🚨🎙️ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከአንጎል ቀዶ ጥገና በኋላ ስላሳለፉት አስፈሪ ጊዜ ተናገሩ!
🗣️ “ድምፄን አጥቼ ነበር፤ መናገርም አልችልም ነበር። ያ በጣም አስፈሪ ጊዜ ነበር።
የልጅ ልጆቼ ሊጠይቁኝ መጥተው ድምፄን እንዳጣሁ አስታውሳለሁ።
ከዚያ የንግግር ሕክምና ባለሙያ አመጡልኝ። እሷም የወፎችን፣ የእንስሳትንና የወንዞችን ስም እንድጽፍ ትጠይቀኝ ጀመር።
በዚህ መንገድ ድምፄ ቀስ በቀስ ተመለሰ።”
ፈርጉሰን በአንድ ወቅት ካጋጠማቸው ከባድ የአእምሮ ደም መፍሰስ እና አስቸኳይ ቀዶ ሕክምና በኋላ ድምፃቸውን ሙሉ በሙሉ አጥተው መናገር እንዳልቻሉ ገልጸዋል።
ይህን አስፈሪ ወቅት በንግግር ሕክምና እና በተደረገላቸው ልምምድ በመታገዝ አልፈውታል።
@man_utd_ethio_fanss@man_utd_ethio_fanss