ማሕቶት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


እይታዎች
አጫጭር ጽሁፎች
ፍልስፍናዎች
For any comment use
@aesoph

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


አዲስ ሳይንስ

ታክሲ ውስጥ ጋቢና የሚባለው ውስጥ ተቀምጬ መንገዱን ሳየው ሳየው አጋጣሚ የሆነ ሰአት ፍዝዝ ማለት ጀመርኩ። ፍጥነቱ ሲጨምር ፍዘቱ ይጨምራል። ምናልባት ቡና ስላልጠጣሁ ሊሆን ይችላል። ቢሆንም ይሄን አሰብኩ።

አንዳንዴ እስኪ የምታደርጉትን ነገር በሙሉ ወጣ በሉና በድሮን እይታ እዩት። እራሳችሁንም ጭምር ወደ ታች ተመልከቱት። የሆነ ልጅ በእግር ሲቀዝፍ ታያላችሁ። አንዳንዴ እኛ ሰማይ ከምንለው እስከ ምድር የሆነ ውሃ የሚመስል፣ ነገር ግን የማናየው ነገር ያለ ይመስለኛል። ነገር የሚል አበዛሁ ይቅር በሉኝ ነገር ግን እኔም ስለማላውቅ ነው ምን እንደሆነ።

አስቡት እስኪ- መብራት ለማጥፋት፣ ጣትን ከፍ ለማድረግ እንኳን ጥረት ይፈልጋል። ስትሄዱ የሚደክማችሁ ይሄ ውሃ ነገሩን ስለምትቀዝፉ አይመስላችሁም? ባይሆንም መኪናው እንዲ እየበረረ ግፊቱ ሲጠፋ ቀጥ ይላል። እኔም ያስደነገጠኝ ሃሳብ ይሄው ነው። እየቀዘፈ ሲሄድ ጎን ያሉት ነገሮች እንደ ቀለም ጭምልቅ እያለ ያልፋል።

ኤር፣ ግራቪቲ፣ ሞመንተም ተብለን ሳንሸወድ አንቀርም። የገባው ይገባዋል- ያው ሲሙሌሽን ውስጥ ሆነን ይሁን እንዴ ? ደግሞ እሱን እንዳንል ይሄ እግር ኳስ የምናየው ነገር፣ የሚገባው ጎልስ? በዛ ላይ ያፈቀርናት ልጅስ?

@mahtot


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
@mahtot


I can never read all the books I want; I can never be all the people I want and live all the lives I want. I can never train myself in all the skills I want. And why do I want? I want to live and feel all the shades, tones and variations of mental and physical experience possible in my life. And I am horribly limited.


From the Unabridged Journals of Sylvia Plath


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ: እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።




ያረጀውን በሬ በስኳር አዲስ የእርሻ method ለማስተማር አትሞክር። ከሞከርክስ? ......


@mahtot


ምለሽ ተገዝተሽ  እንደምትወጅኝ  ስትነግሪኝ ብሰማ፣
ዓለሞ መዞር ብ'ተው ፣በአብሮነታችን ብዛት ተደምማ
ምንም ሳትሰሪ የትም ሳትሄጂ፣
ከቀጠርኩሽ ሰዓት ሴኮንድ ሳታረፍጂ
ዓይንሽ ከዓይኔ ላይ ላፍታ ሳይነቀል፣
ግን ዓይነ ውሃሽ ላይ ባዶ ዕይታ ሲበቅል
ደረቴ ላይ ወደቀሽ - በጆቼ ባቅፍሽሞ፣
ዓይኖችሽ ውስጥ ሳጣሽ... ብትኖሪም የለሽም!!!!

ይሄ ነው መሸነፍ!!


