📗ከመፅሐፍት.ዓለም📗


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ማንበብ የስብዕና ልህቀትን ያጎናፅፋል!!
ማንበብ ምክንያታዊ እና የሰላ አእምሮን ያንፃል!!
በዚህ ቻናል
👉የስነ ልቦና ምክሮች
👉ግጥሞችና ወጎች
👉ሳይንስና ፍልስፍና
👉ከመፅሐፍ የተቀነጨቡ አስገራሚ ፅሁፎች እና ታሪኮች ይቀርባሉ።
ወዳጆዎን የዚህ የንባብ ማዕድ ተካፋይ እንዲሆኑ በመጋበዝ ቻናሉን ይደግፋ።
ማንኛውም አስተያየት @FiyametaGelay ላይ ይላኩልን
Creator -kalkidan

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


📖📖📒📗📘📚


✋😍


ከመፅሐፍ ገፅ ® dan repost
የዘመድ ቄስ
በሀገራችን የዘመድ ቄስ እየፈታ ያልቅስ ይባላል። ሰው ሲሞት ካህናት ይጠሩና ፀሎት ያደርጋሉ። ይኼ ፀሎት > ይባላል ። ለካህኑ ፍትሐት ማድረግ የክህነት ግዴታው ነው። ካህን ሆኖ ምናልባት የተሰማራበት፡ምናልባት እንጀራው የሚበላበት፡ወይንም ደግሞ ስራው ነው። ምንም ቢሆን ግን ሟች ዘመዱ ነውና ያለፈ ህይወቱን፡ውለታውን፡ አብረው ያሳለፉትን፡መለያየታቸውን እያሰበ ያለቅሳል። ዘመድ መሆኑ እንዳይፈታ፡ ካህን መሆኑም እንዳያለቅስ አያግዱትም። ለዚህም ነው "እየፈታ ያልቅስ" የተባለው። ይህ አባባል ሁለት ነገሮችን አንድ አድርጎ የያዘ ነው። ስራን ወይም ኃላፊነትን እና ሰብአዊነትን ። መፍታት ስራው ነው። የተሰማራበት ግዳጁ። ማልቀስ ሰብአዊነት፡ሰው መሆኑ።ሰው በየትኛውም ሥልጣን ፡ክብር ላይ ሲቀመጥ በውስጡ ሰው መሆኑን መርሳት የለበትም ነገሮችን በሥልጣን ወይንም በእውቀት መነፅር ብቻ ማየት የለበትም። በሰብአዊነት ጭምር እንጂ። እርሱም ሰው ሆኖ የዚያኛውንም ወገን ሰውነት ሳይዘነጋ አንዳንዴም ራሱን በዚያኛው ጫማ ውስጥ ቆሞ ማየት አለበት።
ለሁላችንም ቢሆን የዘመድ ቄስ ያስፈልጋል።ኃላፊነቱን ሳይዘነጋ በሰብአዊነት የሚያገለግለን።

ሰሞኑን ያጋጠመኝ አንድ ታሪክ አካፊያቹ ልሰናበት ። በምሰራበት ክልኒክ አንድት እድሜዋ ከ13 የማይበልጥ ልጅ ለእርግዝና ምሪመሪያ መጣች ። በጣም ነበር የደነገጥኩት እንዴት በዚህ እድሜ ብዬ ስለ እሷ ማጣራት ጀመርኩ ይባስ ብሎ በሴተኛ አዳሪነት ተሰማርታ እንደምትሰራ ነገሩኝ ። ከልብ አዘንኩ ማን ይሆን ለዚህች ልጅ ህይወት መበላሸት አላፊነት የሚወሰደው። ምን አይነትስ ወንድ ይሆን በዚህች ህፃን ጭኖች መሃል ገብቶ የሚደሰተው፡ የእሷን የስቃ ድምፅ መስማትስ እንዴት አስቻለው። በነገሩ በጣም ነው ያዘንኩት፡ ይህች ልጅ የዘመድ ቄስ ቢኖራት በዚህ ህይወት ጎዳና ውስጥ ባልተገኘች ነበር፡በየቤቱ በየ ሀገሩ እንደዚህች ልጅ የዘመድ ቄስ አጥተው የሚሰቃዩ ብዙ ህፃናት አሉ። ሁላችንም ቢሆን የዘመድ ቄስ መሆንም ሆነ ለኛ ለራሳችን ያስፈልገናል። ብዙ የዘመድ ቄስ የሚፈልጉ ሰዎች በዙሪያችን አሉ ፡የዘመድ ቄስ እንሆናቸው በማለት ጨርሳለው

ሰናይ ምሽት



rel='nofollow'>Http://t.me/ewuketmad


የምተፈልጉትን ዲዛይን መርጣችሁ በምርጥ ዲዛይነር ማሰራት ትችላላቹ
በተመጣጣኝ ዋጋ ከሚባለው ከሚታየው በላይ quality ባለው ስፌት
even ጨርቅ ሳይቀር ሞክሩና ፍረዱ !


