✅ኢ-ሜይል
🔰በኢሜይል የሚመጡ የመረጃ ስርቆቶችን እንዴት እንከላከል?
💧ሀከሮች ወይም scammers የተጠቃሚዎችን የኢሜይል ወይም የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን የይለፍ ቃል ለማግኘት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ጥረት ያደርጋሉ። እነዚህ scammers መረጃዎቻችንን ሰብረው ሊገቡ ከሚችሉባቸው መንገዶችም ኢሜይል ፊሽንግ የሚባለው የሳይበር ጥቃት አንዱና ዋነኛው ነው።
🔰ለመሆኑ በኢሜይል የሚመጡ የመረጃ ስርቆቶችን እንዴት መከላከል አንችላለን?
ባለንበት ዘመን ኢሜይል እና የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሲያችን ጋር በእጅጉ የተቆራኙ ናቸው።
እነዚህ የበይነ መረብ መድረኮች ግላዊ መረጃዎቻችንን ከመያዛቸው ባሻገር አሁን አሁን ከገንዘብ ዝውውራችን ጋርም ጥብቅ ትስስር አላቸው። በእነዚህን ዲጅታል መድረኮች ገንዘብ ማስቀመጥ፣ማዘዋወር እና መገበያየት በእጅጉ እየተለመደ መጥቷል የዲጂታል wallet መበራከቶችም እና ሰዎችም እነዚህን ዋሌቶች እየተጠቀሙ ገንዘብ ማስቀመጥ መጀመራቸው አይዘነጋም ።ይህንን የተገነዘቡት የበይነ መረብ መንታፊዎች ታዲያ የተጠቃሚዎችን የኢሜይል ወይም የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን የይለፍ ቃል ለማግኘት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ጥረት ያደርጋሉ።የበይነ መረብ ሰርሳሪዎች መረጃዎቻችንን ሰብረው ሊገቡ ከሚችሉባቸው መንገዶችም ፊሽንግ/Phishing / የሚባለው የሳይበር ጥቃት አንዱ ነው።
💧ፊሽንግ /phishing / ወይም ተከታትሎ ማጥመድ ወይም ማማለል ህጋዊ እና ትክክለኛ በሚመስሉ ነገር ግን ባልሆኑ ድረ-ገጾች ላይ የክሬዲት ካርድ ቁጥሮችን፣ የባንክ መረጃዎችን ወይም የይለፍ ቃሎችን እና ሌሎች የግል መረጃዎችን እንዲገልጹ በማድረግ ገንዘብ ወይም መረጃን እና ማንነትን ለመመንተፍ የሚደረግ የሳይበር ጥቃት ነው። ድርጊቱም የሚያጓጉ እና የሚያማልሉ እንዲሁም የሚያስፈራሩ መልዕክቶችን በመላክ የሚከናወን ነው እንደምሳሌም ወደአንዳድ ዌብሳይቶች ስትገቡ ይሔን ያህል ዶላር አሸንፋችኋል ውሰዱ በማለት ስትነኩት እነሱ ወደሚፈለጉት ዌብሳይት በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን ይወስዳሉ ።ለመክፈት የሚያጓጉ አገናኞችን/Links/እና አባሪዎችን (attachments) የያዙ መልእክቶችን ወደ ተጠቂዉ ከመላክ በተጨማሪ፤ የመረጃ በርባሪዎች ዒላማ ላደረጉት ሰዉ ከታወቀ ድርጅት ትልቅ ሽልማት እንዳሸነፈ፣ወይም የሚጠቀመው ዲጅታል ዘዴ የመጠቀሚያ ጊዜው እንዳለፈበት እና እንዲዘምን አልያም የተጠቃሚው መለያ መታገዱን እና ቶሎ ምላሽ እንዲሰጥ የሚገፋፉ መልዕክቶች ሊሆኑ ይችላሉ ። በዚህ መንገድ ከታመነ አካል የተላከ በማስመሰል ተጠቃሚው ኢሜይሉን ወይም የጽሑፍ መልዕክቱን እንዲከፍት ያደርጋሉ።በዚህ ሁኔታ በቀላሉ አጥፊ ተልዕኮ የያዙ አገናኞችን /Links/ በመላክ እና ወደ ሚፈልጉት አደገኛ ገጽ እንዲገቡ በማድረግ ጠቃሚ ወይም ሚስጥራዊ መረጃን በቀላሉ ለአደጋ ያጋልጣሉ።
