ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ለመግባት ፍቃድ ስናገኝ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኔትወርክ ለመገንባት ቃል ገብተን ነበር።
ዛሬ በራሳችን ቡድን የተተከለው የመጀመሪያ ጣቢያችንን በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቆ ለሥራ ዝግጁ መሆኑም የዚህ ማሳያ ነው።
ይህን የመሰሉ ጣቢያዎች ደንበኞቻችን ጋር ለመድረስ የሚያስችሉን የመጨረሻዎቹ ክፍሎች ናቸው።
የመጀመሪያው ጣቢያ በአዲስ አበባ የተተከለ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ይተከላሉ።
አገልግሎቶቻችን ለመጀመር በምንዘጋጅበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ እውን የሚያደርግ ጥራት ያለው ኔትዎርክ የመገንባት ጥረታችንን አፋጥነን እንቀጥላለን።
ይህ ወር የሚያኮሩ ወሳኝ ውጤቶች ያስመዘገብንበት ወቅት ነው፡፡ ዋና መሥሪያቤታችን የገባንበት፤ የተሳካ የመጀመሪያ ጥሪያችንን ያደረበግንበት፣ አሁን ደግሞ የራሳችን የኔትዎርክ ጣቢያ የተከልንበት ነው ፡፡
ለዚህ ሥራ መሳካት ያለእረፍት ሲሰሩ ለነበሩት ባልደረቦቻችን እና አጋሮቻችን እንዲሁም አስፈላጊውን ትብብር የሚያደርግልንን የኢትዮጵያን መንግስት ከልብ ልናመሰኝ እንወዳለን።
#እየገነባንነው #ዲጂታልኢትዮጵያ
@OfficialSafaricom