ቀጥታ ከ Pintreset የተመለከታችኋቸውን ልብሶች ቁጭ አድርገን እንሰራለን እርግጠኞችም ነን!



አድራሻ - አዳማ ፥ አመዴ ውስጥ
Lidu Fashion style👜👗👚👔




ከመፅሐፍ ገፅ ® dan repost
ጥሩ የሚባል ሬስቶራንት ነው በአንዱ ቀን ታድያ
አንድ ሃብታም ሰው ወደዚህ ሬስቶራንት መጣ። ደምበኞችን ጠብ እርግፍ እያለ ሚያስተናግደው ወጣት አስተናጋጅ ወደ ሃብታሙ ሰው ጠጋ ብሎ ምን ልታዘዝ በማለት በሬስቶራንቱ ውስጥ የሚገኙትን ምርጥ የምግብና የመጠጥ አይነቶች በዝርዝር ይነግረዋል።

ሆኖም ግን ባለጠጸጋው ሰው ከማስታወቂያ የፈጠነውን የአስተናጋጁን ሀተታ ከቁብም ሳይቆጠረው ሳንድውች እና ሻይ ብቻ አዘዘ።

አስተናጋጁ በተወሰነ መልኩ ቅር ቢሰኝም የታዘዘውን ወዲያው ያቀርብለታል።
ሰውየውም ከጨረሰ በኋላ ሒሳቡን ጠየቀ።
አስተናጋጁም አሰርቶ ሒሳቡን አሰርቶ ሲመጣ ሃብታሙ ሰው በዓይኑ ውስጥ ሀዘን እንዳለ አስተዋለ።
ጠየቀውም “ሁሉም ነገር ደህና ? ቢለው
"ከባድ ህይወት እያሳለፍኩ ነው" አገልጋዩ መለሰ።

ከዚያም ምንም ሳያስብ ሥራውን ቀጠለ። ወደ ሃብታሙ ሰው ጠረጴዛ ሲመለስ ግን 10,000 ዶላር ከስኒው መቀመጫ ስር አገኘ።
አስተናጋጁ ልጅ ባለጸጋውን ሊደርስበት ሮጠ። ወደ መኪናው እየገባ ነበር።
እሱም “ለምን ይህን አደረግክ ? ” ሲለው
ሰውየው እንዲህ ሲል መለሰ፡- እኔም በአንተ እድሜ ሆኜ “እንደዚህ ባሉ ሬስቶራንቶች ውስጥ እሰራ ነበር። ህይወትን ለማሸነፍ ከባድ ውጣ ውረዶችን አሳልፌአለሁ ሁሉ ነገር ይገባኛል አንድ ሰው በአንድ ወቅት የኮሌጅ ክፍያዬን ሲሸፍንልኝ ለሱ ምንም ማለት ባይሆንም ለእኔ ግን ያቺ ቅፅበት ህይወቴን ለውጠዋለች። ትንሽ ቢሆንም ገንዘቡ እንደሚረዳህ ተስፋ አደርጋለሁ” ከማለቱ
ወጣቱ አስተናጋጅ ሚለውን አጥቶ ፊቱ በእንባ ራሰ

በመጨረሻም “ጌታዬ ለበሽተኛዋ እናቴ አሁን ደረስክላት። ” ብሎት ተለየው።

በማግስቱም ይህ ምስኪን ልጅ ባገኘው ገንዘብ አሳክሞበት እናቱ ከበሽታዋ ተፈወሰችለት።

ለናንተ ትንሽ የሚመስላችሁ ማንኛውም ነገር የብዙሃንን መንገድ ታቃናለችና ከልባችሁ በመስጠት ብቻ ካላችሁ በላይ ፀጋ እና በረከቱን መቀበል ትችላላችሁ።

