“80 000 ብር ናት ያለችኝ ኡምራ ማድረግ እፈልጋለሁ”
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
አላህ ይዘንለት ወንድማችን ሙሐመድ ሰኢድ በዘንድሮው ረመዳን መጨረሻ ኡምራ መሄድን ከመጠን በላይ ፈለገ። ብዙ ወንድሞችንም ይህንኑ አማከረ። “እረ እባክህ አንተኮ አቅም የለህም ዋጋውምኮ ውድ ነው አንተ ደሞ አቅም የለህም” አሉት። “በፍፁም” አለ ሙሐመድ። “ከረመዳን በኃላ ብትሄድ ይሻላል” ብለው ሊያግባቡት ሞከሩ። “አይሆንም የረመዷን መጨረሻዎቹን ቀናት ኡምራ ነኝ” አለ ፈርጠም ብሎ። “ምንድነው የመጨረሻህ አደረግከውኮ” ብለው ሲቀልዱበት “ያው በሉት” ብሎ መለሰላቸው።
ቪዛ ፍለጋ ለፋ ወጣ ወረደ። አልሀምዱሊላህ አላህ ፈቀደና ህልሙ ተሳካ። ሰዎች ገንዘብ ስላላቸው ብቻ ሳይሆን ሲጠሩ ብቻ ወደሚሄዱበት የአላህ(ሱወ) ቤት ሄደ። የሚወዳቸው የረሱላችን(ሰአወ) ሀገርን ረገጠ። ኡምራን ፈፅሞ መዲናን ዘይሮ ወደ ሀገር ቢመለስም በድንገተኛ ህመም ወደ አኸራ ሄዷል።
እውነትም የመጨረሻው ኡምራ ነበረች!
አላህ ይዘንለት!
ኡስታዝ በድር ሁሴን በአባድር መስጂድ ሽኝቱ ላይ የተናገረው።
- - - - - - - - - - - - - - - -
ሙሀመድ ሰኢድ የ4 ልጆች አባት ነው። ልጆቹን የቲም አድርጎ ነው የሄደው የሁላችንንም ድጋፍ ይፈልጋል። የቲም የሆኑ ልጆቹ የአባትነት ጣዕማቸውን ቢያጡም እንደማህበረሰብ አንድ ነገር ብናደርግ መልካም ነው። እናም ለየቲም ልጆቹ የምትለግሰት ስጦታ ካለ በልጆቹ እናት በባለቤቱ አካውንት የምንችለውን እንነይት።
የአካውንት ስም:- ነጃት አብዱልመናም ጡሃ (ሚስቱ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000458278297