መነቀፍህ አይቀርም!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
ጉዳይ የምትሰራው ተዓምር አይደለም፤ ጉዳዩ የምትፈጥረው አዲስ አለም አይደለም፤ ጉዳዩ በራስህ ተጣጥረህ የምትደርስበት ከፍታ እደለም፤ ቁብነገሩ ብቻህን ሮጠህ የምትበጥሰው ሪከርድ፣ ብቻህን ደክመህ የምታመጣው ውጤትም አይደለም። ጉዳዩ መጀመር፣ መስራት፣ ማድረግ መቻልህ ብቻ ነው። ምንም ብታደርግ ግድ አይሰጣቸውም፣ ሃገር ዝረፍክ ሃገር አለማህ፣ እራስህን ጠቀምክ እራስህን ጎዳህ፣ ፍጥነትህን ጨመርክ ዝግ አልክ፣ አገባህ አላገባህ፣ ወለድክ አልወለድክ አጀንዳ ከመሆን፣ የወሬ ርዕስ መነጋገሪያ ከመሆን መቼም አታመልጥም። አንድ እርምጃ በተራመድክ ቁጥር አይኖች ወዳንተ ይሆናሉ፣ ጆሮዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ፣ መነጋገሪ ሊያደርጉህ ይፋጠናሉ። ሊጥሉህ ቢሽቀዳደሙም ስለመነሳትህ፣ ስለመታረምህ ግድ አይሰጣቸውም።
አዎ! ጀግናዬ..! መነቀፍህ አይቀርም፣ መወገዝህ አይቀርም። ለመወገዝም ሆነ ለመነቀፍ ብዙ አስደናቂና አስደማሚ ተዓምር መስራት አይጠበቅብህም። ብዙሃኑ ስለሁሉም ነገር የሚያውቅና የሚያገባው ይመስለዋል፣ ለዛም በየትኛውም አጋጣሚ ማውራት ይፈልጋል፣ አስተያየት መስጠት ያምረዋል፣ ለመተቸት ይንደረደራል፣ ነቀፋ ይቀድመዋል። ማንንም እንደ ልማዱና እንደማንነቱ ካልተቀበልከው ትልቁ መሰናክልህ ሰው ሊሆን እንደሚችል አስታውስ። አንዳንዴ ልታገለግለው በለፋህ፣ ልትረዳው ጊዜህን፣ እራስህን ለሰዋህ እርሱ እራሱ መልሶ ህፀፅ ያወጣብሃል፤ ጣት ይቀስርብሃል፤ ጥረትህን ያሳንሰዋል፤ ዋጋ ያሳጣሃል። ብዙዎች በሰዎች ተሰናክለው ወድቀዋል፣ ብዙዎች በሰዎች ንግግር፣ በሰዎች ተግባር ከህልማቸው ተለይተዋል፣ አላማቸውን ትተዋል፣ እቅዳቸውን ጥለዋል።
አዎ! ጥቂቶች ግን በትቺታቸው ላይ ተራምደዋል፣ በስድብ በዘለፋቸው ላይ ተሸጋግረዋል፣ በስራቸው የተናጋሪዎችን አፍ አዘግተዋል። የምትሰማውን ካልመረጥክ፣ የምታየውን ካልለየህ፣ የሚጠቅምህ ላይ ብቻ ካላተኮርክ ትቺቱን ደጋግመህ በሰማህ ቁጥር፣ እርሱ ላይ ባተኮርክ ልክ እየተንሸራተትክ፣ እየወደክ፣ አላማህን እየሳትክ፣ እራስህን እያጣህ ትመጣለህ። በምድር ርካሹና የትምቦታ የምታገኘው ነገር ሃሳብና አስተያየት ሆነና የሚያውቀው የማያውቀውም፣ የሚመለከተውም የማይመለከተው አስተያየት ለመስጠት ሰስቶ አያውቅም። በማንም አስተያየት የመጣ ህልም የለህምና ማንንም እንዳትሰማ፤ ማንም ደግፎህ የህይወት አለማህን አላገኘህምና ለማንም ነቀፋ ጆሮ እንዳትሰጥ፤ ብቻህን ያየሀውን ህልም ብቻህን ማሳካት እንደምትችል አሳይ፤ ከውስጥህ የመነጨው የህይወት ስንቅ በፍሬው አስመስክር።
❤️መልካም ቀን ይሁንላችሁ ❤️