ በሕግ ወይም እንደ ድርጅቱ የሥራ ጠባይ በአሠሪዉ በተሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን መሰረት የሥራ አመራር ፖሊሲዎችን የማዉጣትና የማስፈጸም ሥልጣን ያለዉ ወይም ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማዛወር፣ የማገድ፣የማሰናበት ወይም የመመደብ ተግባሮችን የመወሰን ሥልጣን ያለዉ ግለሰብ ሲሆን እነዚህን የሥራ አመራር ጉዳዮች አስመልክቶ የአሠሪዉን ጥቅም ለመጠበቅ አሠሪዉ ሊወስደዉ ስለሚገባዉ እርምጃ በማንም ሳይመራ የራሱን የዉሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ የሕግ አገልግሎት ኃላፊ ጭምር እንደሆነ ተደንግጓል፡፡በዚህ ድንጋጌ ላይ “…በአሠሪዉ በተሰጠዉ የዉክልና ሥልጣን…”የሚለዉ አገላለጽ ድርጅቱ ግኡዝ እንደመሆኑ ድርጅቱን ወክሎ የመሪነት ሥራን የሚሰራ ሰዉ ለማለት እንጂ ለአጭር ጊዜ በድርጅቱ ሥራ መሪ ተወክሎ የሚሰራ ሰዉ ለማለት አይደለም፡፡ምክንያቱም በድርጅቱ ሥራ መሪ ጊዜያዊ ዉክልና የሚሰጠዉ ሰዉ ከመነሻዉ ከድርጅቱ ጋር ያለዉ የቅጥር ግንኙነት በአዋጁ አንቀጽ 2/10 ስር የተዘረዘሩትን ተግባርና ኃላነቶች እንዲፈጽም ሥልጣን የሚሰጠዉ ላይሆን ስለሚችል ነዉ፡፡በያዝነዉ ጉዳይ በድርጅቱ ለተጠሪ በተሰጣቸዉ የሥራ መዘርዝር ላይ ተጠሪ እንዲሰሩ የተሰጣቸዉ ተግባርና ኃላፊነት የሥራ አመራር ፖሊሲዎችን የማዉጣትና የማስፈጸም ወይም ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማዛወር፣ የማገድ፣የማሰናበት ወይም የመመደብ እንዳልሆነ ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ ተረድተናል፡፡የአመልካች ኃላፊ ለአጭር ጊዜ ለተጠሪ በሰጧቸዉ ዉክልና የፈጸሙት ተግባር ተጠሪን የሥራ መሪ የሚያሰኛቸዉ አይደለም፡፡በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት የተጠሪን የሥራ መዘርዝር መሰረት በማድረግ ተጠሪ የሥራ መሪ አይደሉም በማለት በመወሰኑ የተፈጸመ ስህተት የለም ብለናል፡፡