ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የግቢ ጉባኤያት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራን በተመለከተ ምክክር አካሄደ።
የማእከሉ የግቢ ጉባኤያት አማካሪ ቦርድ፣ የግቢ ጉባኤያት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ኮሚቴ እና የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል በጋራ በመሆን ያዘጋጁት እና በማእከሉ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው መርሐ ግብር በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተካሂዷል።
በመርሐ ግብሩ ላይ መምህራን እና በማኅበሩ አገልግሎት ረዥም ልምድ ያላቸው አባላት የታደሙ ሲሆን በማእከሉ የሚገኙ ግቢ ጉባኤያት ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው በሚል ርእስ ጽሑፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
በመጨረሻም የጉባኤው ታዳሚዎች በቀረቡት የግቢ ጉባኤያት ችግሮች ዙሪያ መፍትሔ ለመስጠት በ አምስት ቡድን ተከፍለው እንዲሠሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል።