➲ ❤️ትርጉም አልባ ስሜት🌹
ስረሳህ እያስታወስክ ስቀርብህ መራቅህ
ምን ይሆን ነገሩ አንዴ ልጠይቅህ
ባታፈቅረኝ እንኳን ባይጥምህ መውደዴ
እየሄድክ መምጣትህ ለምን ይሆን ውዴ
አልጠላኸኝ አውቃለሁ ዛሬ ላይ ቢሆንም
ስለኔ በማሰብ ከጎኔ ብትሆንም
አንድ ለመሆናችን ማረጋገጫ የለም
እኔም ያንተ አይደለሁ አንተም ለኔ አትሆንም
ተለያየን ብለን ቆርጠን ተራርቀን
ተጣልተዋል ብለው ሀሜተኛም ቢያማን
ከሳምንት አያልፍም መዘጋጋታችን
ትርጉም አጣሁለት አብረን የመሆናችን
አስበህ ይሆናል ትርሳኝ እኔን ብለህ
ትራቅ ትሂድ እያልክ ልብን አደንድነህ
ጨክነህም ነበረ እንድሸሽ ከጎንህ
ሲጎዳኝ አየሁት ለኔ መጨነቅህ
በቃ አታስብልኝ ተወው ግድ የለውም
ጉድ አድርጎኝ ነው ፍቅር ባንተ አይፈረድም
ቂም ልያዝ ከእንግዲህ ጀርባዬን ልሰጠው
ፊቴን አላዞርም አምርሬ ልወቅሰው
አንተም እንዳሻህ ሁን ልብህ እንዳለልህ
እየጠገንክ አቁሳይ ከሆነ እድልህ
አልሰናበትም መልካም ተመኝቼ
ከተመለስክ ብዬ ልቤን አሳስቼ
ሊጠብቅ ይችላል ተስፈኛ ነው ፍቅሬ
መተው እሱ አያውቅም ሲኖር እስከዛሬ
ግን አንተ ከፈለክ ሂጂ ብቻ በለኝ
የተገፋ አይቀርብም ውዴ አሰናብተኝ።
✨Join & Share✨
@loverzonn
@loverzonn
ስረሳህ እያስታወስክ ስቀርብህ መራቅህ
ምን ይሆን ነገሩ አንዴ ልጠይቅህ
ባታፈቅረኝ እንኳን ባይጥምህ መውደዴ
እየሄድክ መምጣትህ ለምን ይሆን ውዴ
አልጠላኸኝ አውቃለሁ ዛሬ ላይ ቢሆንም
ስለኔ በማሰብ ከጎኔ ብትሆንም
አንድ ለመሆናችን ማረጋገጫ የለም
እኔም ያንተ አይደለሁ አንተም ለኔ አትሆንም
ተለያየን ብለን ቆርጠን ተራርቀን
ተጣልተዋል ብለው ሀሜተኛም ቢያማን
ከሳምንት አያልፍም መዘጋጋታችን
ትርጉም አጣሁለት አብረን የመሆናችን
አስበህ ይሆናል ትርሳኝ እኔን ብለህ
ትራቅ ትሂድ እያልክ ልብን አደንድነህ
ጨክነህም ነበረ እንድሸሽ ከጎንህ
ሲጎዳኝ አየሁት ለኔ መጨነቅህ
በቃ አታስብልኝ ተወው ግድ የለውም
ጉድ አድርጎኝ ነው ፍቅር ባንተ አይፈረድም
ቂም ልያዝ ከእንግዲህ ጀርባዬን ልሰጠው
ፊቴን አላዞርም አምርሬ ልወቅሰው
አንተም እንዳሻህ ሁን ልብህ እንዳለልህ
እየጠገንክ አቁሳይ ከሆነ እድልህ
አልሰናበትም መልካም ተመኝቼ
ከተመለስክ ብዬ ልቤን አሳስቼ
ሊጠብቅ ይችላል ተስፈኛ ነው ፍቅሬ
መተው እሱ አያውቅም ሲኖር እስከዛሬ
ግን አንተ ከፈለክ ሂጂ ብቻ በለኝ
የተገፋ አይቀርብም ውዴ አሰናብተኝ።
✨Join & Share✨
@loverzonn
@loverzonn