© Eyob Mihreteab Amlesom
#ተፃፈ: 02 March 2023
[ኒኮላይ ስቴፋኖቪች ሊዮንቴቭቭቭ!]
∞ ∞ ∞ ∞ ∞ ∞ ∞
.
ቦምብም ወረወሩ፣ መትረየስ ደገኑ
አሉ ጋደም ጋደም፣ አሉ ጎንበስ ጎንበስ
አውሬ መስያቸው፣ አውሬ መስያቸው
ከሠው መፈጠሬን፣ ማን በነገራቸው
ቆርጬ ስነሳ፣ ቆርጬ ስነሳ ልበኔን ሳነሳ
ይፈሩኝ የለም ወይ፣ እንደ ዳልጋ አንበሳ
.
-
.
. [ጌታዬ]
እኛ እኮ በአድዋ ድል የምንኮራው፣ የምንመካው፣ አውርተን አውርተን፣ ተናግረን ተናግረን፣ ተደንቀን ተደንቀን፣ ተመክተን የማንጨርሰው በ'ዘራፍ ዘራፍ'፣ በ'አሉ ምናሉ' ሳይሆን የሚነበብ #አንብበን፣ አገናዝበን፣ አሠናስለን አወራርደን፣ የዚህን ዓለም የያኔና የአሁን ሁናቴ ጠንቅቀን አውቀን ነው፡፡
-
[እስኪ ይሄንን አንብብና አንተነትህን ውደደው። ቀንህን ምሉዕ አድርገው]
-
የዋሺንግተን ዩንቨርሲቲ የታሪክ ፕሮፌሰር የሆኑት Raymond Jonas ስለ አድዋ የጻፉት ታዋቂ መጽሃፍ አላቸው፡፡ ርዕሱም ‘The Battle of Adwa: African Victory in the Age of Empire’ ይላል፡፡
ኦሪጂናሉን ቨርዥን በዶላር ሂሳብ ከመግዛት አድዋ ሄዶ መዋጋት ይቀላል ብዬ ትቼው ነበረ፡፡ Muluken Tariku የተባለ ወሳኝ ሰው ተርጉሞት 100 ብር ገዛሁት፡፡
እንገርበው እስኪ፡፡
.
-
.
#ሀ
[ለመሆኑ፣ አድዋ ለኦሮሞው ምኑ ነው?]
“የጣልያን ሠራዊት በመገስገስ ላይ የነበሩትን የኦሮሞ ፈረሰኞች በተመለከተበት ወቅት የሚገባበት ጠፋው፡፡ ቀድሞ በሠራዊቱ ውስጥ ስለ ኦሮሞ ፈረሰኞች የተነገራቸው ኋላ ቀር እና ተራ ተዋጊዎች እንደሆኑ ነበር፡፡ በጦር ሜዳ ላይ የተመለከቱት ግን ፈረሰኞቹ እጅግ የተካኑ መሆናቸውን ነው፡፡
የጀነራል አርሞንዲ የበታች ከሆኑት መሃል ጂዮቫኒ ቴዶኒ ለሠራዊታቸው መሸነፍ ቁልፍ ሚና የተጫወቱት የኦሮሞ ፈረሰኞች መሆናቸውን መስክሯል፡፡ የወቅቱን አስፈሪ ሁኔታ ሲገልጽም “ፈረሰኞቹ ወደ ሸለቆው ሲወርዱ በድንገት የገነፈለ ጥቁር ባህር ይመስሉ ነበር” ብሏል፡፡
በርካታ የጦር መሪዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል፡፡ ሌተናል ኮሎኔል ጋሪባልዲ ፔናዞ እና ሌ/ኮ ማዞሊኒ የኦሮሞ ፈረሰኞችን ጦርና ጎራዴ በመፍራት በራሳቸው ሽጉጥ ራሳቸውን አጥፍተዋል፡፡”
(ገጽ- 195/196)
.
-
.
#ለ
[ከድል በኋላ ዓለም ምን አለ?]
“የምኒሊክ እና የጣይቱ ዝና በሠፊው መናኘቱን ተከትሎ የተለያዩ አዳዲስ ክስተቶች ታይተዋል፡፡ በርካታ አውሮፓውያንም አዳዲስ ለተወለዱ ልጆቻቸው “ምኒልክ” የሚል ስም ሰጡዋቸው፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአድናቆት ደብዳቤዎች የምኒሊክን ቤተ-መንግስት አጣበውት ነበር፡፡ አንዳንድ ደብዳቤዎች ንጉሱን የገንዘብ ውለታ የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ አንዲት አድናቂያቸው በጻፈችላቸው ደብዳቤ አፄ ምኒልክ ለጅምር ቤቷ ማስጨረሻ የሚሆን 200 ፍራንክ እንዲልኩላት ጠይቃቸው ነበር፡፡”
(ገጽ 218)
.
-
.
#ሐ
[ጥልያንስ ምን አለ?]
“የጣልያን ሕዝብ ለድጋፍና ለተቃውሞ እጅግ ፈጣን ነው፡፡ ጦራቸው በ1895 ራስ መንገሻን ሲያሸንፍ ከፍተኛ የድጋፍ ሰልፍ አድርገው ነበር፡፡ በአምባላጌ፣ መቀሌ እና አድዋ አውደ ግምባሮች ሽንፈት ያጋጠመው ጦራቸውን ለማውገዝም ጊዜ አልፈጁም፡፡ የሮም ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የተቃውሞው ዋና መሪ የነበሩ ሲሆን “ቪቫ ምኒልክ” የሚል መፈክር ይዘው ነበር ለሰልፍ የወጡት፡፡”
(ገጽ- 236)
.
-
.
#መ
[ወደ ገደለው፣ የአድዋ ቁልፍ ትርጉም ምንድን ነው?]
“የአድዋን ድል ተከትሎ አፄ ምኒልክ የአፍሪካ የምንጊዜም ታላቅ መሪነታቸውን በደማቅ ቀለም አስጽፈዋል፡፡ ድሉ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን መፃኢ እድል የወሰነ ነበር፡፡ በዚህም የአድዋ ጦርነት የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም ጭምር ነው፡፡ ምክኒያቱም በቀጣይ መቶ አመታት የአውሮፓ የበላይነት እና አገዛዝ በአፍሪካ አክትሟል፡፡ የዘመናዊት አፍሪካ የሉዓላዊነት መሠረት ድንጋይ የተጣለው አድዋ ላይ ነበር፡፡”
(ገጽ-244)
.
-
.
#ሠ
. [በመጨረሻም]
“ፈጣጣ ሁን፣ አትፍራ!” ይልሃል ኒኮላይ ስቴፋኖቪች ሊዮንቴቭ፡፡ ይሄንን ፀዴ ሠውዬ ተመልከትልኝ እስኪ!
[“ራሱን (በራሱ) የሾመው ዲፕሎማት”]
.
-
.
“ኒኮላይ ስቴፋኖቪች ሊዮንቴቭ በዩክሬን የተወለደ ሩስያዊ ነው፡፡ በወታደርነት ተቀጥሮ ሳለ የመጓዝ ልምድ ያካበተ ሲሆን በከፍተኛ ብድር ውስጥ በመዘፈቁ ከሩስያ በመውጣት ወደ ሌላ አገር ተጉዞ ሥራ ለመሥራት ይስናል፡፡ በመሆኑም ዕዳውን ለመሸሽ ከአገሩ በመውጣት በ1895 ወርኃ ጥር ላይ ወደ አዲስ አበባ ተጓዘ፡፡
በአዲስ አበባ ቆይታው ከአፄ ምኒሊክ ጋር በመገናኘት የሩስያ ንጉስ መልዕክተኛ መሆኑን ገለጸላቸው፡፡ በቆይታውም ከጥር 1895 ጀምሮ የሩስያ አምባሳደር በመሆን ራሱን ሾመ፡፡ በመቀጠልም አፄ ምኒሊክን አግባብቶ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችን በመያዝ ወደ ሞስኮ ተጓዘ፡፡
ህዳር 1894 ላረፉት ንጉስ አሌክሳንደር የመታሰቢያ ስጦታ እንዲሆን ከአፄ ምኒሊክ የተለያዩ የኢትዮጵያ ውድ ጌጣጌጦችን ለሞስኮው ንጉሥ ልከዋል፡፡ ሐምሌ 17 ቀን 1895 ልዑካኑ በፒየትሮቭ ቤተ-መንግስት አቀባበል ያደረጉላቸው ንጉስ ኒኮላስ ነበሩ፡፡
ልዑካኑ ፒተርስበርግ ሲደርሱ ከፍተኛ አቀባበል ተደርጎላቸው በንጉሱ ትዕዛዝ መሠረት በአገሪቱ ታላቅ በሆነው ሆቴል ዩሮፕ እንዲያርፉ ተደርገዋል፡፡አጋጣሚውን መጠቀም የቻለው ሊዮንቲቭ በንጉሡ ዘንድ ተመራጭ ሆነ፡፡ በመሆኑም ንጉሡ በኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አድርገው ሾሙት፡፡ ልዑካኑ ነሐሴ 9 ቀን 1895 የመልስ ጉዞአቸውን ሲጀምሩ 135 የቤርዳን ጠመንጃዎች በስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
ራሱን የሾመው ሊዮንቲቭ ምስጋና ይግባውና በአዲስ አበባ ከነበሩ በርካታ አውሮፓውያን መካከል የሩስያ ተወካይም እድል አገኘ፡፡
አፄ ምኒሊክ ወደ አድዋ ለመዝመት በሚዘጋጁበት ወቅት ሊዮንቲቭ ወደ አውሮፓ አቀና፡፡ በአውሮፓ ቆይታውም ኢትዮጵያን እና ጣልያንን ለመሸምገል ሞክሯል፡፡ ከጣልያን ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አልቤርቶ ዲ ብላንክ ጋር ያደረገው ውይይት ውጤት ስላላስገኘለት ድርድሩ ሳይሳካ ቀረ፡፡
ሊዮንቲቭ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰው ከጦርነቱ በኋላ ነበር፡፡ በወቅቱ አፄ ምኒሊክ ለጣልያኗ ንግስት ማርጋሪታ የልደት ስጦታ ይሆን ዘንድ 50 ምርኮኞችን በነፃ ለቀቁ፡፡ በመቀጠልም በሊዮንቲቭ አግባቢነት ለሩስያው ንጉስ በዐለ ሹመት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በወርኃ ሐምሌ ሌላ 50 ምርኮኞችን ለቀቁ፡፡”
(ገጽ 239-240)
-
ሠው ሞቷል ሠው ሊያድን
ሠው ሠውን ሲያከብር፡፡
-
እመነኝ፣ ከየትኛውም አፍሪቃዊ የተለየው ኩሩው ማንነትህ የተገነባው #በዛሬው_ቀን ላይ ነው፤ #አድዋ ላይ ነው፡፡
መልካም የድል በዓል