#አንፈርስምአንታደስም

@mahtot


🌼🌼የዛሬ አመት ያረድነው በግ ይሁን ተመልሶ መጥቶ የሚታረደው ? 🌼🌼

አለ 𝙽𝚒𝚎𝚝𝚣𝚜𝚌𝚑𝚎

አዲስ አመት...ማለቴ አዲስ ገበያ- ልል እፈልግና፣ ለበዓል ገበያ መሄድ እንደምወድ ሳስብ መለስ አልኩኝ። የወትሮው የትችት መንፈሴ consumerism ምናምን በል በል ይለኛል፣ ነገር ግን አውቃለሁ: እሱም፣ በዓል ያለ ገበያ እና ንግዱ በዓል እንደማይሆን።

ሶፋ ላይ ሰብሰብ ብላ "ህዝቡ ገብያ በገቢያ ሆኖ ሊሞት ነው። ምነው እቴ፣ እንዲህ ሳይተራመሱ አይከበርም እንዴ" ብላ የምትተቸው እናቴ በራሷ ከ3 ቀን በፊት ሻሼ ገበያ ገዛዝታ ጨርሳ ነው። ይዛ የመጣችው ዶሮ ጓሮ ያፈራው ሳይሆን ከሻሼ የተሸመተ ነው። የምታቁላላው ሽንኩርት ከጋርመንት እንጂ ከገበያ የተገዛ አይመስላትም። በዓል ማለት እኮ በራሱ ገበያ ነው።

አስተውላችሁ ከሆነ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገበያ ላይ ብቅ፣ ብቅ እያሉ ያሉ አዳዲስ ትሬንዶች አሉ። በዋናነት

✯ዶሮ ከቆዳ መልስ የሚሸጠት ነገር ነው።
(ዶሮን በትእዛዝ የሚገነጥሉ)

ይሄ በእውነቱ ከሆነ ሞያ-አነስ ሴቶቻችን exponentially እየበረከቱ መሆኑን ያሳያል።

የፕላስቲክ ቄጤማዎች።

ይሄ ቄጤማ ፕላስቲክ ከመሆኑ የበለጠ እጅግ የቀለም ተጻራሪነት አለው። ቄጠማ ሳይሆነ ለምለም ዊግ ነው የሚመስለው። የቄጠማ አገልግሎት፣ የበዓሉ እለት እቤት ከማስዋብ በቋሚ ቅርስነት ወደመቀመጥ ተዘዋውሯል። ይሄ በመሰረቱ ተጸናውቶን የኖረ የዕቃ-አለመጣል ባህላችንን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ይመስለኛል። ለዚህ ያለኝ ምክር: በሐበሻ ቤት ውስጥ በእቃው ላይ የተጻፈውን ጽሁፍ አትመኑት የሚል ነው(ጨው የሚለው እቃ የእርድ ማስቀመጫ ሊሆን ይችላል)።

ሆነም ቀረ በዓልን ዳቦ በትዛዝ እያስደፋን፣ ጠላ እየገዛን፣ ዶሮን እያስገነጠልን፣ ቡና እየፈጨን፣ ገበያም እየቀረን ስናከብር ደስ ይላል😉...

🌼🌼🌼🌼መልካም ዋዜማ 🌼🌼🌼🌼

@mahtot


ይሄ ጽሁፍ ለእናንተ ነው:

❊ከዶፍ ዝናብ ቤታችን መቅረት ላልቻልን፣
❊ታክሲ ስለሌለ ረጅም ሰልፍ ላይ ውሃ በጀርባችን ለተንዠቀዠቀብን።
❊ጣታችን እንደ አንከር ደንዞዞ ወደ'ሚደብር ስራ ለምንሄድ።
❊በታክሲ፣ በባስ እየሄዳችሁ ለምታነቡ እህት ወንድሞቼ- እኔ የእናንተ ታናሽ ይሄን ፅፌላችሁአለሁ።
❊አንድ ቀን እንደ ትዝታ እስክናወጋው .....መልካም መንገድ ወ ዝናብ