ቅን እንሁን

http://t.me/ewuketmad


ከመፅሐፍ ገፅ ® dan repost
በተጋቡ የመጀመሪያው ቀን ማንም እቤታቸው ቢመጣ በራቸውን ላለመክፈት ይስማማሉ ። ከዛ በቀጣዩ ቀን ፣ የባል ወላጆች እነሱን ለማየት መጡ ። ባልና ሚስት ተያዩ ባል ፣ በሩን መክፈት ፈለገ ፣ ግን በስምምነታቸው መሰረት በሩን ሳይከፍት ቀረ ፣ ወላጆቹም ተመልሰው ሄዱ ። ከተወሰነ ቀን በኋላ የሚስት ወላጆች እዛው ቤት ተከሰቱ ።

ሚስትና ባል ተያዩ ፣ ምንም እንኳ ስምምነት ቢኖራቸውም ፣ ሚስት ስምምነቱን ጥሳ እያለቀሰች ፣ ለባል ቀስ ብላ በጆሮው ፣ እንዲህ አለች "ወላጆቼ ላይ ይሄን ማድረግ አልቻልኩም" ፣ ብላ በሩን ከፈተች ፤ ባል ምንም አልተገረመም ከብዙ አመታት በኋላ ባልና ሚስት- 4 - ወንድ ልጆችን ወልደው አምስተኛዋ ሴት ልጅ ተወለደች ።

አባት ፦ አምስተኛዋ ሴት ልጅ ስትወለድ ፣ ትልቅ ድግስ አዘጋጅቶ ፣ ሰው ጠርቶ ጋበዘ ። ሚስትም በድግሱ ተገርማ ፣ ባልን እስከ ዛሬ አራት ወንዶችን ሥናፈራ ምንም ያልተናገረ ምንም ያልደገሰ ሰው አዲሷ ህፃን ስለተወለደች ለምን እንደዚህ እንደደገሰ ጠየቀችው ?

ባልም እንዲህ ሲል መለሰላት ። ውድ ባለቤቴ ያኔ ትዝ ይልሻል ? የሠርጋችን የመጀመሪያ ሰሞን ለወላጆቻችን በር አንከፍትም ብለን የተነጋገርን ዕለት ፣ አላስችል ብሎሽ ለቤተሰቦችሽ ስትከፍችላቸው ? ለእኔም ''በር የምትከፍትልኝ : ሴት ልጅ እሷ ነች አላት'' ይባላል!

ሴት ልጅ ክቡር ናት!!

http://t.me/ewuketmad


ከመፅሐፍ ገፅ ® dan repost
አንተ ያስተኛህውን...

፨፨፨

ፍልስፍና እንግዲህ የኛ የሁላችንም ተግባር ነው..እስካሰብን ድረስ መጠየቃችን እስከጠየቅን ድረስ መልስን መሻታችን...መልሱንም መልሰን መጠየቃችን የሕይወት አዙሪት ነው ።

ሶርያ ውስጥ...

" መምህሩ ክላስ ገብቶ እያስተማረ ነው..ድንገት ጥግ ላይ አንድ ተማሪ ቁጭ ብሎ አንቀላፍቶ ይመለከታል...ከዛም ይህንን ይናገራል..

" ጥግ ላይ ያለህው አጠገብህ የተኛውን አስነሳው "
ይለዋል...

ልጁም ይሄንን መለሰለት...

" አንተ ያስተኛህውን ሥለምን እኔ አስነሳው ዘንድ ትጠይቀኛለህ? "



ብዙ ግዜ እኛ አገር ላይ የምንስተው አስተሳሰብ አለ ። ለተማሪ ማንቀላፋት ተማሪውን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ...!! ተማሪን እሚያነቃቃ እና እየገባው እንዲማር እሚያደርግ መምህር ከሌለ ተማሪ ቢያንቀላፋ ምን ይገርማል ። ተማሪ ያልገባውን እንዲጠይቅ የሚያደርግ መምህር በሌለበት ተማሪ ልክ እንደገባው ሆኖ ዝም ማለቱ ምን ያስደንቃል?



ተማሪ አይጠይቅም ማለት ገብቶታል ማለት ብቻ ላይሆን ይችላል ። ወይ እየተማረ ያለው እየገባው አይደለም ወይም መማር አልፈለገም ማለትም ሊሆን ይችላል ። ምህንያቱም ለመጠየቅም በራሱ የተወሰነ መረጃ ወይም መረዳት ያስፈልጋልና ። ትክክለኛ መምህር ማለት ደግሞ የራሱን አስተሳሰብ እኛ ላይ እየጫነ የአስተሳሰቡ ወዛደር የሚያደርገን ሳይሆን እኛም ማሰብ እንደምንችል የሚያሳየን ነው ። ለዛም ነው ሶቅራጥስ...