ይህም በግለሰቦች እና በመስሪያ ቤቶች ሀብት እና መረጃዎች ላይ ትልቅ ጉዳት ያስከትላል።በመሆኑም ጉዳቱ ከመከሰቱ በፊት ከስሜት ነፃ ሆኖ የኢሜይል መልዕክቶችን መመዘን ተገቢ ነው ።
💧በሌላ በኩል በኮምፒዩተር ወይም በተንቀሳቃሽ ስልኮቻችን ላይ የምንጭናቸው ደህንነታቸው ያልተረጋገጠ መተግበሪያዎች(apps)፣ ድረ-ገፆች እና ነፃ በይነ መረቦች/Wi Fi/ በዋናነት publicኮቹ ለዚህ አደጋ ተጋላጭ ያደርጋሉ። በተጨማሪም እንደ ቪፒኤን ያሉ አውታረ መረቦች ጥንቃቄ ካልታከለበት ለዚህ ችግር ሊያጋልጡ ይችላሉ።
🔰ስለሆነም በኢሜይል የሚመጡ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል
💧 አላስፈላጊ የሆኑ የኢሜይል መልዕክትን ማጣራት /Filter Spam/
💧 የማይታወቁ ወይም አላስፈላጊ የኢሜይል መልእክቶች ወደ ግል ሆነ ወደ የድርጅት የመልዕክት ሳጥን እንዳይገቡ ማገድይረዳል
💧ሰዋሰዋዊ ስህተት እና የፊደል ግድፈቶች ያሉባቸው ድረ-ገፆችን ሁልጊዜ በትኩረት ማየት እና አለመጠቀምም
💧በይነመረብ ስንጠቀም ያለፍቃዳችን ብቅ እያሉ እንድንጭናቸዉ የሚጠይቁ ማስታውቂያዎችን ከመክፈት እና ሚስጥራዊ መረጃዎችን ከማስገባት መቆጠብ
💧የግል እና ሚስጥራዊ መረጃዎን እንዲሁም የገንዘብ ነክ መረጃን በይነመረብ ላይ በጭራሽ አለማጋራት
💧 የባንክ ሂሳብ መግለጫዎች /statements/ በመደበኛነት ማረጋገጥ
💧የመረጃ ማፈላለጊያን/web browser/ ወቅቱን ጠብቆ ማዘመን ያስፈልጋል።
💧 መረጃዉ ቢጠፋ እንኳ መተካት የሚያስችል መጠባበቂያ /backup/ መያዝ
💧የሚጠቀሙትን የድረ-ገጽ ደህንነት ማረጋገጥ
💧ደህንነቱ የተጠበቀ ፋየርዎልን /firewall/ በመጫን ኮምፒዉተር ላይ አጥፊ ተልዕኮ ያላቸዉ ሶፍትዌሮች እንዳይገቡ መከላከላል
💧ከዚህ በተጨማሪም ጠንካራ እና የማይገመቱ የይለፍ ቃሎችን መጠቀምም አስፈላጊ ነው
💧ከዚህ ባሻገር የባለብዙ ደረጃ የደህንነት ማረጋገጫ መጠቀም ፣ በፅሁፍ መልእክት የሚመጣ የአንድ ጊዜ የይለፍ-ቃል እንዲሁም በአሻራ እና በፊት ገፅ የሚከፈቱ የይለፍ ቃሎችን መጠቀም ጠቃሚ ነው
💧 የይለፍ-ቃሎችን በመደበኛነት መቀየርም ሌላው አስፈላጊ ነገር ነው
🔰ከምንም በላይ ግን ችግሩ በእውቀት የሚፈታ በመሆኑ ለዚህ ይረዳ ዘንድ በግልም ሆነ በመስሪያ ቤት ስለ መረጃ አጠባበቅ ግንዛቤ የሚሰጡ ስልጠናዎችን መውሰድ ወይም ከመረጃ መረቦች ማንበብ ተገቢ ነው
✅ በአጠቃላይ ብዙ አይነት የኢሜይል ጥቃቶች ሲኖሩ በቀጣይ ዘርዘር አርገን እናያቸዋለን
✅ ወደፊት አሁን ካለንበት የdigital ህይወት በበለጠ የእለት ከእለት ውሏችን ወደ ዲጂታል መንገዶች ስለሚቀየር ከአሁኑ እራሳችሁን በጥንቃቄ ገንቡ maf digital ቻናልም በዚህ ዙሪያ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉ መረጃዎችን ወደፊትም ያቀርብላችኋል ቻናላችንን ሼር በማድረግ መተባበር ትችላላችሁ
@maf_digital