የ ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ዲጅታል ቤተ-መጽሐፍ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Kitoblar


ይህ የተለያዩ መንፈሳዊ መጻሕፍት የሚጋሩበት የ ቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ዲጅታል ቤተ-መጽሐፍ ነው።
ለመወያየት : ለገንቢ ሀሳባት እና ለመጻሕፍት ጥቆማ @timbri7 እንዲሁም @YNSel

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


አዲሱን ዓመት እንዴት እንጀምር.pdf
1.7Mb
በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ




✝ ሰላም ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት ሰነበታችሁ ✝

💫 እግዚአብሔር ወዶ እና ፈቅዶ እስከ ዛሬዋ እለት የነበረንን የዲያቆን ሄኖክ ሀይሌን የብርሃን እናት የተሰኘውን መፅሀፍ የንባብ challenge በዛሬው እለት አጠናቀናል።

🌷 እግዚአብሔር ይመስገን 🌷

አብራችሁን ለነበራችሁ ውድ አንባቢያን እንዲሁም አድማጮቻችን በሙሉ በቅዱስ ጴጥሮስ ግቢ ጉባኤ ቤተ መፅሐፍት ክፍል ስም እግዚአብሔር ይስጥልን




የብርሃን እናት የመጨረሻዎቹ ገፆች .pdf
3.4Mb
•
•
•
🌷🌷የዝምተኛዋ ንግግሮች🌷🌷




የብርሃን እናት ከገፅ 340-375.pdf
3.0Mb
🌹የጻድቃን ቀጠሮ🌹
•
•
✨️ ብፅዕትና ብፁዓን
✨️ነቢይት ማርያም
✨️የዝምተኛዋ ንግግሮች..


🌺🌺🌺የብርሃን እናት🌺🌺

🌹🌷ቅምሻ🌺🌷🌷
አንዳንድ አሳዛኝ ሰው ድንግል ማርያምን 'አንደ እኔ ሰው እኮ ናት' የሚል ምክንያት በማቅረብ ከእርሱ በምንም የማትለይ እንደሆነች ሊከራከርና ክብርዋን ሊያሳንስ ይሞክራል፡፡ ወዳጄ እውነት አንተ እንደ እርስዋ ነህ? ብርሃናዊ መልአክ ከፊትህ ቆሞ አመስግኖህ ያውቃል? እንኳንስ ከሰማይ የተላከ እንግዳ መልአክን ቀርቶ አብሮህ ያለውን ጠባቂ መልአክህንስ አይተኸው ታውቃለህ? እንደ ድንግሊቱ የመላእክትን ዝማሬ ከሆድህ ውስጥ ሰምተሃል? እግዚአብሔር እንኳንስ በእንተ
ሊያድር በሕልም እንኳን አነጋግሮህ ያውቃል? እውነቱን ንገረኝ ካልከኝ እንኳን ሊወለድብህ በቃል ሊያነጋግርህም አልመረጠህም፡፡
በዚህ ትዕቢትህ ከጸናህ ደግሞ ለሰማዩም እፈራልሃለሁ፡፡ በሰማይ በእግዚአብሔር ፊት ቁም ብትባል ስለድንግሊቱ አሁን የተናገርከውን
ነገር በፊቱ ደግመህ ትለዋለህ? እግዚአብሔርን 'አናትሀ ከእኔ በምንም አትበልጥም" - ልትለው - ትደፍራለህ? በክንፎቻቸው ተሸፍነው የሚያመሰግኑት በንጽሕናቸው ወንድሞችዋ የተባሉ ኪሩቤልና ሱራፌል እንኳን እንዲህ ሊሏት አይደፍሩም፡፡ ይህ ዓይነቱ አነጋገር እግዚአብሔር
'በውኑ ባሪያዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ አገደ አርሱ ፍጹምና ፥ አግዚአብሔርንም የሚፈራ፣ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም' ብሎ ሲነግረው እግዚአብሔር ደስ የተሰኘበትን ጻድቅ ሰው የኢዮብን ከብር ለማሳነስ ምክንያት ከደረደረው ከዲያብሎስ ንግግር ጋር ተመሳሳይ
ነውና አስተውለህ ተናገር፡፡