" ማንንም ስለምንም አስተምሬ አላውቅም የኔ አላማ ማሰብ እንደሚችሉ ማሳየት ብቻ ነው "

ይል የነበረው ።



የኛ የትምህርት አቀራረብ እና አሰጣጥ ላይ ችግር ካለ ተማሪ ለምን አያንቀላፋም...? አንዳንዴኮ የደከመን ሰውነት እንኳን አነቃቅቶ ለትምህርት ዝግጁ እሚያደርግ መምህር አለ...አንዳንዱ ደግሞ የነቃውንም እንዲያንቀላፋ ያደርጋል ። መምህር ራሱን ከመጠየቅ ነው መጀመር ያለበት...የትምህርት አይነት አይደለም የአስተማሪ ልዩነት ነው ተማሪን ለንቃትም ሆነ ለእንቅልፍ የሚዳርገው ።

ራስን መጠየቅ ይቅደም...!!

ምንጭ ፦
📰 philosophical world
ግኝት :- ከፍልስፍና ዓለም

ይቀላቀሉን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/ewuketmad


ከመፅሐፍ ገፅ ® dan repost
ዴል ካርኔጌ ፦ እንደሚለው ራስህን ፈልግና ራስህን ሁን አስታውስ አንተን የሚመስል
በምድር ላይ ማንም የለም።


ራስህን ሁን ራስህንም እወቅ በህይወት ስትኖር ራስህን ካወቅክ አሸናፊ ትሆናለህ።


ሌሎችን ለማስደሰት የራስህን ደስታ ማጣት የለብህም


በሌሎች ሰዎች ዘንድ ብንወደድ መልካም ነው። ሌሎች ሃሳባችንን ቢቀበሉልን
መንገዳችንን ቢደግፉልን ፍላጎታችን ፍላጎታቸው ቢሆን እሰየው።


ነገር ግን የሌሎችን አትኩሮት እና እይታን ስንፈልግ እስከመቼ
መንገዳችንን እንስታለን? ሌሎች እንዲወዱን ስንል
ህሊናችንን እንሸጣለን፤ ሌሎች እንዲያዩን ስንል ያለቦታችን
እንቆማል? ከብዙሃኑ ጋር ለመቀላቀል ስንል ማንነታችንን
እንለውጣለን? ልዩ መሆን ለምን ይሆን የሚያስፈራን?


የራስን መንገድ መርጦ፤ የራስን ማንነት ይዞ፤ የራስን
አስተሳሰብ መሪ አድርጎ መኖር ለምን ይሆን ለብዙዎቻችን
የሚከብደን? እንደሚመስለኝ የብዙዎቻችን ችግር
እንደሌላው ለመኖር ስለምንጥር ነው።


ሌሎች የሄዱበት መንገድ ብቻ ትክክለኛው መንገድ ስለሚመስለን፤ ሜዳው ሁሉ መንገድ
መሆን እየቻል አንዲት ቀጭን መስመር ላይ እየተጋፋን ጊዜያችንን እያባከንን ነው።


ራስህን ፈልግና ራስህን ሁን። አስታውስ አንተን የሚመስል በምድር ላይ ማንም የለም።


ከአሸናፊነት ስነ-ልቦና የተወሰደ


http://t.me/ewuketmad


ከመፅሐፍ ገፅ ® dan repost
ያወቅነው ግን ያላወቅነው!
===============



- አንድ ሰው ከብዙ ዓመታት በኋላ ከቀድሞ የትምህርት ቤት ጓደኛው ጋር በመንገድ ይገጣጠማል፣ ለማመን እስኪያዳግተው ድረስ ጓደኛው አዲስና የቅርብ ሞዴል የሆነች መኪና እንደያዘ ይመለከታል። ታዲያ ወደቤት ሲመለስ ፊቱ በሃዘን ተሞልቶ ይተክዝና ያዝን ጀመር። እርሱ ወደ ኋላ እንደቀረ/እንደከሰረ አስቧልና። ይሁንና ያላወቀው ነገር ቢኖር፥ ጓደኛው የመኪና ሾፌር ሲሆን፣ ለመስክ ሥራ በአለቃው መኪና መላኩን ነው።
*
- ሮዛ ሁልጊዜም ፍቅር አትሰጠኝም/አታቀማጥለኝም/ በሚል ሰበብ ከባለቤቷ ጋር ትጋጫለች። ይኸውም፤ በመኪና ካደረሳት በኋላ እንደጓደኛዋ ሄለን ባል ከመኪና ወርዶ፡ ዞሮ፡ በር ከፍቶ እርሷን አለማውረዱን እንደምክንያት ታነሳለች። ሮዝ ያላወቀችው ነገር፡ የነሄለን መኪና፡ የፊት በሩ ላይ ብልሽት ስላለው ከውጪ ካልሆነ በስተቀር ከውስጥ መከፈት አለመቻሉን ነው።
*
- አንዲት ሴት ከረጅም ጊዜ ቆይታ በኋላ፣ የብዙ አመት ጓደኛዋን ልትጎበኝ በሄደችበት፡ ሶስት የሚያማምሩና ለዓይን የሚያሳሱ ልጆች ሲቦርቁ ዐይታ ስሜቷ ይረበሻል። የመጀመሪያ ልጇን ከወለደች በኋላ ለረጅም አመታት ሌላ ልጅ ለማርገዝ ብትጥርም ሳይሳካ /እየጨነገፈ/ ቀርቷልና። ይሁን እንጂ ያላወቀችው ነገር፡ የጓደኛዋ ልጅ በካንሰር በመያዙ መኖር የሚችለው ለአንድ አመት ብቻ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ ልጆች ደግሞ የማደጎ ልጆች ናቸው።
* * *

