Click Ethiopian Laws:- by Mastewal dan repost
የገጠር ባዶ መሬት ሽያጭ ዉል ህገ ወጥ ድርጊት በመሆኑ በመርህ ደረጃ ዉሉን ተከትሎ የተሰሩ ስራዎች ምንም አይነት ህጋዊ ውጤት ባይኖራቸውም ነገር ግን መሬቱን የገዛው ሰው በመሬቱ ላይ ያለማቸው አትክልቶች ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚሰጡ እንደ ቡና፣ ጫት፣ አቡካዶ፣ ፓፓየ፣ ማንጎ፣ ብርቱካን፣ አፕል፣ ዘይቱና፣ እንሰት፣ ግሽጣና ሙዝ የመሳሰሉ ተክሎች ከሆኑ ተቆርጠውም ጥቅም የማይሰጡ ስለሆኑ በልዩ ሁኔታ ገዢው አትክልቶቹን ለማልማት ያወጣቸውን ልዩ ልዩ ወጪዎቺ ባለመሬቱ እንዲተካ ማድረግ የሚገባ እንጂ ቆርጦ እንዲያነሳ ሊወሰን የማይገባ ስለመሆኑ፣ በመሬቱ ላይ የተሰራው ቤት ከሆነ ግን ገዢ የሰራውን ቤት አፍርሶ መሬቱን ሊያስረክብ የሚገባ ስለመሆኑ የተሰጠ ውሳኔ