@mahtot


ሰዎች ሁሉ ይቸገራሉ - ያ ዘላለማዊ ሃቅ ነው። ነገሩ፣ አንድ አንዱ የሚቸገረው በህይወቱ እራሱ የፈጠራቸውን ችግር በመፍታት ነው። ሌላው ደግሞ በሞት እና ህይወት መኅል ባለች ጠባብ መስመር ላይ በመሄድ ነው። ሌላው ከቄዬው ሲፈናቀል፣ አባት እናቱ ሲገደሉ፣ መውጫ መግቢያ አጥቶ ሲታሰር፤ አንድ-አንዱ ለምን ትኩረት ተነፈግኩ ብሎ የሰው ህይወት ቁም-ስቅል ያደርጋል።

ችግርን የምንለይበት አይን ይስጠን፤ አሜን።
አስተዳደግ የበደለውን ንቀን፣ የእውነት የተቸገረውን እንረ:ዳ ዘንድ ማስተዋል ይለግሰን፤አሜን።

@mahtot


I would say Uzbek is my first love (from a travel point of view). It's a type of travel that'd live in your heart forever. I went there as a kid, but I remember it was the most beautiful country. Rich in culture, color, history, and everything, you know. The most fascinating thing about it is their buildings. I've never seen such a thing before or since. In my country, even historical buildings are boxy, but there, everything is geometry. Their food is new; I forgot the names. I remember going to Qarshii, it's a city in the south—the people are gentle and kind. After that, we went to Khiva—another lovely city. It could take me hours to talk about it, but in short, it was really mesmerizing...

@mahtot




የቀዘቀዘ ቡና


አንድ አንዴ ህይወት ላይ- ጥቃቅን ነገሮች የሚሰጡት ስሜት የተለየ ነው።

የሆነ የወደድነው ሰው ደውሎ፣ ልክ ልናነሳው ስንል-ስልኩ ሲዘጋ የሆነ ውስጣችን የሚያንሰራራ ስሜት አለ። ምናልባትም የመደወል ሃሳቡን ቀይሮ ይሆናል። ይሄንን አግንነን ከማሰባችን በፊት ድጋሜ ስልካችን ይጠራል-እኛም አንስተን የዛን ሰው 'ሄሎ' ስንሰማ...በቃ ሞቅ ይላል።

ዝናብም ብርድም ነው። የሆነን ሰው ወደ ላይ፣ ምናልባት በዛ በኩል ሄዳ ይሁን ብለን-ወደ 'ታችም ስንጠብቅ... ብርዱ ጣታችንን ምንም ያህል ቢያቀዘቅዘው አልፎ አልፎ ከተጠለልንበት ጣራ' ወደሚወርደው ውሃ እንሰደዋለን። ይሄ ውሃ አይቀዘቅዝም፤ ምክንያቱም ነገ እነዚህ የሚወርዱ ውሃዎች በግጥም እና በትዝታዎቻችን ውስጥ የመኖራችን ማስራጃዎች ናቸው። ሆኖም ግን አንድአንድ ---መጣች ከላይ(ይቅር በሉኝ ለዓረፍተ ነገር መቋረጥ።)

ቡናችን ይቀዘቅዛል። ምክንያቱ እሷ ነች። ቃላቶቿን ለመስማት ናፍቀን አልነበር? የናፈቅነውን ስናገኝ በዝንጋኤ ቡናችን ይቀዘቅዛል። አለም ላይ ላሉ ቡናዎች መቀዝቀዝ ሁላ ተጠያቂው እሷው ናት።

የዝናብ Anatomy በጣም ይገርመኛል። ቀኑን በተወሰነ መልኩ የማላቅ አቅም አለው።
ሰው የምትጠብቁ ከሆነ-መጠበቃችሁ እንዲሰማችሁ ያደርጋል።
እጇን የምትይዙ ከሆነ-ሙቀቱ እንድትለዩ ያደርጋችኋል። የቱ ጣቷ:የቱ ጋር እንዳረፍ ታውቃላችሁ። የምትናገራቸውን ሃሳቦች በዝናብ ከሰማችሁ-ይለያል። እልፍ አለም ከልባችሁ ላይወጣ ይችላል። የዝናቡ ችክችክታ 'ረትታ ቃሏን ካወጣች በተለየ መልኩ ውስጣችሁ ሊዘልቅ ግድ ይላል።

@mahtot


This line




የሆነ ሰው ካንተ ያነሰ እየሰራ ካንተ የተሻለ ለምን እንደሚከፈለው መቼም ልትረዳው የማትችለው ነገር ነው .....