ህይወት ሁሉንም አንድ ዓይነት በሆነ መንገድ የምታስተናግድ መድረክ አይደለችም። ካወቅነው ይልቅ የማናውቀው ብዙ ነው። ዐይነቱና መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁሉም ሰው የራሱ ጉድለት አለው። ይሁንና ደስታ የምርጫ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ሰው ግን በህይወቱ ደስተኛ አይደለም።

ይኸውልህ፤ ኤሊ ምን ዓይነት ሸክም እንደተሸከመች ካወቅክ ለምን በጥንቃቄ እንደምትራመድ አትጠይቅም። ከሚታየው ምቾት ባሻገር የማይታዩ ብዙ ሸክሞች፣ ከሚማርኩ ፈገግታዎች ጀርባ ብዙ የልብ ቁስልና ህመሞች እንዳሉ እወቅ። ከሩቅ ያማረ ኑሮ ሁሉ የስኬት ምልክት፣ ከውጭ የሚታይ አንጸባራቂ ነገር ሁሉ ወርቅ አይደለምና። ስለዚህ ያወቅነው 'ደስታውን' ሲሆን ያላወቅነው ደግሞ 'ጉድለቱን/ችግሩንና ድካሙን/' ነው።

"ለምን እኔ ብቻ?" እያልክ ትጠይቅ ይሆን?

እኩዮቼ አግብተዋል።
እኩዮቼ ልጆች አፍርተዋል።
እኩዮቼ ጥሩ ሥራ ይዘዋል።
እኩዮቼ ስኬት ተጎናጽፈዋል።
እኩዮቼ ውድ ቤትና መኪና አሏቸው።
እኩዮቼ በማኅበረሰቡ የተከበሩ ናቸው።
እኩዮቼ እንዲህ ናቸው፤ እንዲያ ናቸው...!!!

ትክክል ብለሃል። ይሁንና ይህንን ጨርሰህ መርሳትህ ያሳፍራል...

እኩዮችህ ሆነው በህይወት የሌሉትን።
እኩዮችህ ሆነው በህመም የሚሰቃዩትን።
እኩዮችህ ሆነው በአእምሮ መታወክ በማህበረሰቡ እንደ እብድ የተቆጠሩትን።
እኩዮችህ ሆነው መንገድ ዳር የሚያድሩትን።
እኩዮችህ ሆነው ወላጅ አልባ የሆኑትን።
እኩዮችህ ሆነው የለት ጉርስ ያጡትን።
እኩዮችህ ሆነው አንተ የምትኖረውን ኑሮ የሚናፍቁና ባንተ ህይወት የሚቀኑ መሰል የሰው ዘርን...ረስተሃል።

ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፡ ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን።

አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!

