ከፍቅር ማህደር


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 t̑̈ȏ̈ ከፍቅር ማህደር❤
💙በዚ 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 ላይ
💜ድርሰቶች
💚የፍቅር ግጥሞች
💛ጣፋጭ ታሪኮች
❤️ምክሮች ...
አልፎ አልፎ ቀልዶች ይለቀቁበታል 😂

Since 2016 e.c
❤️ከናተ ሚጠበቀው 𝐉𝐨𝐢𝐧 to request በማረግ ብቻ መከታተል ነው ❤️
👇👇👇

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Profile picture dan repost
❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️❗️

የአንበሳ ልጅ ምን ይባላል?

ቀድመው ለመለሱ 5 ሰዎች የ500 ብር ካርድ ይሸለማሉ።




       ❤️ኤልዳና 💗   

ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ

         
    ክፍል 7

✍ፀሀፊ ማኔ


ማለት እእ እናትህ ስለኔ ታቃለች እንዴ አት ??
እንዴት አታቅሽም ሁሌ ሳወራሽ ትሰማ የለ እንዴ በዛ ላይ ስላንቺ ነግሪያታለሁኮ አለኝ።

እእ የምርህን ነው ምን ነገርካት ስለኔ አልኩት??
ብዙ ነገር ነው የነገርኳት በተለይ ስለፀጉርሽ በደንብ ነግሪያታለሁ  ፀባይሽንም ኮስታራና ጎበዝ ተማሪ መሆንሽንም ብቻ ስላንቺ የማቀውን ሁሉ ነግሪያታለሁ አለኝ።

ማለት ግን እንዴት ስለኔ ልታወሩ ቻላችሁ በድጋሜ ሌላ ጥያቄ ጠየኩት።

የዛኔ ሳቁ አመለጠውና ቆይ ዛሬ ግን ታውቆሻል የጥያቄ መአት እያወረድሽብኝኮ ነው በቃ አወራን ነገርኳት ካላመንሽኝ ደሞ ከራሷ አንደበት አረጋግጪ ላገናኝሽ አለኝ።

አረ አረ አልፈልግም እንዴ ምን አወራለሁ ያምሀል እንዴ በቃ ቻው ስልኩን ልዘጋው ነው ብዬ ካፌ ሳልጨርስ አረ አንቺ አታምሪ ስቀልድ ነው ደሞ እኔ ስደውል አንድ ሰአት ሙሉ እያወራሽ አንቺ ስትደውይ የምን ቶሎ መዝጋት ነው ካርድሽ እስኪዘጋ ታወሪያታለሽ አለኝ።
አረ የኔ ካርድ አያልቅም ሌሊቱን ሙሉ ማውራት ትችላለህ አልኩት።

ብቻ በቃ ድጋሜ ማውራት ተጀመረ  ክፍሌ ገብቼ እስካወራው መጓጓት ሆነ ስራዬ።

እያሱ ቀን ተአምር ቢፈጠር አይደውልም ያችኑ 5 ሰአት ጠብቆ ነው ሚደውለው ቀን ሊያወራኝ ሲፈልግ ቀጥታ text እንኳን አይልክም ቴሌግራም ላይ መልእክት ያስቀምጥልኛል እንጂ ።

ክረምቱን እረፍት ስለሆንኩ ከቤት ምወጣበት እድል የለኝም አባቴ ከከተማ ይዞን ከወጣና ካዝናናን እንጂ እንደሰው አክስቴጋ አጎቴጋ ዘመዴጋ ሚባለው ነገር ለኛ ቤት አይሰራም።

ገና እረፍታችን 15 ቀን እንደሞላው እያሱ ለምን የሆነ ሰበብ ፈጥረሽ አንገናኝም የሚል ሀሳብ አቀረበልኝ እኔም ብሆን እሱን የማየት ፍላጎት ውስጤ ስለነበር እሺ አልኩት ግን እንዴት እንደምንገናኝ ከቤት በምን ሰበብ እንደምወጣ ሁላ አላውቅም ነበር።

ሌሊቱን ሙሉ በምን ሰበብ ላገኘው እንደምችል እያሰብኩ አደርኩኝና አንድ ሀሳብ መጣልኝ በቃ ዴቭን ከቤት ይዞኝ እንዲወጣ አደርግና በዛው እያሱን አገኘዋለሁ ብዬ ወስኜ ዴቭን አወራሁት ካለወትሮዬ ተጨዋች ሆንኩበት በቃ አንተ ቅዳሜና እሁድን ካልሆነ እኛ ቤት አትመጣም ማለት ነው።
በጣም ደብሮኛል ለምን ከቤት ይዘኸኝ አትወጣም አልኩት አይኑን ሳያሽ እሺ አለኝ ።
8 ሰአት ላይ መጥቶ እንደሚወስደኝ ነገረኝ እኔም ተስማማሁ ወዲያው ለእያሱ 8 ሰአት ላይ ከቤት እንደምወጣና የዛኔ እንደምንገናኝ ነገርኩት

አንዱን ልብስ ሳነሳ ስጥል ፁጉሬን አነሰዴ ሳሲዘው ደሞ ስለቀው እንዲሁ መስታወት ፊት ተገትሬ ሰአቴን ገደልኩት።
በስተመጨረሻም ምለብሰውን ልብስና ጫማ መራርጬ አዘጋጅቼ ከዴቭጋ እንደምወጣ ምንም እንደማያውቅ ሰው ሆኜ ሳሎን ከናቴጋ ቁጭ አልኩኝ።

ዴቭ 7.30 ምናምን ላይ ቤት መጣና ለናቴ ይዞኝ ሊወጣ እንደሆነ ነገራት እኔ እንደማያቅ ሰው ማለት ወዴት ልንሄድ ነው ምናምን ብዬ ጠያቄ አነሳሁ
አባትሽ እንዳይደብርሽ ከቤት ይዤሽ እንድወጣ ነግሮኝ ነው አለኝ።
ብድግ ብዬ ወደመኝታ ቤቴ ገባሁና ያዘጋጀሁትን ለባበሼ ፀጉሬን አስተካክዬ ወጣሁ።
መኪናውን ከግቢ ውጪ ነበር ያቆመው  ልክ ከግቤ ውጥት እንዳልን ጥብቅ አድርጎ አቀፈኝና ስላገኘሁሽ ደስ ብሎኛል በማንኛውም ሰአት ከቤት መውጣት ስትፈልጊ ለኔ ንገሪኝ ሹፌርነቴ አሁንም ድረስ ነው አለኝ።

እሺ አመሰግናለሁ ብዬ ወደመኪናው ገብተን ጉዞ ተጀመረ።
ወዴት መሄድ ነው የፈለግሽው ምን መብላት ነው ያማረሽ የት ልውሰድሽ ብሎ በጥያቄ አጣደፈኝ።

እኔ አንዴ ከቤት ወጥቼ እያሱን ስለማገኘት እንጂ ከዴቭጋ ምን እንደማደርግ ምንም አላሰብኩም ነበር።
ሙሉ ስልጣኑን ላንተ ሰጥቼሀለሁ በቃ አንተ ጋብዘኝ ግን ቶሎ ስለምመለስ እሩቅ አኔድም አደል አልኩት በቃ እንደፍላጎትሽ አለኝ ዴቭ ሲያወራ በየመሀሉ እንግሊዘኛ ይቀላቅላል።

እሱ ሚያቀው ቤት ወሰደኝ ምሳ በላን ትንሽ አወራንና ቴሌግራም ውስጥ ስገባ እየጠበኩሽ ነው ልክ ልትመጪ ስትይ አሳውቂኝ እንዳልደውል አይመችሽም ብዬ ነው የሚል መልእክት አስቀምጦልኛል።

አነበብኩትና ቀና ብዬ በቃ ዴቭ ወደቤት እንሂድ አደል ይሄን ያህል ከተናፈስኩ ይበቃኛል አልኩት እሺ እሱን ከፈለግሽ እንሂድ ብሎ ሂሳብ ከፍሎ ከቤቱ ወጣን እየተመለስኩ እንደሆነና ከትምህርት ቤታችን ፊት ለፊት ያለው ካፌ መገናኘት እንደምንችል text አደረኩለት ለእያሱ።

እሺ በቃ እዛ እጠብቅሻለሁ እንዳትቆይ ብሎ መለሰለኝ ።
ከዴቭጋ እኛ ቤት ለመድረስ ትንሽ ሲቀረን በቃ እዚጋ አውርደኝ አልኩት
እንዴ ለምን አለኝ።
በቃ በጣም ስለጠገብኩ ቢያንስ እስከኛቤት ወክ ላድርግ እዚጋ ልውረድ አልኩት።