የብርሃን እናት ከገፅ 308-340.pdf
2.6Mb
🌹የጻድቃን ቀጠሮ🌹
•
•
✨️ መዝሙረ ድንግል
✨️ያመነች ብፅዕት


🌺🌺🌺🌺የብርሃን እናት🌺🌺🌺

🌹🌹ቅምሻ🌹🌹

ድንግል ማርያም ለእርስዋ የተደረገላትን ለኤልሳቤጥ ከተደረገው ነገር ጋር አላነጻጸረችም፡፡ 'ኤልሳቤጥ ካረጀች በኋላ መፅነስዋ ምን ይገርማል? አኔ ያለ ወገድ ዘር የፀነሰሁ አይደለሁምን? ኤልሳቤጥ የልጅ እናት ልትሆን መብቅትዋስ ምን ይገርማል? አኔ የአምላክ እናት ልሆን አይደለምን?" ብላ ሳትኩራራ የኤልሳቤጥን ታናሽ ደስታ ልትካፈል ተነሣች፡፡ በብርሃናዊ መልአክ 'ደስ ይበልሸ' የተባለችው ድንግል በማግስቱ አንዲትን ሴት 'ደስ ይበልሽ' ልትል ጉዞ መጀመርዋ ምንኛ የሚያስደንቅ ነው? 'ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሸ የተባለላት ድንግል ከእርስዋ የምታንሰውን ከሴቶች አንዲቱን ልትጎበኝ መቸኮሏስ ምንኛ ድንቅ ነው?




የብርሃን እናት ከገፅ 286-308.pdf
2.0Mb
✨️ምዕራፍ ፬✨️
🌹የጻድቃን ቀጠሮ🌹

🔶 ፈጥና ወጣች
🔶 ያልተወለደው ባለቅኔ




የብርሃን እናት ከገፅ 257-286.pdf
2.5Mb
🌹ምዕራፍ ፫🌹

☀ከፀሐይ አጠገብ የነበረው ኮከብ✨️


.....በእውነት ይህች ድንግል ስለእርስዋ 'ታማልዳለች ወይስ አታማልድም' በሚል ተራ ክርክር ላጠፋነው ጊዜ ይቅር ትበለን፡፡ ወዳጄ የአንተን ጊዜያዊ ችግር ለመፍታትስ ማንኛውም ተራ ሰው  ሊጸልይልህ ይችላል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ለሁላችን 'ምልጃ ይደረግ ሰለ አናንተ ሲያማልዱ ይናፍቋችኋል ክፋት ሲናገሩን አንማልዳለን ብሎ እርስ በእርሳችን አንዳችን ለሌላችን ልንማልድ እንደምንችል ጽፎአል፡፡ መቼም አብዛኛው ጥያቄያችን ከሥጋ አያልፍምና ደህና ገንዘብና ሥልጣን ያለውም ሰው የአንተን ችግር ለመፍታት አያንስም፡፡ 'ይሁንልኝ' የሚል የእምነት ቃልዋን ተናግራ ሰማይና ምድርን በማሕፀንዋ ያስታረቀች የእግዚአብሔር ውድ ፍጥረት ድንግል ማርያም አንተን አማልዶ ማስታረቅ ትልቅ ነገር የሚሆንባት ይመስልሃል?
✨እውነት ለመናገር ለእኛ ተራ ጉዳይ 'አታማልድም' ብሎ መወዛገብ ቀርቶ 'ታማልዳለች'" ብሎ መናገርም ከክብርዋ ጋር የማይመጥን ተራ መልስ ነው፡፡ ስለ ሌሎች ጻድቃን እንኳን 'የጌታ ዓይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው ፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው ተከፍተዋል' ተብሏል፡፡ ድንግል ማርያም ግን እናት ለልጅዋ እንደምታወራ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ በእቅፍዋ ይዛ በጆሮቹ የእናትን የፍቅር ቃል ያፈሰሰች ናትና ከየትኛውም ሰው ድምፅ በላይ የእርስዋ ቃል ለፈጣሪ ጆሮ ጣዕም ያለው ነው፡፡
ከ" የብርሃን እናት " መጽሐፍ የተወሰደ




የብርሃን እናት ከገፅ 232-257.pdf
2.3Mb
🌹የምሕረት አዋጅ🌹
                 •
                 •
                 •
    🌸የፍጥረት ናፍቆት




የብርሃን እናት ከገፅ 208-232.pdf
1.9Mb
🌹የምሕረት አዋጅ🌹
                 •
                 •
                 •
    🌸የአብርሃም ድንኳን

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.