@mahtot


ኢትዮጵያውያንን እና chatGptን
ምን ያመሳስላቸዋል:


ይሄን አነስተኛ የAiን ክፍል መጠቀም ከጀመርን ሰንበትበት ሳይል
አይቀርም። የሆነው ሆኖ አሁንም ድረስ ይሄንን የቃለምልልስ አውታር የማይጠቀሙ ሰዎች ጥቂት አይደሉም። ጥሩ ነው መጥፎ-ጊዜ ይፈታውል።

ከጥቂት ጊዜ በፊት SEO(search engine optimization) የሚባል ሃሳብ ወይም የትምህርት ክፍል ነበር። ሰዎች እና ቢዝነሶች እንዴት በኢንተርኔት መውጫዎች ይበልጥ ለሰዎች ጎልተው መታየት ይችላሉ፤ እንዲሁም ተጠቃሚዎች እንዴት ለነሱ ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ፣ ከፈለጉት ነገር ጋር የሚጣጣም ግብአት ያገኛሉ የሚል ሃሳብ/ትምህርት ነበር።

ለምሳሌ አንድ ሰው 'እንዴት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሃብታም መሆን እችላለሁ?' ብሎ ቢያስብ። ጎግል ውስጥ በመግባት how to be rich fast ብሎ ይጽፋል።
በመሆኑም ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ ጋር የተያያዙ ጽሁፎች፣ቪድዮዎች፣ዜናዎች ወዘተ የመጡለታል።

ኢንተርኔት የሚሰራው በተለያየ መንገድ ቢሆንም፣ በቀላሉ ሰውየው የተጠቀማቸው ቃላት እንደ ውጤት በመጡት ግብዓቶች ውስጥ ምን ያህል ተጠቅሰዋል በሚል ነው።

በዚህ መሰረት በቅድሚያ

How 50 ጊዜ
Fast 35 ጊዜ የተጠቀሰበት ከላይ ያስቀምጥና

How 44 ጊዜ
Fast 30 ጊዜ የተጠቀሰበትን ያስከትላል።
በዚህ መሰረትም በክፍት ቦታ ያስቀመጥናቸውን ቃላት አስልቶ ይዘረዝርልናል።

የቱ ጋር ነው ታዲያ SEO የሚመጣው ብላችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ።
አሁን አንድ ጽሁፍ ውስጥ how እና fast የተወሰነ ጊዜ ተጠቅሰዋል ማለት እኛ የጠየቅነውን ጥያቄ ይመልሳል ማለት አይደለም። ምናልባት እነዚህ ጽሁፎች ጥቂት ቦታ ስለ ገንዘብ አውርተው አብላጫውን ስለ መኪና አነዳድ ያወሩ ይሆናል(how to be drive fast)።

ምናልባት እኛ ላሰብነው ጥያቄ ይበልጥ ጠቃሚ የሆነው ቃል how፣fast፣be፣rich የሚሉት ቃላቶች ላይሆኑ ይችላሉ። እና SEO በመሰረታዊነት ካሰብነው ሃሳብ ጋር ጥብቅ ዝምድና ያላቸው ከዛም ባለፈ በኢንተርኔት አለም ከሃሳባችን ጋር ዝምድና ያላቸው ጽሁፎች ሲጻፉ ብዙ ጊዜ አገልግሎት ላይ የሚውሉትን ቃላቶች ወይም አረፍተነገሮች ስለማወቅ ነው የሚያጠናው ወይም የሚያጠነጥነው። ለእኛ ጥያቄ ምናልባት የሚያስፈልጉት የፍለጋ ቃላት currency, wealth, income, grow ይሆናሉ።