አይ አይቻልም ወክ ማድረግ ከፈለግሽ ግቢያችሁ እንኳን ወክ ለማድረግ ፈረስ ያስጋልብ የለ እንዴ አደራ እስከተሰጠኝ ድረስ ለእናትሽ ማስረከብ አለብኝ አለ።

አረ ዴቭ ከምሬን ነው በናትህ እዚጋ አውርደኝና ወክ ላድርግ እእ እኔኮ እናንተ እንደምታስቡት ህፃን ኘደለሁም እስቲ ከዚች እስከዚች እንኳን ወክ እንዳደርግ ፍቀዱልኝ አልኩት እየተቅለሰለስኩ እሺ በቃ እደውላለሁ እሺ አሁኑኑ ግቢ ብሎ ጫፍጋ አውርዶኝ እሱ ተመለሰ እኔ እቤት አዩኝ አላዩኝ እየተሳቀኩ ወደ እያሱጋ ለመሄድ የመጣሁትን መንገድ ተመልሼ ሄድኩኝ ።

እውነት ለመናገር ለብቻዬ ወጥቼ ስለማላቅ መሰለኝ በቃ ሁሌ ምሄድበት መንገድ በራሱ ጥፍት አለብኝ ታክሲ ከየቱጋ እንደምይዝ ድንብርብሬ ወጣ በዛ ላይ ልቤ በጣም ተጨንቆ ነበር ቤተሰቦቼን የከዳኋቸው ያዋረድኳቸው አይነት ስሜት እየተሰማኝ ነበር።

ሰው ሁላ ለምን እያፈጠጠብኝ እንደሆነ እኔን እኔን ሲያዩ ደሞ ጭራሽ ባሰብኝ እያሱጋ ደርሼ እስክመለስ ነገር አለሙ ሁላ ተበጥብጦ ሚጠብቀኝ መሰለኝ።

ስመለስ የናቴን አይን እንዴት እንደማየው ጨነቀኝ ድንገት ዴቭ ወደቤት ተመልሶ ቢመጣስ እናቴጋ ቢደውልስ እናቴ ምን ትላለች በቃ እዛ አስፋልት ላይ ቆሜ ጭንቅ ሲለኝ እንዴ ምነው ይሄን ያህል ቢቀርስ ብዬ ወደቤቴ ተመለስኩ እየተመለስኩ ስልኬን ከፍቼ እያሱ የላከልኝን አየሁ ኤልዱ ቆየሽኮ እየጠበኩሽ ነው ይላል አይቼው ዝም ብዬ ወደቤቴ ገባሁ...



ክፍል 9 ከ 100 like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

                 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
      
https://t.me/+cRqtf_gOk54zYmU8


             


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ ኤልዳና ክፍል 8 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


       ❤️ኤልዳና 💗   

ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ

         
    ክፍል 7

✍ፀሀፊ ማኔ

        አቀልጂ የምርሽን ነው ብሎ ቶሎ አወረደኝና ወደመኪናው ገብቶ ሄዴ ከአይኔ እስኪሰወር ቆሜ አየሁትና ወደ ግቢ ለመግባት ዞር ስል እያሱ ጥጉን ይዞ ቆሞ እኔ ላይ እያፈፈጠብኝ ነበር ።

ምን እንደዛ እንዳስደነገጠኝ አላቅም ግን የመደንገጥ አንድና ሁለት የሌለለው አደነጋገጥ ነበር የደነገጥኩት ።
ብቻ ዝም ብዬው ወደ ክላሴ ገባሁ ከኋላዬ ተከትሎኝ ገብቶ ቁጭ አለ ብንጠብቅ ብንጠብቅ አስተማሪ አልገባ አለ።

ሁሉም እያወራ እየተሳሳቀ ክፍሉን እየበጠበጠ ነበር።
እኔና እሱ ብቻ በዝምታ ውስጥ ቁጭ ብለናል። በመሀል ወረቀትና አስኪብርቶ አውጥቶ ፅፎ ቀስ ብሎ ሰጠኝ።

ውይ ሹፌርሽ ደስ የሚል ሰው ነው ጭራሽ እያንጠለጠለ ነው ቻው የሚልሽ ወይስ ሹፌርሽ ብቻ ሳይሆን የወደፊትም ባልሽም ጭምር ነው ይላል።
አንብቤ እስክጨርስ ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር ወረቀቱን ቀዳድጄ ከፊት ለፊቱ መሬት ላይ በተንኩትና ዝም አልኩት ግን አላስችልሽ አለኝና ፃፍኩለት።

ይቅርታ ግን እድሜዬ ስለትዳር ለማሰብ የደረሰ ይመስላል እንዴ ምንድነው ምታወራው አልኩት።

መልስ ሳይሰጠኝ ዝም አለኝ።

ማታ ላይ online ሳይገባ አመሸ ሰአቴ ሲደርስ ተኛሁ።
አምስት ሰአት ላይ ደውሎ ቀሰቀሰኝ አነሳሁት ይቅርታ እረበሽኩሽ እንዴ እንቅልፍሽ በጣም ከመጣ ተኚ አለኝ።
አረ ችግር የለውም አውራኝ ቆይ አንዴ መልሼ ልደውልልህ ብዬው ተነስቼ ፊቴን ታጠብኩ ነቃ ለማለት እንዲረዳኝ ብዬ ነበር።
መልሼ ስደውልለት ዘጋብኝ
ወዲያው መልሶ ደወለ አነሳሁት።
ካርድ እንዳያልቅብሽ ብዬ ሳይሆን የገዛሁት ፓኬጅ እንዳይቃጠል ነው አለኝ።
እእ እሺ እና እንዴት ነህ ውሎ ምሽች በቃ ከዚህ የዘለለ ጥያቄ የለኝም።

ሁሉም ቆንጆ ነበር ጠዋት አናደድኩሽ እንዴ አለኝ።
አዎ ግን አሁን እረስቼዋለሁ አልኩት።
ይቅርታ በጣም ላናድድሽ ፈልጌ አደለም ባለፈው ወንድምሽ ምናምን መስሎኝ ነበር ግን ትናት ወንድምም እህትም የለኝም ስትይ ወንድም እንደሌለሽ አወኩ እና በዛ ልክ ትቀራረባላችሁ ብዬ ስላልጠበኩ ነው እንደዛ ያልኩሽ አለኝ።
አረ እንደምታስበው ያን ያህል ምንቀራረብ ሰዎች እንኳን አደለንም አጋጣሚ ዛሬ ስላየኸን ነው እንጂ አልኩት።
አይ አሪፍ ነው ሹፌርሽ ግን ሹፌር አይመስልም ሀብታም እንደሆነ ወዙ እራሱ ያስታውቃል መቼስ በዘመድ ገብቶ መሆን አለበት አለኝ።
.
.
.
እያወራን ያው 6 ሰአቷ ደረሰችና ስልኩ ተዘጋ እንደለመድኩት እንደ እብድ መስታወት ፊት እራሴን ገትሬ ቆይ ግን እውነት ሁሉም እንደሚሉት ቆንጆ ነኝ እንዴ እላለሁ በፈገግታ እራሴን እየተመለከትኩት ከዛ ደሞ እደጅልም ያዘልለኛል ።
የሆነ ሰአት ደሞ ቆም ብዬ አስብና ቆይ ግን ከእያሱጋ ለምንድነው እንደዚህ ምናወራው ምን እየሆነኩ ነው ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ
ግን ምናወራው ጓደኛ ሲኖረን ደስ ይላል ጓደኛዬ እራሱ መሆን ይችላል ምን ችግር አለው በስልክ ብቻ ነው በአካል አናወራ እላለሁ ።
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተዘረርኩኝና ጣራ ጣራ ማየት ጀመርኩ።
ሳላስበው እንቅልፍ ወሰደኝ።
.
.
.
.
የኛ ፈተና በየጊዜው ነው ማለት ይቻላል አንዱን ተፈትነን ብዙም ሳይቆይ ሌላው ይመጣል።
የሚቀጥለው ውጤቴ ወደ አንደኛ ካልተመለሰ አባቴ ምን እንደሚያደርገኝ መገመት በራሱ በጣም ከባድ ነው እንደምንም አጥንቼ እያሱን መብለጥ አለብኝ ብዬ አስብና መልሼ ደሞ አረ እንኳን በለጠኝ እኩል ብንሆን እራሱ  አውቄ  x እንዲገባብኝ የማደርግ ነው ሚመስለኝ እላለሁ።
ብቻ ጊዜው ይሮጣል እያሱ አንዳንዴ የልቤ ሰው የሆነ ያህል እስኪመስለኝ እንቀራረባለን።
አንዳንዴ ደሞ ምክንያቱን ሳላቀው ለምን እንደምናወራኮ አላቅም ዝም ብሎ ልጅነት ይዞን እንጂ ጓደኝነታችን ትርጉም የለውም ይለኝና ድንገት ተነስቶ ይጠፋብኛል።