Credit Samuel geda

http://t.me/ewuketmad




🎄MIK_ARTS WORLD 🌎 dan repost
Hatching and cross hatching are linear drawing techniques that can be used to create texture, value, and the illusion of form and light. Typically used as an application technique when the medium is linear in nature, hatching and cross hatching are often used together.
@Ersasss
MIKARTS ETHIOPIA 🇪🇹
#ስዕል #ስእል #DRAWING


ፍጥረት ሁሉ ፍፁም መሆኑን ተረዳ። ፍፁም ያልሆነ ሁኔታ እንጂ ፍፁም ያልሆነ ሰው የለም። ሁሉም ሰው ክፍቶብህ ከታየህ ከመራገም ይልቅ ነኝ ብለህ ምታስበውን መልካምነት ሁን። ጥላቻ ሲከብህ ነኝ ብለህ ምታስበውን ፍቅር ሁን። ይሄን መሆን ካልቻልክ ግን ሁሌም ቢሆን ማንነትህን ሳታውቅ ትኖራለህ። እራስን መካድ የፈጠረን መካድ ነው። ውብ እና ድንቅ ሆነህ ከተፈጠርክ ውብ ና ድንቅ ሆነህ መኖር ብቸኛው አማራጭህ ነው። ውብ ና ድንቅ ሆኖ የተፈጠረው ደግሞ አንተ ብቻ ሳትሆን ሁሉም ነውና መንገዱን የሳተ ሰው ሲጎዳህ ከመርገም ይልቅ ወደ ውብነቱ ወደ መልካምነቱ የሚመለስበትን ብርሀን አብራበት። ✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው




ከመፅሐፍ ገፅ ® dan repost
ፀሃይ vs አምፖል
ፀሃይ እሷ ወደ ፈለገችበት የሰውን ጥላ ታንቀሳቅሳለች ሰውየው ቆመም ሄደም። አምፖል ግን ሰውየው የራሱን ጥላ እንደፈለገው ተንቀሳቅሶ መቀየር ይችላል። አንተም እንደ ፀሃይ ሁን በዙሪያህ ያሉትን ሰዎች አንተ በምትፈልገው አይነት ባህሪ ቅረፃቸው።


rel='nofollow'>Http://t.me/ewuketmad


ንጉሱ ግጥም አነበበና እንዴት ነኝ¿ ብሎ ነስሩዲንን ጠየቀዉ

"ምንም አትችልም። ልክ እንደ ህፃን ነህ።"

ንጉሱ ተናደደና 3 ቀን አሳሰረው።

በአራተኛው ቀን አሶጣውና አነበበለት...ከዛም እ አሁንስ እንዴት ነኝ? አለው።

ነስሩዲን ዝም ብሎ ሄደ። ንጉሱ ተናዶ ወዴት እየሄድክ ነው? ሲለው

ነስሩዲን፦ "ወደ እስር ቤት.."


http://t.me/ewuketmad


ከመፅሐፍ ገፅ ® dan repost
✔️ ሞቶ ማሸነፍ ✔️

ፈሪ ሸሽቶ ሲድን ባፉ ሊሾምበት፣
ሺ ገዳይ ነኝ ይላል ሺ ሟች በሌለበት፣
በየጦሩ ሜዳ በየትግሉ አቀበት፣
ጀግናው ሞቶ አልቆ ማን ይመስክርበት...?
የኋሊት ተሂዶም ፋኖ በዋለበት ሬሳ ቢቆጠር፣
የሞተ ካለ እንጅ በቃላቱ ጠጠር፣
አንድም ሰው ላይገኝ የሱ ጦር የወጋው፣
አላዩም ብሎ ነው ለቀሪ ሚያወጋው።
እኛም ሁልጊዜ…
የተረፈ አግንነን የሞተ እየረሳን፣
ፈሪ በምላሱ ሠላም ከሚነሳን፤
ገዳይ ብቻ ማድነቅ እንዳይሆንብን ሱስ፣
ሞቶ ማሸነፍን እንማር ከእየሱስ!!

ተፃፈ በክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

ፍቅር ያሸንፋል!!


rel='nofollow'>Http://t.me/ewuketmad


ባዶ እጆች ነን።

ባዶ እጅ ይሰጣል፣ ባዶ እጅ ይቀበላል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እጃችንን ለበጎነት ዘርግተናል:-

እናም ወዳጆች......
እስቲ አንድ ልብስ-የተለበሰ
እስቲ አንድ መፅሐፍ-የተነበበ
እስቲ አንድ ጫማ-የተጨመተ
እስቲ እጃችሁ ላይ ያለውን.....