አሁን አሁን ሰዎች ምንም ነገር ፍለጋ(search) ማድረግ ሳይጠበቅባቸው፣ ወደ chatGpt በመግባት ጥያቄ በማስፈር መልሶችን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። አመተምህረት፣ ስታትስቲክስ ፣ ቀን ሁሉንም በእርግጠኝነት ይነግራችኋል። ከእናንተ የሚጠበቀው ኮፒ፣ፔስት ማድረግ ብቻ ነው።

ጥያቄው:ያሰቡትን ማግኘት ይችላሉ ??የሚለው ነው።


ነጥብ ቁጥር
1. ሰዎች በረጅም ታሪካቸው ቸልታቸው ሁሌ ዋጋ ሲያስከፍላቸው የኖሩ ዝርያዎች ናቸው። ሁሉም በሚባል መልኩ chatGptዎች ከስራቸው


-- may make mistakes, please don't rely on its information.
-- may display inaccurate info, including about people. So double check its responses.

ማስጠንቀቂያዎች አሉ።

እና ሁሌም ፊትለፊታችን አለ፣ ነገር ግን ግድ አይሰጠንም። ጥቂት ሰዎች ይሄንን ያውቃሉ(ሰዎች የሆነ ነገር ልክ እንዳልሆነ ብትነግራቸው ልክ ነው ብለው በራሳቸው መንገድ እንደሚሄዱ። ወይም ይጎዳል ብለሃቸውም ያደርጉታል ሆነም ቀረም-ለዚህ: ሲጋራ ጥሩ ምሳሌ አይደለም?) ለራሳቸውም ጥቅም ይጠቀሙበታል። ልክ ባይሆንም ያገኘነውን መልስ አሜን ብለን እንወስዳለን።

2. ChatGpt ለመዋሸት ግድ የለውም። የሆነ ነገር ጠይቃችሁት የመለሰውን መልስ 'it's not correct' ብትሉት፣ በአቋሙ ጸንቶ ልክ ነው ምናምን አይላችሁም። ይልቅ my apologies ብሎ ሌላ ይቀይርላችኋል።

3. ምኑን ከየት እንዳመጣው በምን ይታወቃል?

ሆነም ቀረ ያ ሁሉ word fitting, SEO ገደል ገባ። እና ወደ ዋና ነጥቤ ስመጣ። አንዳንዴ እኛ እና ይሄ ነገር አንድ ነን ያስብለኛል። መቼም ቢሆን አላውቅም አይልም፤ልክ እንደእኛ። ይቀባጥርላችኋል እንጂ sorry I'm new to this የሚል መልስ ከ'ሱ አታገኙም።

ይሄን ለማወቅ እስኪ የሆነ ፐዝል puzzle ስጡት። ይቀባጥራል፣ የሌለ ነገር ይነግራችኋል። ቁጭ የእኛ ባህርይ አይደል?

ለማረጋገጥ እስኪ ይሄን አናግራም (anagram) ወደ ፍራፍሬ ቃል ወይም ወደ ማንኛውም ቃል ለውጥ በሉት:

1. Ohyaicrem
2. Sirceaenrbr
3. Ursmreelib
4. Hpecsae
5. Iayatp

ያስቃል አይደል? ሌላ የማየው ተመሳሳይነት ምን መሰላችሁ: አቋም አልባነት።
በያዘው ነገር ጽንቶ አይከላከልም፣ ልክ ነው/ስህተት ነው አይልም። አጎብዳጅ እና ጥፋቱ ላልሆነ ነገር ይቅርታ ይጠይቃል።

እና እኔም አቋሜን ትቼ በመሃል አቋርጬ ል...

@mahtot
@mahtot






#መስቀል
@mahtot

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.