ለምን እንደዛ እንደሚሆን አላውቅም።

በዚህ በኩል ዴቭ በቃ መልአክ የሆነ እስኪመስለኝ ድረስ ከኔጋ ለመቀራረብና ጓደኛ ለመሆን ይሞክራል ግን ለምን እንደሆነ አላቅም ይሄ ውስጤን ክፍት አድርጎ ለማስገባት የሚከብደኝ አይነት ቅርቤ ሆኖ እሩቅ እንዳለ የሚሰማኝ አይነት ሰው ነው ሚሆንብኝ ።

     

ፈተና የደረሰ ሰሞን እያሱ ከነጭራሹ ዘግቶኝ ማውራት አቁመን ነበር ::
እኔ ደሞ እሱ ካላወራኝ ማውራት ካልደወለ መደወል ያስጠላኛል።

ሲዘጋኝ እኔም እዘጋዋለሁ ሲቀርበኝ እኔም እቀርበዋለሁ።

ፈተና የደረሰ ሰሞን ግን በጣም አናዶኝ እልህ ይዞኝ ስለነበር ላለመበለጥ ወጥሬ አጠናሁ።

በሚገርም ሁኔታ አንድ ትምህርት ብቻ ነበር አንድ ጥያቄ የተሳሳትኩት ሌላውን እንዳለ ደፈንኩኝ እያሱ ስንት ያምጣ ስንት ያምጣ ሁላ ቼክ አላደረኩትም።
ፈተና እንደጨረስን ስለውጤት በመጠየቅ ሰበብ ደግሞ አወራኝ።
ሁሌ አዲስ ምሆነው ነገር አለ ደግሜ እንዳዲስ ከሱጋ ማውራት መሳሳቅ ጀመርኩ።

የsecond ሴሚስተር ውጤታች የሁለታችንም አሪፍ ውጤትና ተቀራራቢ ነበር
አባቴ በገባ በወጣ ቁጥር ድጋሜ ትበለጭና ዋ ኤልዱ እንዳላዝንብሽ ይለኛል።
ብቻ በቃ ፈጠሪ የፈቀደው ይሁን እኔ ስለ እያሱ ሳላስብ የራሴን ፈተና እሰራለሁ ፋይናል ላይ ብዬ ወስኜ በጣም ማጥናት ጀመርኩ።
ያው ጊዜው ይሮጥ የለ እነደቀልድ ዘጠኝን ጨርሰን ፋይናል ፈተና ደረሰ።

ተፈተንን ውጤት መጣ እያሱን በ0.5 ብቻ በልጬው እኔ አንደኛ ወጣሁ አባቴ በደስታ ብዛት ሚሆነውን አጣው ድሮምኮ የኔ ልጅ እተማመንብሻለሁ አለ ።

ለመጀመሪያ ጊዜም እያሱን በደንብ አየውና ተፎካካሪዬ ማን እንደሆነ አወቀ አስተያየቱ ልክ አልነበረም እኔ በመሀል ቤት ልቤ ደስታም ሀዘንም እየተሰማው ወደቤት ሄድኩ ሁሉም በውጤቴ ደስተኞች ስለነበሩ የቤተሰብ አራት ውጪ እንብላ ተብሎ ወጣን የቤተሰብ እራት ውስጥ ዴቭ ምን ሊሰራ እንደመጣ ባይገባኝም እሱም ተገኝቶ ነበር።
አሪፍ ጊዜ አሳልፈን ወደቤት ተመለስን የሚገርመው ነገር አባቴ እኔና ዴቭ በሱ መኪና ከኋላ እንድንመጣ አባቴና እናቴ በሱ መኪና ከፊት እንዲሄዱ አደረገ ለምን እንደሆነ ግን አልገባኝም ነበር ።
ወደቤት እየሄድን ዴቭ በውጤቴ ምን ያህል ደስ እንዳለው እየነገረኝ ነበር።
ቤት አድርሶኝ ተሰነባብቶን ተመልሶ ወደቤቱ ሄደ።
ቤት እንደደረስን ሁሉም  ወደመኝታው  አመራ እኔ ግን ክፍሌ ገብቼ መተኛት አልቻልኩም ነበር ባለፈው እያሱ ያለኝ ነገር መጣብኝ።
ስለውጤትና ስለናቱ ያወራውን አስታውሼ አላስችልሽ አለኝና ደወልኩለት።
አነሳውና አወራኝ ።
ስለበለጥኩህ ደበረህ እንዴ ብዬ ጠየኩት።
ከት ብሎ ሳቀና ኤልዱ ተይ እንጂ እኔኮ ሀ እንጂ ፋራ አደለሁም የበለጥሽኝ ጎብዘሽ ስለሰራሽና ስላጠናሽ ነው ታዲያ ምን ልሁን ብዬ ነው ምናደድብሽ ።
ሚገባሽን ነው ያገኘሽው ውጤቱን ካያችሁ ቡሀላ የነበረውን ያባትሽን ደስታ ሳየው ደሞ እኔም ደስ ብሎኝ ነበር።
ቤተሰብን እንደማስደሰት ደስ የሚል ነገር የለም እናቴም ብትሆን አንቺ እንደበለጥሽኝ ስታውቅ ደስ ነው ያላት አለኝ።    

ክፍል 8 ከ 100 like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

                 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
      
https://t.me/+cRqtf_gOk54zYmU8


             


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ ኤልዳና ክፍል 7 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


       ❤️ኤልዳና 💗   

ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ

         
    ክፍል 6

✍ፀሀፊ ማኔ


እኔኮ ከግሩፕ ውስጥ ነው አውጥቼ ያወራሁሽ ቴሌግራም ላይ ደሞ ቁጥርሽ አይወጣም ላኪልኝና እደውልልሻለሁ አለኝ።
እሺ ብዬ ላኩለት ።
በቃ እደውላለሁ ብሎ ከonline ወጣ እኔም እንቅልፌን ተኛሁ።
አምስት ሰአት አካባቢ ላይ ስልኬ ጠራ በእንቅልፍ ልቤ አነሳሁት ሄሎ ኤልዱ ሲለኝ እንዴት ብድግ እንዳልኩ ሁላ አላቅም ባንዴ ነበር እሱ መሆኑን ያወኩት ምነው በዚህ በሌሊት በሰላም ነው አልኩት።
አዎ በአምስት ብር የአንድ ሰአት ፍሪ ፓኬጅ ገዝቼ ነው እስከ ስድስት ሰአት ይቆያል ፈታ ብለሽ አውሪ አለኝ።

ድምፁን ስሰማ የማወራው ሁላ ጠፋብኝ እየደገምኩ ተመሳሳይ ነገር ማውራት መጠየቅ ጀመርኩ ።

እሱ ምንም አልመሰለውም ፈታ ብሎ ጥያቄዎችን ይጠይቀኛል ።

እህት አለሽ ወንድምስ??

ቤት ውስጥ ስንት ናችሁ ምን ያናድድሻል ምን ያስደስትሻል ,ክላስ ውስጥ ለምንድነው በዛ ልክ ኮስታራ የሆንሽው ?? ብቻ ስለራሴ ማወቅ ያለበትን ያህል ጠየቀኝ ።

እያሱ በጣም ደስ የሚል ልጅ ነው ጥሎብኝ ሰዎችን አይቼ ከሚገዛኝ ነገር አንዱ ሲያወሩ እርጋታቸው ነው።

እያሱ እንደዛ ነው አንዱን ወሬ ጀምሮ ወደሌላኛው አይዘልም ሲያወራ አይቸኩልም ካፉ ሚወጡት ቃላት ተዘጋጅቶበት የሚያወራ ነው ሚመስሉት ብቻ ፈጣሪ በሚያቀው ምን ምን እያወራን 6 ሰአት እንደሞላ ማስታወስ አልችልም ግን እስከዛ እያወራን ነበር መጨረሻ ላይ ስልኩን ከመዝጋቱ በፊት ሳረሳው በጣም ቆንጆና ደስ የምትይ ልጅ እንደሆንሽ ሳልነግርሽ ማለፍ አልፈልግም ሀብታም ብሆን ኖሮ ሳድግ አንቺን ነበር ማገባው አለኝ።

ከት ብዬ ሳኩኝ ይሄ ከልብ የመነጨ ደስታ ሚባለው አለ አደል በቃ ከልቤ ደስ አለኝና ለትዳር ሀብት መስፈርት ይሆናል እንዴ አልኩት??