እኛ ከእጃችን ያለውን በጥቅሉ እስከ ሁለት ሺህ ብር አሰባስበናል። ለህፃናቱ እና በበጎ አድራጎት ቤት ውስጥ ላየናቸው ወጣቶች እና ታዳጊዎች ግን ይህ:-

->ልብስ እና ጫማ

-->የመማሪያ ግብአቶች

(ለልጆቹ መማሪያ መሳሪያዎች
-እስራስ፣
-ላጲስ፣
-ደብተር፣
-መቅረጫ፣
-እስክሪብቶ እና
-ቦርሳ )

->ንፅህና መጠበቂያ

(-ዳይፐር በሳይዝ-ትልቅ፣ትንሽ እና መካከለኛ፣
-ትንሹ ዳይፐር 02፣ 04፣ 05

-ሳሙና ፣
-የገላ ሳሙና ፣
-በረኪና ፣
-ላርጎ ፣
-ዋይፐር ፣
-ቅባት ፣
-ቫዝሊን ፣
-ሶፍት ፣
-ኦሞ ፣
-የእቃ ሳሙና ፣
-መወልወያ እና
-ሞዴስ )


->ምግብ
( -ጤፍ
-ዱቄት
-ዘይት
-በርበሬ
-ሽሮ
-ምስር ክክ
-አተር ክክ
-ድፍን ምስር
-ፓስታ
-መኮረኒ
-ሩዝ
-ወተት ቤቢላክ ቁ.01,ቁ02,ቁ0
-ወተት ሲፕቶሜል ቁ.01,ቁ02,ቁ03
-ኒዶ ወተት(ኮስት)
-ቡና
-ሻይ-ቅጠል
-ፓስቲኒ
-ኦትስ
-ስኳር
-ቂንጬ
-ጨው
-ክኖር )
ሊሸፍን አይችልም።

እናም

"ስለ እናት down syndrome እና otisem የተጠቁ ህፃናትን እና ወላጅ ያጡ ህፃናትን ማሳደጊያ"  አዲስ አበባ ፤ ሣር ቤት በተለምዶ ቫቲካን ኤንባሲ አካባቢ  ለሚገኘው የተራድኦ ድርጅት ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱትን ቁሳቁሶች ወጪ መሸፈን የምትፈልጉ

@MAHiiiiiiTA

👆 በዚህ ውስጥ አልያም

0906945795
0961911174

በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።

እስካሁን ለዚህ በጎ ስራ ፈቃዳቸውን ያሳዩን

-> ኤዞፕ  ነባርና ቀደምት መጻሕፍት መገኛ ቤተ መጽሐፍት። አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት የሚገኘው

-> እነሆ መጻሕፍት

->ብሔረ መዓሕፍት ዘኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል


*በአዲስአበባ 4ኪሎ የምትገኙ እና ቁሳቁስ(ልብስ፣ጫማ፣መፅሀፍት እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን) ለመርዳት የምትፈልጉ
ኤዞፕ ቤተ መጽሐፍት። አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ጀርባ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ፊት ለፊት የሚገኘው መደብር እየሄዳቹህ ከእነሱ ዘንድ ማስቀመጥ ትችላላችሁ። ወይም በስልክ ቁጥር-> #0911723656 መሳይ ብትሉ ታገኙታላቹህ።

*ወይም እነሆ መጻሕፍት ➍ኪሎ ምኒሊክ ት/ቤት ፊት ለፊት
ሮሚና ዝቅ ብሎ
በስ.ቁ-> #0912735000

*እንደዚሁም በአብርሆት እና ጃፋር መጽሐፍ መደብር በሚቀርባችሁ አከባቢ ጎራ እያላችሁ ያላችሁን የቁሳቁስ እገዛ ማድረግ ትችላላችሁ። እኛም አሰባስበን ከልዩ እና ከሚያምር ዝግጅት ጋር ሳር ቤት አከባቢ በሚገኘው "ስለ እናት " የበጎ አድራጎት ድርጅት ከባዶ እጆች፤  ለተዘረጉልን ባዶ እጆች ልንሰጥ ተዘጋጅተናል እና ባዶውን እጃችንን ሙሉሉን።

ለዚህ ሀሳብ የተነሳነው አብዛኛዎቻችን ተማሪዎች ነንና አቅም ቢያጥረን ባዶ እጃችንን ሙሉልን ስንል እጃችንን ዘረጋን።

ለበለጠ መረጃ እና በቅርበት ለማውራት ይደውሉ⬇
0906945795
0964668988

እናመሰግናለን 🙏


ከመፅሐፍ ገፅ ® dan repost
ሁዳረም የኪነት ውድድር

🔔🔔🔔3ተኛው ዙር የኪነት በዮዳኒ ኪነታዊ ውድድር እንደ አውደዓመት አመቱን ጠብቆ በተደራጀ መልኩ መጣ📢


የመወዳደሪያ ዘርፎች

🎬ትወና [ከ2 ደቂቃ ያልበለጠ ተንቀሳቃሽ ምስል-Video]

🎤በድምፅ[የፈለጉትን አይነት ዜማ በማንጎራጎር በድምፅ በመላክ]

🎨በስዕል [የእጅ ስዕል፣ ውበት ያረፈባቸው ስዕሎች]

📸ፎቶ ማንሳት[በዝምታ ብዙ የሚናገሩ ጥንቅቅ ያሉ ተናጋሪ ፎቶዎችን አንስቶ በመላክ]

📝በስነ-ጽሁፍ [አጭር ወግ፣ አጫጭር ታሪኮች፣ ግጥም፣ እና የተለያዩ ፈጠራ የታከለባቸው ስነጽሑፎች]

📚ንባብ እና ትረካ[የግጥም ወይም የወደዱትን የመጽሀፍ አልያም የወግ ትረካን ማራኪ በሆነ መልኩ ተርኮ እና አንብቦ በድምፅ መላክ]

🪗የዜማ መሳሪያ መጫወት[ባህላዊም ሆነ ዘመናዊ የዜማ መሳሪያዎችን እየተጫወቱ በተንቀሳቃሽ ምስል ከ2 ደቂቃ ሳይበልጥ መላክ]



በውድድሩ መጨረሻ

🥇1ኛ የወጣ/ች 500ብር
🥈2ኛ የወጣ/ች 300ብር
🥉3ኛ የወጣ/ች 200ብር
🏅4ኛ የወጣ/ች 100ብር
🎖5ኛ የወጣ/ች በቻናሉ የአድሚንነት ድርሻ ይሰጣል
🏵6ኛ የወጣ/ች በቻናሉ የአድሚንነት ድርሻ ይሰጣል
🏵7ኛ የወጣ/ች በቻናሉ የአድሚንነት ድርሻ ይሰጣል



ማሳሰቢያ

💬በውድድሩ የገንዘብ አሸናፊዎች በራሳቸው ፈቃድ በጥቅሉ እስከ 2ሺህ ብር ለ "ስለ እናት down syndrome እና otisem የተጠቁ ህፃናትን እና ወላጅ ያጡ ህፃናትን ማሳደጊያ"  አዲስ አበባ ፤ ሣር ቤት በተለምዶ ቫቲካን ኤንባሲ አካባቢ  ለሚገኘው የተራድኦ ድርጅት ገቢ ማስድረግ ፤ በተጨማሪም በአካል በቦታው መገኘት ለሚችሉ ያሉትን መጠየቅና አዝናኝ የሆነ መርሃግብርን ለተራድኦ ድርጅቱ ማህበረሰብ አቅርቦ መመለስን ያካተተ።

💬 ማንኛውም በዚህ ውድድር ላይ የሚቀርብ የተወዳዳሪዎች ስራ የባለቤትነት መብቱ በ2ሺህ ሰዎች ፊት የተጠበቀ ነው።

💬ዳኝነቱ 60 በመቶ ከውድድሩ አዘጋጆች በተሰየሙ ዳኞች፤ 40 ከመቶ በተመልካች

💬 ውድድሩ ዙሮች የሚኖሩት ሲሆን፤ ከአንደኛው ዙር ወድድር በኋላ በይፋ ቀጣዮቹን ዙሮች የምናሳውቅ ይሆናል

💬ደንብና ግዴታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ።

🕐ማንኛውም መወዳደር የሚፈልግ ሰው ከዛሬ ማለትም ከቀን 18/7/2016 ዓ.ም እስከ 30/7/2016 ዓ.ም ድረስ መወዳደሪያ ስራችሁን ስም፣ አድራሻ እና ስልክ-ቁጥር በማያያዝ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ማስገባት ይችላል:-👇

@Dayanuna

@MAHiiiiiiTA

@Yoakin_92




💬ከውድድሩ ውጪ በፈቃደኝነት ሳርቤት ያሉ
"ስለ እናት down syndrome እና otisem የተጠቁ ህፃናትን እና ወላጅ ያጡ ህፃናትን ማሳደጊያ"  አዲስ አበባ ፤ ሣር ቤት በተለምዶ ቫቲካን ኤንባሲ አካባቢ  ለሚገኘው የተራድኦ ድርጅት ወገኖቻችን በአካል መጠየቅ ለምትፈልጉ
@znetsebrak በውስጥ አውሩን።

ተጀመረ.................

@gbw_dan

Share Share->->->


ለጥበብ ወዳጆች በሙሉ ይሄንን ግሩፕ በመቀላቀል አጋርነታችሁን ወዳጅነታችሁን ከእኛ ጋ አዝልቁ!!

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.