ግጥም አድርጎ ነዋ ለነገሩ ልጅ ነሽ አሁን  ብዙም አይገባሽም  ወደፊት ታቂዋለሽ በቃ ደና ደሪ አለኝና ስልኩ ተዘጋ ።

ደሞ ሚገርመው እሱም ለቤተሰቦቹ ብቸኛ ልጅ ነው።

ስልኬን እያየሁ ፈገግ አልኩና መልሼ ኩስትር አልኩ። ምን እየሆነኩ ነው ሆ የምን መጃጃል ነው አልኩኝ ለራሴ መልሼ ደሞ ወይኔ ግን ታድሎ እንዴት እንደዚህ ፈጣሪ ሁሉን አሟልቶ ይሰጠዋል እልና መልሼ ፈገግ እላለሁ ብቻዬን ድራማ ስሰራ እንቅልፌን ተኛሁ።


ጠዋት ተነስቼ ክላስ ስገባ እያሱን እንደማየው እያሰብኩ ግቢው ውስጥ እስክደርስ ጓጉቼ ነበር።
ዴቭ ጠዋት ሲመጣ በቃ በጣም በሚባል ደረጃ  አምሮበት ነበር

እንዴየሁት ፈገግ አልኩና ዛሬ ምን ተገኝቶ ነው ሙሽራ መስለሀል አልኩት ሰላምታ እየተቀያየርን።
ያው አንዳንዴ ያስፈልጋል  እስኪ እናንተን እንምሰል ብዬ ነው አንቺ ምን እያገኘሽ ነው ሁሌ ሙሽራ መስለሽ ምትወጭው አለኝ።
ኦኦ ዛሬ አለባበስህ ብቻ አደለም ምላስህም ተቀይሯል በል በል እንሂድ ብዬው ጉዟችንን ጀመርን።

ወደ መኪናው ሲገባ የሸተተኝ ሽቶ ይለይ ነበር እንዴ ዛሬ ምትሄድበት አለህ እንዴ ከወትሮው ለየት ብለኽብኛል አልኩት።

አዎ አንድ ፕሮግራም አለኝ  አንቺን ሳላደርስ እንዳልሄድ ብዬ ነው አለኝ።
አረ ችግር የለውም ነበር ነግረኸኝ ብትቀር ኖርማል ነው

ለማንኛውም ግን ዛሬ መጠለፍህ ነው ዘጠኝ ሰአት መጥቶ ሚወስደኝ ሰው ማጣቴ ነው ጠረንህ ሁላ ከሩቅ ይጠራቸዋል አልኩት።

አረ የምርሽን ነው አንቺን ከሩቅ ጠርቶሻል እንዴ አለኝ።

አረ እኔ ባይጠራኝምኮ ወዳንተ መምጣቴ አይቀርም ነበር አልኩት እየሳኩ።
እሱም እኔም በጣም እያወራን ትምህርት ቤቴ በር ላይ ደረስን ልወርድ ስል በል በቃ መመለስህንም እንጃ ልሰናበትህ እንጂ ብዬ ቀልጄበት ቻው ብዬው ከመኪናው ወረድኩ ተከትሎኝ ወረደና መመለሴን ከተጠራጠርሽማ በቃ ልሰናበትሽ ብሎ አቅፎ አንጠለጠለኝ ስስቅ ተማሪ እንዳያየኝ ሳቄን ዋጥ አድርጌ አንተ አውርደኝ ጉዴ ፈላ በቃ አስተማሪ አየኝ አልኩት እንዲደነገጥ ብዬ
      ‌‌‌‌‌‌‌     

ላይኩ 50 ከሞላ አንድ ክፍል ይጨመራል


ክፍል 7 ከ 100 like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

                 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
      
https://t.me/+cRqtf_gOk54zYmU8


             


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ ኤልዳና ክፍል 6 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


       ❤️ኤልዳና 💗   

ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ

         
    ክፍል 5

✍ፀሀፊ ማኔ

እኔ ምን አውቃለሁ ብያት ከዳዊትጋ ከቤት ወጣን በጣም የሚያምር የተንጣለለ የሚባል ቤት ወሰደኝ።
ገብተን ቁጭ አልን ለሚያየን ሰው ታናሽ እህቱን ለማዝናናት የመጣ ነው ሚመስለው።
ምንም ነገር ከማዘዛችን በፊት ዴቭ እኔኮ ይሄን ያህል ቅንጦት የበዛበት ቦታ የምወድ አይነት ልጅ አደለሁም ግዴታ በዚህ ልክ ወጪ ማውጣት የለብህ ምሳ ለመብላት ከሆነ ከዚህ ረከስ የሚሉ ቤቶች አይጠፉምኮ ካቅም በላይ ወጪ ምን አስወጣህ አልኩት??

ይሄን አስተሳሰብሽንኮ ነው ምወድልሽ ግን ችግር የለውም ላንቺ ሚሆን አላጣም እዘዚ አለኝ።
እሺ ብዬ ምሳችንን አዘዝን የሚጠጣ ነገር ሲባል ውሀ አዘዝኩኝ ምናልባት መጠጣት ከፈለግሽ ግን ይቻላል አለኝ።
ከመቼ ጀምሮ ነው እኔ መጠጣት ምፈልገው ተው እንጂ ዳዊት አልኩት ንዴቴን በፈገግታዬ ለመሸፈን እየሞከርኩ።

እሺ በቃ ማይናገረውን ብይ አለኝ።
ምሳ እየበላን አስሬ ስልኬን እየከፈትኩ ከእያሱ የተላከልኝ መልእክት ካለ እያየሁ ነበር።

ብቻ ምንም ሳናወራ እንዲሁ ቁጭ አልን በጣም ጨነቀኝ የማየው ሁላ ግራ እስኪገባኝ ድረስ ነበር የተጨነኩት
ትንሽ ከቆየን ቡሀላ በቃ ዴቭ እንሂድ እኔ እየጨነቀኝ ነው አልኩት እሺ በቃ እንሂድ እኔኮ ማወራው ነገር ግራ ገብቶኝ ነው ድንገት በንግግሬ መሀል ገደቤን እንዳላልፍ ስለምፈራ ነው አለኝ።

አረ በዚህ ልክ አትጨነቅ እኔኮ ነገሮችን አክብጄ የማይ አይነት ልጅ አደለሁም ደሞ በጣምም ታናሽህ ነኝኮ ምንም ብትናገር መብትህ ነው ነፃ መሆን ነው ያለብህ አልኩት ወደመኪናችን እየገባን ነበር።
ወደቤት እየሄድን ለምን ዞር ዞር ብለን ከተማዋን አናያትም በጊዜ ወደቤት ከምትገቢ አለኝ።
አይ አመሰግናለሁ ወደቤት ብገባ ይሻለኛል ከናቴጋ ማምሸት ነው ምፈልገው አልኩት እሺ አለኝና ወደቤት ነዳው።

በር ላይ ስንደርስ አውርዶኝ አቅፎ ቻው ብሎኝ ከውጪ ተመለሰ።
ቤት ስገባ እናቴ ቁጭ ብላ ፕሮግራም እያየች ነበር ።
አስተያየቷ ደስ አላለኝም ስሚያት ልብስ ልቀይር ብዬ ወደክፍሌ ገባሁ ልብሴን ከመቀየሬ በፊት እራሴን በመስታወት ማስተዋል ጀመርኩ ።
ልክ ጥፋተኛ የሆንኩ ያህል ተሰማኝ ከዴቭጋ መውጣቴ ቤተሰቦቼ በሌሉበት እሱን ማግኘቴ በቃ ቤተሰቦቼ ላይ በደል የፈፀምኩ ያህል ውስጤን ክፍት አለው።
ለምን እንደዛ እንደምሆን ሁላ አላውቅም ነበር ብቻ እራሴን ለማፅናናት ያህል አባቴ ፈቅዶልኝኮ ቆይ ምን አደረኩ እላለሁ።

ልብሴን ቀይሬ ተመልሼ ወጥቼ ከናቴ አጠገብ ቁጭ አልኩኝ እንዴት እንደነበር ከዴቭጋ ምን ምን እንዳደረግን ጠየቀችኝ ነገርኳት ጥሩ አንዳንዴ እንደዚህ ወጣ ማለትሽ አይከፋም አለችኝ እኔ ግን ምንም ደስ እንዳላለኝ እሱን አግቼ ስመለስ የተሰማኝን ስሜት በሙሉ ነገርኳት።

እንድረጋጋ ያህል ጉልበቷ ላይ አስተኝታ ፀጉሬን እያሻሸች ሊያዝናናኝ የሚችሉ አይነት ወሬዎችን አወራችልኝ።

ሲመሽ እራታችንን በላንና ወደክፍሌ ገባሁ አባቴ ሲደውል ተመልሼ ወጣሁና አውርቼው ተመልሼ ገብቼ እያሱ ቴክስት እስኪልክ መጠበቅ ጀመርኩ።
ወደ 3 ሰአት አካባቢ ላከልኝ ምነው ቀኑን ሙሉ ጠፋህ?? አልኩት

ስራ ይዤ ነበር አለኝ።

ዛሬ እሁድ እረፍት አደል ምን ስራ ይኖራል አልኩት።

እሁድ እረፍት የሚሆነው ለእናንተ ነው ለኛ አደለም አለኝ።
ማለት አልኩት ወሬ አስቀይሶ ሌላ ነገር ማውራት ጀመረ።ብቻ እኔና እሱ online ላይ ወሬያችንን እየኮመኮምን በአካል ደሞ አንድ ቀን ቀና ብለን እንኳን ሳንተያይ ዴቭም እቤት እየመጣ ቅዳሜና እሁድን እኛጋ ማሳለፉን እንደተያያዘው ግማሽ ሴሚስቴር ደርሶ ለፈተና መዘጋጀት ጀመርን።

እያሱ  ከፈተናው ከሳምንት በፊት ነበር ማውራት እንድናቆም የነገረኝ።

ፈተናው እንደጨረስን ድጋሜ ከእያሱጋ ማውራት ጀመርን።
ለካ አሁን እረፍት ነን አንተያይም ቢያንስ በፊት ስትገባ አይህ ነበር ስገባ ታየኝ ነበር አልኩት።

አዎ ምን ማድረግ ይቻላል ውጤት ግን እንዴት የሚሆን ይመስልሻል አሪፍ ሰርተሻል አደል አለኝ።

አዎ ፈተናው ያን ያህል ከባድ አልነበረም አንተስ አልኩት("በነገራችን ላይ እሰካዛሬ ከተፈተናቸው ፈተናዎች ውስጥ በአንዱ ብቻ ነው የበለጥኩት ሌላውን እንዳለ በልጦኛል)

ቀላል ነበር ያጠናሁት ነው የመጣው አለኝ።

ብቻ እረፍቱን አባቴ ከኔጋ ሰፊ ጊዜ እንዲኖረው ስለፈለገ አብዛኛውን ጊዜ እቤት ነበር የሚውለው

ዴቬም ቅዳሜና እሁድን እየጠበቀ ቤት ይመጣል ካባቴጋ ጓደኝነት ይሁን የስራ ባልደረባ አይገባኝም ብቻ ቅርበታቸው በጣም ያስደንቀኛል።

አባቴ ከሚባለው በላይ ሰው ይመርጣል አደለም ቤቱ ድረስ እንዲመጣ ከልጁጋ አብሮ እንዲዝናና ሚፈቅድለትን ሰው ይቅርና መንገድ ላይ ሰላምታ ሚሰጠውን ሰው ሁላ መርጦ ነው ።
እንዲሁ የዴቭ ነገር ለኔና ለናቴ ጥያቄ እንደሆነብን  እረፍታችን አልቆ ወደ ክላስ ተመለስን ከእያሱጋ የእረፍቱን ቀን እንደበፊቱ እያወራን አልነበረም ትምህርት ሊከፈት አካባቢ ትንሽ ቀዝቀዝ ብለን ነበር ለምን እንደሆነ ግን አላቅም ወደ ክላስ ከተመለስን ቡሀላ ውጤት ስናይ እያሱ ነበር ከክላስ አንደኛ የወጣው በትንሽ ነጥብ በልጦኝ ነበር።

አባቴ ይሄን ሲሰማ አበደ ለመጀመሪያ ጊዜ በክላስ ተማሪ ተበለጥኩ እንደው አይቻል ሆኖበት እንጂ ቢመታኝ ሁላ ደስታው ነበር ልጁን አሳዩኝ ማነው ወንዱ የኔን ልጅ የበለጠው አንቺ ከመማር ውጪ ምን ስትሰሪ ነው የተበለጥሽው ብሎ ጮኸ እኔ ግን ምንም አልመሰለኝሥ ምክንያቱም የበለጠኝ እያሱ ነው።

ቀጣይ አንደኛ እንደምወጣ ቃል ገብቼለት አባቴን አረጋጋሁትና ወደ ትምህርቴ ተመለስኩ  ።

አስታውሳለሁ እሮብ ቀን ነበር ጠዋት የመጀመሪያውን ክፍለ ጊዜ እየተማርን አንደኛ ስለወጣህ እንኳን ደስ አለህ ቴሌግራም ላይ ስለማናወራ በአካል ልበልህ ብዬ ነው የሚል ወረቀት ፅፌ ሰጠሁት።

ተቀበለኝና ሳያነበው ኪሱ ከተተው  እንዴት እንደተቃጠልኩ እኔና ፈጣሪ እናውቃለን ።
ልክ አስተማሪዋ እንደወጣች ወደኪሱ ገብቶ ወረቀቱን አወጣና አነበበው።

ስለበለጥኩሽ ይቅርታ ግን ካንቺ ቤተሰቦች የኔ እናት በጣም ታሳዝነኛለች ላደርግላት የምችለው ብቸኛ ነገር በቃ በትምህርቴ በጣም ጎበዝ ሆኜ ላስደስታት ላኮራት ተስፋ ልሆናት ነው ምችለው ደሞ ከዛሬ ጀምሮ ቴሌግራም ላይ እናወራለን እሺ ብሎ ፅፎ ሰጠኝ።

ተቀብዬ አነበብኩትና ቀዳድጄ ጣልኩት

ማታ እራቴን በልቼ እንደጨረሰኩ ወደክፍሌ ገብቼ ማጥናት ጀመርኩ ስልኬን ካጠገቤ አርቄ ነበር እናቴ አስሬ እየመጣች ማጥናት አለማጥናቴን ቼክ እያደረገች ስለነበር እንዳትጠረጥረኝ ፈርቼ ነበር።

ማታ እስከ አራት ሰአት ድረስ ጥናቴን ጨራረስኩና ክፍሌን ቆልፌ ስልኬን አነሳሁ እያሱ ፅፎልኝ ነበር ።
ይቅርታ በየቀኑኮ ካንቺጋ ሳወራ በቀን በቀን ካርድ መሙላቱ እራሱ ሌላ ወጪ ሆኖብኝ ነው እንደውም ለምን ስልክሽን አትልኪልኝም ደውዬልሽኮ ማውራት እንችላለን አለኝ።

እስካሁን ስልኬ የለህም እንዴ ማውራት ከጀመርንኮ ቆየን አልኩት።


ላይኩ 50 ከሞላ አንድ ክፍል ይጨመራል


ክፍል 6 ከ 100 like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

                 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
      
https://t.me/+cRqtf_gOk54zYmU8


             


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ ኤልዳና ክፍል 5 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የሀገራችን ችግር እንደዚህ ተቆልፎ ነው እኮ አልፈታ ያለው😂😂


       ❤️ኤልዳና 💗   

ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ

         
    ክፍል 4

✍ፀሀፊ ማኔ

ብቻ የዛን ቀን ውጤቱን ሲያይ አይሞቀው አይበርደው በቃ የጠበቀው ነገር እንዳገኘ ግልፅ ነው።

ማታ ቤት እንደገባሁ ግሩፓችን ውስጥ ገብቼ የሱን ስም ፈለኩና እራሴ ፃፍኩለት ለካ እንደዚህ ጎበዝ ነህ በቃ ታስጠናኛለህ አልኩት ለመቀለድ መሞከሬ ነበር በኔ ቤት።

አረ ባክሽ አስጠናሀለሁ ለማለት ፈልገሽ ነው አለኝ።
አንተኮ ነህ የበለጥከኝ ??

እኔ እንደበለጥኩሽ በምን አወቅሽ የኔን ውጤት ስትከታተይ ነበር ማለት ነው አለኝ።
አረ አደለም እንዲሁ ከፊት ለፊት ስለምትቀመጥ አጋጣሚ ነው እንጂ አልኩት።

እሺ አለኝ።
እሺ ሲለኝ እልህ ነገር ያዘኝ ይሁን ወይ እኔጃ ብቻ ግን ንዴት በሚመስል መልኩ ማውራት አልፈለክም እንዴ አልኩት።

ማውራት ባልፈልግኮ እንደባለፈው እንዳንቺ የተፃፃፍነውን አጠፋው ነበር አለኝ።

ኦኦ በሱ ተናደህ ነው እንዴ ይቅርታ በቃ አልኩት።
ችግር የለውም አልፏል በቃ አለኝ።
አሺ አልኩት።
ግን በድጋሜ ልንገርሽ በጣም ተናድጄብሽ ነበር አለኝ።

አረ በቃ እርሳው ጭቅጭቅ አስመሰልነውኮ ወሬያችንን አልኩት ነገሮችን ለማብረድ አስቤ።
ደስ የሚለው እሱም ቀለል አደረገውና በዛው አንድ አንድ እያልን ማውራት ጀመርን ።
ምንም ሳላጠና እራት ተጠርቼ ወጣሁ ወደክፍሌ እስክገባም ቸኩዬ ነበር ብቻ ካባቴጋ የተወሰነ ካወራን ቡሀላ ያልጨረስኩት ጥናት እንዳለኝ ነግሬው ቶሎ ወደክፍሌ ገባሁና ማውራት ጀመርን።

ምን እንዳወራን ሁላ አላውቅም ግን ዴቭ ሁላ ምነው እስካሁን እንዴት ቆየሽ ብሎ እስኪረመብኝ ድረስ እያወራን ነበር።
የሆነ ሰአት ላይ ከonline ወጥቶ ቆየ እኔም እንቅልፍ ወሰደኝ።
ጠዋት እንደተነሳሁ መጀመሪያ የሱን text ቼክ አደረኩኝ ምንም አላከልኝም።
ተነስቼ ወደክላሴ ሄድኩ አሁን ግን ስንገናኝ በአካል እናወራ ይሆን እንዴ ወይስ እንደሌላ ጊዜው ዝም ነው ምንባባለው እያልኩ ከራሴጋ እያወራሁ ነበር።

ክላስ ስገባ እሱ አልመጣም ገብቼ ቁጭ እንዳልኩ አስተማሪ ገባ ከኋላዋ ተከትሏት ስላረፈደ ይቅርታ ጠይቆ ገባ።

ቀኑን ሙሉ ምንም እንዳላወራ እንደማይተዋወቅ ሰው ሆነን ዋልን።
ቴሌግራም ላይ ግን ማውራታችንን ተያያዝነው ።
እስከሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ክላስ ውስጥ ምንም እንደማይተዋወቅ ሰው እየሆንን እቤት እቤት ስንሆን ደሞ ከኛ በላይ ጓደኛ ያለ እስከማይመስለን እያወራን ቆየን።
እያሱ መልክና ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን የሚገርም ፀባይም አለው ።
ስናወራ ይሄ እረጅም አመት አብሮ እንደቆየ እንደሚተዋወቅ ሰው ነበር ወሬያችን።

ከወሬያችን ውስጥ ግን ቀልቤን የሳበው አንድ ነገር ነበር።
እያወራን ሳናስበው ሰአቱ ይሄዳል አምስት ሰአት አካባቢ በቃ ደና ደሪ 11 ሰአት ስለምነሳ አሁን ቶሎ መተኛት አለብኝ ይለኛል።
ለምን ስለው??
እናቴን ማገዝ አለብኝ 11 ሰአት ተነስቼ እሷን በስራ አግዤ ነው ወደትምህርት ቤት የምመጣው ይለኛል።
እናትህ ስራዋ ምንድነው በሌሊት እንድትነሳ የሚያደርግህ ልለው አስብና አጉል ድፍረት መስሎኝ ዝም እላለሁ።

ብቻ ሳምንቱ አልቆ እሁድ ቀን ላይ ዴቭ እንደለመደው ቤት መጣና አብረን እንውጣ ምሳ ልጋብዝሽ አለኝ ።

አረ እኔ አልወጣም አባቴ ይገለኛል እንደዚህ ስትል ቢሰማህ እራሱ መባረርህ ነው አልኩት ማስጠንቀቂያ በሚመስል መልኩ።

አረ ኤልዱ አባትሽ እራሱ ነው ወጣ አድርጌ እንዳዝናናሽ የነገረኝ እንጂ በምን ድፍረት መጥቼ እጠይቅሻለሁ አለኝ።

ተአምር ሆነብኝ አባቴ ቤት ስላልነበር ደውዬ ጠየኩት።
አው የኔ ልጅ ወጣ ብለሽ ተዝናኚ እኔ ቤት ስለሌሁ እንዳይደብርሽ ብዬ ነው ፈቅጄልሻለሁ አለኝ።

እንዴት እንደተናደድኩ እኔና ፈጣሪ እናውቃለን ብቻ አልወጣም ሂድ አይባል ነገር ሆኖብኝ ልብሴን እንደነገር እንደነገሩ ለብሼ ወጣሁ እናቴ በጣም ደብሯት ነበር የሆነ ደስ ያላለኝ ነገር አለ ከዛሬ ጀምሮ አባትሽን አወራውና ከቤት መውጣት የለም የምን ቅዳሜን እሁድን እየጠበቁ መገባበዝ ነው አለችኝ ለብቻዬ ጠርታ..........


ክፍል 5 ከ 100 like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

                 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
      
https://t.me/+cRqtf_gOk54zYmU8


             


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ ብዙዎቻችሁ የተጀመረው ታሪክ ይቀጥል ብላችዃል እንቀጥላለን ይቀየር ያላችሁ በሌላ ቻናል ሌላ ታሪክ እንጀምራለን ታገሱን


ቤተሰብ የተጀመረውን ታሪክ ላይክ እያደረጋችሁ አደለም አልወደዳችሁትም ወይ?
ይቀጥል 👍
ይቀየር ✍


       ❤️ኤልዳና 💗   

ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ

         
    ክፍል 2

✍ፀሀፊ ማኔ


የዛን ምሽት ሳናወራ አደርን ጠዋት እንደተነሳሁ ከሱጋም ከኔጋም ደለትኩት ቴሌግራም ውስጥ ከሁለቱ የሴት ጓደኞቼና ከዴቭ ውጪ ማንንም አላወራም ።
ስልኬን ሁላ ሁለቱ የክላሴ ልጆችና ቤተሰቦቼ ከዛ ውጪ ዴቭ ብቻ ነው የሚያቀው መደዋወል መፃፃፍ social media መከታተል የሚባሉት ነገር ላይ ብዙም ጎበዝ አደለሁም።

ከክላስ ተማሪዎቼ ውስጥም ቢሆን ማንም ደፍሮ ሊያናግረኝ የሚሞክር የለም።

ማታ ላይ ከዴቭጋ  በደንብ ለመግባባት ይረዳን ዘንድ የተወሰነ ነገር እናወራለን 4 ሰአት ሲል ሰአቴን ጠብቄ እተኛለሁ።

የሰአት አጠቃቀሜ እንዴት ነበር መሰላችሁ ጠዋት ትምህርት ቤት እሄዳለሁ።
ከትምህርት እንደተመለስኩ ልብሴን ቀያይሬ መክሰሴን በልቼ ከናቴጋ አወራለሁ።

12 ሰአት ሲሆን ክፍሌ እገባና እስከ 2 ሰአት የቤት ስራዎቼንና ጥናቴን እጨራርስና 2 ሰአት ላይ እራት ለመብላት ወደሚጠብቁኝ ቤተሰቦቼ ሄጄ እራቴን እበላለሁ።
አባቴ ቀኑን ሙሉ ስራ ስለሚውል ከእራት ቡሀላ ነው ከሱጋ የማውራት እድል የማገኘው ።
እሱን እንደጨረሰኩ ወደክፍሌ ገብቼ tv እያየሁ 4 ሰአት ሲሆን እተኛለሁ።

ብቻ life እንደዛ ነበር እላችኋለሁ።

ያው በነጋታው ቅዳሜ ስለነበር እቤት ዋልኩኝ።

እሁድ ለምን እንደሆነ ባይገባኝም ዴቭ እቤት መጥቶ ነበር በጣም ትልቅ ጥያቄ ሆነብኝ አባቴ አደለም ቀርቶ የውጭ ሰው ዘመዶቻችን እንኳን ሲመጡ ደስ አይለውም ዘመድ እኛ ቤት መጥቶ ሲጫወት በአል ሲያከብር አይቸ አላቅም እኔና እናቴም ብንሆነ የቤቱ እስረኞች ስለሆንን ቤታችን ውስጥ ገባ ወጣ የሚበዛበት አይነት ቤተሰቦች አደለንም።

ታዲያ የዴቭ ቤት መምጣት ግርምትን የፈጠረብኝ ለዛ ነበር።
እናቴን እንዴት መጣ ብዬ ጠየኳት እኔጃ ልጄ ብቻ ግን ጥሩ ልጅ ይመስላል ልብሶቹም ብራንድ ናቸው እራሱን በጣም ይጠብቃል  ተቀጥሮ ሚሰራ ሹፌር አይመስልም አለችኝ እሷም።

ጥያቄዬን በጥያቄ ስትመልስልኝ ዝም አልኩኝ።

ከዴቭ በጣም ከሚገዛኝ ነገሩ ዝምታውን እወድለታለሁ ፊቱ ላይ የሚታየው እርጋታ ቀልብን ይገዛል ብቻ ብዙም ሳያወራ አባቴ ያወራውን ሲያዳምጥ ወደማታ አካባቢ ላይ ካባቴጋ ተያይዘው ወጡ።

ሰኞ ውጤት ለማየት ትንሽ ጓጉቼ ስለነበር ቀስቃሽ ሳያስፈልገኝ በጠዋት ተነስቼ ለባበስኩ ቀድሜ ጨራርሼ ዴቭ እስኪመጣ መጠበቅ ጀመርኩ።

ሲመጣ ተነስቼ ወጣሁ። ትምህርት ቤት እስክንደርስ ካለወትሮው በጣም እያሳቀኝ ነበር።
ክላስ ስገባ እያሱ ቀድሞ ገብቶ ቁጭ ብሉ ደብተሩን እያገላበጠ ነበር።

ስገባ ቀና ብሎ አይቶኝ ፊቱን ቋጠረብኝ።
ዝም ብዬ ሄጄ ቦታዬ ላይ ተቀመጥኩ።
ሁሉም አስተማሪ ፈተናዎቻችንን የሚሰጡበት ቀን ነበርና የገባው ሁሉ ውጤት እየተናገረ ይሰጡን ጀመር በሚገርም ሁኔታ ሁሉንም ፈተናዎች ከፍተኛ ውጤት ያመጣው እሱ ነበር አይገርምም ለመጀመሪያ ጊዜ ክላስ ውስጥ የሚበልጠኝ ተማሪ ተገኘ።
መናደድ ሲገባኝ እኔ ግን ደስ አለኝ እንዴት ስለበለጠኝ ደስ እንዳለኝ አላውቅም ግን ውጤቶቹን ሳያቸው ደስ ይላል የበለጠኝም አንድ ትምህርት ብቻ ነው ያውም በአንድ ነጥብ።


ክፍል 4 ከ 100 like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

                 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
      
https://t.me/+cRqtf_gOk54zYmU8


             


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ ኤልዳና ክፍል 3 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


       ❤️ኤልዳና 💗   

ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ

         
    ክፍል 2

✍ፀሀፊ ማኔ


ያደረገው ጫማ ያምራል ፀጉር ስታይሉ ደስ ይላል።
ማንንም ቀና ብሎ አያይም ከአስተማሪዎቹ ውጪ ማለቴ ነው።
አየሁትና በቃ እንደኔ ነው ማለት ነው አልኩኝ።
እኔ አንዴ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ከገባሁ ቡሀላ ከማንምጋ አላወራም አልስቅም ኮስተር ብዬ ቁጭ ነው ሁለት ልጆች አሉ ጓደኞቼ ናቸው ለማለት ቢከብደኝም የተወሰነ ግን ከሌሎቹ ተማሪዎች ቀተለየ እቀርባቸዋለሁ ማለት እምችለው እነሱን ብቻ ነው ።
ሌሎች ተማሪዎች እሷ ሀብታም ስለሆነች ሰው ስለምትንቅ ነው ከኛጋ ማታወራው ይላሉ እኔ ግን የምኮሳተርበት ምክንያት መጃጃል ስለሚያስጠላኝ ነው ከቀረብኳቸው መናናቅ ይመጣል ብዬ አስባለሁ ቁጥብነቴን እወደዋለሁ።

እቤት ውስጥ እንደኔ የሚያስቃቸው የለም ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ስገባ ግን እንኳን ሰውን የማስቅ ለራሴ ስቄ ማውቅ ሁላ አይመስላቸውም።
ድንገት የሚያስቀኝ ነገር ቢፈጠር እንኳን ሳቄን ዋጥጥ አድርጌ ካለፈ ቡሀላ አጎንብሼ ሁላ ልስቅ እችላለሁ።

ብቻ የዛን ቀን ልጁ አንድ ቦታ ላይ stack እንዳደረገ ወደቤት ሰአት ተደወለና ወጣን።
ዳዊት በር ላይ እየጠበቀኝ ነበር ወደመኪናው ገባሁኝና እየተመለስን ምን እንደሚያወራ የጨነቀው ይመስል አስሬ አየት አየት እያደረገኝ ተጫወች ተጫወች ይለኛል።

ትምህርቱ እንዲህ እንዲያ እያለ ሁለት ወር ሞላን አንድም ቀን ከልጁጋ አውርተን አናቅም በጣምም ጎበዝ ተማሪ ነው የገባ አስተማሪ ሁላ ይወደዋል ግን ፊቱ አይፈታም በጣም ዘናጭ ነው የክላስ ተማሪዎች በተለይ ሴቶቹ ሊግባቡት ይሞክራሉ እሱ ጭራሽ ቼክ አያደርጋቸውም ዝምም እንዳለ ነው።

አስተማሪ ሲገባ ሲጠይቁት መልስ ሲሰጥ ባንሰማው ሁላ ሁላችንም ማውራት አይችልም ብለን ምንደመድም ይመስለኛል።

አልፎ አልፎ ሰርቅ አድርጎ ሲያየኝ አይን ለአይን እንገጣጠምና እደነግጣለሁ።

ፈተና ሊደርስ አካባቢ እኔ በጣም በጥናት ተወጥሬ ነበር እንደክላስ የተከፈተ  ግሩፕ አለ።

እዛ ግሩፕ ላይ ወርክሽቶችና ለፈተናው የቀረቡ የቀረቡ ጥያቄዎች ይለቀቁልንና እንሰራለን።

እነሱን ወርክሽቶች ለማየት ቴሌግራም ገባሁኝ።
hi የሚል text ተልኮልኛል ግን ምንም ግድ አልሰጠኝም ከማን እንደሆነ ሁላ አላየሁትም የተለቀቁትን ወርክሽቶች ብቻ አውርጄ ወጣሁ።

በነጋታው ፈተና ነበርን ዴቭም እስከትምህርት ቤት ካደረሰኝ ቡሀላ መልካም ፈተናን ተመኝቶልኝ እንደጨረስኩ ምሳ ሚጋብዘኝ እሱ እንደሆነ ነግሮኝ እኔም ተስማምቼ ሄደ።

ክላስ ገብተን የጠዋቱን ፈተና ከጨረስኩ ቡሀላ  ከዳዊትጋ ምሳ በላን የወሰደኝ ቦታ ሚገርም ቤት ነበር ።
አሰብኩትና አሳዘነኝ እሱ ሹፌር አደል እንዴ ለምሳ ብቻ እንዴት ይህን ሁሉ ብር ይከፍላል ይሄኔኮ የሀብታም ልጅ ናት ትልልቅ ቦታ ካልሆነ አትበላም ብሎ ሼም ይዞት ይሆናል ይሄን ሁሉ ብር የሚያወጣው ብዬ አሰብኩ።

ምሳ ከበላን ቡሀላ ወደ ክላስ ገባሁኝ የከሰአቱን ተፈትኜ ወጣሁ።
ሳምንቱን ሙሉ ተመሳሳይ ቀን አሳለፍኩ።

ፈተና የጨረስን ቀን ማታ ላይ ዝም ብዬ tg ገባሁ።

ምነው ዘጋሽኝ የሚል tfxt ገባልኝ ማነው ሚጃጃለው ብዬ ፕሮፋይሉን ለማየት ገባሁ።

ለምን እንደሆነ አላውቅም ግን ልቤ ለሁለት ነበር ክፍል ያለው ፎቶዎቹ ስታይሎቹ በጣም ያምራሉ ከአንዴም ሁለት ሶስቴ እየደጋገምኩ አየኋቸው ብቻዬን ፈገግ እያልኩ ይሄ ልጅ ግን በደንብ አይቼውኮ አላውቅም እንደዚህ ቆንጆ ነው እንዴ አልኩኝ።

ልመልስለት አልመልስለት ከራሴጋ ክርክር ጀመርኩና ሳላስበው ho ብዬ ላኩኝ።

ኦኦ እሺ በጣም ይቅርታ ጨቀጨኩሽ መሰለኝ በድጋሜ ይቅርታ ብሎ ላከልኝ።

አረ ችግር የለውም የምን ይቅርታ ነው ተሳስቼ ሆ ያልኩህ እንዴት ነህ አልኩት።
ደና ነኝ አንቺስ እንዴት ነሽ ኩራቱስ እንዴት እያረገሽ ነው አለኝ።

እእ የምን ኩራት ??
ያው ግቢ ውስጥ ካሉ ልጆች ኩራተኛዋ አንቺ ነሽ ብዬ ነው አለኝ።

አረ እኔ ኩራተኛ ከተባልኩ አንተ ምን ልትባል ነው ፊትህ ሁላኮ አይፈታም አልኩት።

አረ ባክሽ ለማንኛውም እያሱ እባላለሁ የክላስሽ ልጅ ነኝ አለ።
አውቄሀለሁ እኔ ደሞ ኤልዳና እባለለሁ።

ስላወኩሽ ደስ ብሎኛል አለኝ።
እሺ አልኩት።

ከዚህ በፊት ከዴቭ ውጪ ቴሌግራም ላይ ማንንም ወንድ አውርቼ አላውቅም እና ሁለቱ የትምህርት ቤት ጓደኞቼ ናቸው ባይባልም ግን ያው ጓደኞቼ ልበላቸው ብቻ ከነሱ ውጪ ማንንም አላወራም።

ሲጀመርም ከስንት ቀን አንዴ ቴሌግራም ብገባ ነው እንጂ የመፃፃፍ ልምድ የለኝም ከማንጋ አውርተሽ ይኖርሻል በሉኝ እንጂ።


ክፍል 3 ከ 100 like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

                 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
      
https://t.me/+cRqtf_gOk54zYmU8


             


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ ኤልዳና ክፍል 2 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


       ❤️ኤልዳና 💗   

ልብ አንጠልጣይ የ ፍቅር ታሪክ

         
ክፍል 1

✍ፀሀፊ ማኔ

ሰላም ኤልዳና እባላለሁ።
ዛሬ እስቲ ከኖርኩት በትንሹ ላካፍላችሁ አሁን ላይ ወደኋላ ዞር ብዬ ታሪኬን ሳስበው ከኖርኩት በላይ ሳወራው እየደከመኝ ተቸግሪያለሁ ።

ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ ነው ቤተሰቦቼ የሀብታም ልጥጥ ከሚባሉት ውስጥ ናቸው።

ከልጅነቴ ጀምሮ የጠየኩት ሁሉ እየተሟላልኝ ተሞላቅቄ ግን ደሞ ሴትነትንና ጨዋነትን ከስነምግባርጋ ተምሬ ነው ያደኩት።

የቤቱ ብቸኛ የአይን ማረፊያቸው እኔ ነኝ።
ቤት ውስጥ እኔ አባቴና እናቴ ከሰራተኛችንጋ 4 ሆነን ነው ምንኖረው ።

የኔ ስራ መብላት መጠጣት መማር ብቻ ነው ከዛ ውጪ ጭንቅላቴ ውስጥ ስለሌላ ነገር ሀሳብ መጥቶልኝ አያውቅም።

ታሪኬ የሚጀምረው 8 ሚኒስትሪ ተፈትኜ በሚገርም ውጤት ሰቅዬ ወደ ዘጠኝ ካለፍኩ ቡሀላ ነው።

ትምህርት ሊጀመር ቀናቶች ሲቀሩት ትምህርት ቤት የሚያደርሰኝና የሚመልሰኝ ሹፌር እየፈለገ እንደሆነ አባቴ ነገረኝ።

አዲስ ስራ ስለጀመረ  በዚህ አመት ብዙ ጊዜ እዚህ ስለማይሆን ሹፌር መቀጠር እንዳለበት ነገረኝ እሺ አልኩት።

መስከረም 18 የመስቀል ማግስት  ትምህርት ለመጀመር ዝግጅት እያደረኩ ነበር።
እኔ ሁሌም ክረምት ላይ ትምህርት ከተዘጋ ቡሀላ መስከረም መጥቶ ትምህርት ሊጀመር ሲል በጣም ያስጠላኛል አንዴ እስክጀምር ለኔ ፈተና ነው አንዴ ከጀመርኩ ቡሀላ ግን በቃ መቅረት ሚባለውን ነገር አላስበውም እኔጃ ብቸኛ ተማሪ እኔ ሳልሆን አልቀርም የለም አትምጡ ቢሉኝ እራሱ ትምህርት ቤት ደርሼ አረጋግጬ ምመለስ ይመስለኛል።

ቁርሴን በላላሁና ከቤታችን ፊት ለፊት ወደ አለው ፀጉር ቤት ሄድኩኝ ።ደንበኛዬ ናት ገና ስደርስ ውዬ ኤልዱዬ የኔ ቆንጆ መጣሽ አረፍ በይ አለችኝ ከሌሎች ሰዎች ቅድሚያ ሰጠችኝና እራሴ ነኝ ምሰራሽ አለችኝ።
ያንቺን ፀጉር መስራትኮ በራሱ ደስታን ይሰጣል ነይ እዚጋ ምን መሰራት ነው የፈለግሽው አለች ከመስታወት ፊት ለፊት ቁጭ ብዬ እራሴን እያየሁት ከፊት ለፊት መቆረጥ ፈልጌ ነበር አልኳት።

ደነገጠች አረ ኤልዱ አታደርጊውም ይሄን የመሰለ ፀጉር መቀስ ልታስነኪው ነው ይሻላል ብለሽ ነው አለችኝ።

እውነት ለመናገር እኔ ያን ያህል የተጋነነ ፁጉር እንደማልወድ ታቂያለሽ ሰው ያለውን ሳይሆን የሌለውን ስለሚፈልግ ይሁን ወይ ለምን እንደሆነ አላውቅም ግን አጭር ፀጉር  ሳይ ደስ ይለኛል ሙሉውንም የማልቆረጠው እናቴ ፀጉሬን በጣም ስለምትወደው እሷን ላለማስደበር ብዬ እንጂ ሙሉውን ብቆረጠው እራሱ ደስ ይለኛል አሁን ከፊት ለፊት ቁረጭልኝ አልኳት።
እሺ በቃ አዴ እንደፈለግሽ ብላ ሰራችኝ ተስተካክዬ ስጨርስ ወደቤት ሄድኩ።
ለነገ ለትምህርት ቤት የሚያስፈልጉኝን እቃዎች ሙሉ እናቴና ሰራተኛችን ፅጌ ትባላለች አዘጋጅተው ጠበቁኝ።

በነጋታው ፅጌ መጥታ ቀሰቀሰችኝና ተነሳሁ እየደበረኝም ቢሆን ተነስቼ ለባበስኩ ሹፌር እስኪገኝ አባቴ ነው ትምህርት ቤት የሚያደርሰኝ።
አደረሰኝና መልካም ቀን ተመኝቶልኝ ተመለሰ  ትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ ስገባ ጀምሮ አስጠላኝ እየደበረኝም ቢሆን ወደ ክላሴ ገባሁ ክላስ ከገባሁ ቡሀላ የ8ኛ ክፍል ጓደኞቼን ሳገኝ ትንሽ ቀለል አለኝ።

በነገራችን ላይ የልቤ የምለው የምቀርበው የልብ ጓደኛ እንኳን አልነበረኝም ከናቴ ውጪ።

መጀመሪያዎቹ ሳምንቾች መምህሮችና ተማሪዎች የሚተዋወቁበት ጊዜ ስለሆነ ያን ያህል ትምህርት አልተጀመረም ነበር።

ሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ ላይ እኔም ትምህርት መሄዱን እየለመድኩት ሹፌርም ተቀጥሮልኝ አዲሱን ሳምንቴን ከሱጋ እንደምጀምር ተነግርኝ በጠዋት ተነስቼ ለባብሼ ወጣሁ።

መኪና ውስጥ ከመግባቴ በፊት አባቴ ተዋወቂው አዲሱ ሹፌርሽ እሱ ነው መልካም ልጅ ነው ካንቺጋም እንደምችስማሙ ተስፋ አደርጋለሁ አለኝ።

ሰላም ኤልዳና እባላለሁ አልኩት ዳዊት እባላለሁ አለኝ መኪናውን ከፍቶ አስገባኝ።

ዳዊት እንደጠበኩት አልነበረም ገና ወጣት ነው ተግባቢም ይመስላል ጀነን ያለ አይነት ነው መልኩ ያን ያህል ቆንጆ ባይባል የሚያሳፍር አይነት አደለም ካባቴጋ የተወሰነ ቆመው ካወሩ ቡሀላ ወደ መኪናው ገባና መንገድ ጀመርን።

እኔም ዝም እሱም ዝም አልን የሆነ ሰአት ላይ ወሬ ለመጀመር ይመስል ፀጉርሽ ያምራል የራስሽ ነው ወይስ ገዝተሽው ነው አለኝ።
ፈገግ አልኩና አይ የራሴ ነው አልኩት።
እሺ ያምራል በጣም ቆንጆ ፀጉር አለሽ አለኝ።
አመሰግናለሁ።
ከዛ ዝምምም እንዳልን ትምህርት ቤት ደረስኩና አውርዶኝ መልካም ቀንን ተመኝቶልኝ ሄደ።

ወደ ክላስ ገባሁኝ እኔ ከምቀመጥበት ወንበር ፊት ለፊት ሳምንቱን ሙሉ ያላየሁት ከዚህ በፊትም የማላቀው አዲስ ልጅ ተቀምጧል።

አቤት አኮሰታተር ጭራሽ ከተፈጠረ ስቆ ሚያቅ አይመስልም


ክፍል 2 ከ 100 like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like ❤️ማድረግ አይርሱ።

                 ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
      
https://t.me/+cRqtf_gOk54zYmU8


             


ምሺት 2:30 እሚጀመር ታሪክ አለ ዝግጁ ናችሁ ?

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.