"ላመንስ በየቀኑ ይበልጥ እየተሻሻለ ይሄዳል " !!
የማድሪዱ እና የቤልጅየሙ ኮከብ ቲቦ ኩርቱዋ ስለ ሴኔ ላመንስ ያለውን አስተያየት ገልጿል :
“ቤልጂየም ከዓለም ዋንጫው ከተሰናበተች በኋላ ላመንስ ትችት ደርሶበታል፤ ግን በጣም ጥሩ ምላሽ ሰጥቷል ።
በቅርብ ጊዜ በተደረጉት ሁለት የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች 12 ኳሶችን አድኖ አንድ ግብ ብቻ ተቆጥሮበታል፤ እንዲሁም አንድ ጨዋታ ግብ ሳያስተናግድ አጠናቋል ።
በዓለም ዋንጫው ወቅት ልምድ አልነበረውም፤ ከስፔን ጋር ባደረግነው ጨዋታ ደግሞ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታና ከተከላካዮቹ ጋር በቂ ቅንጅት ሳይኖረው ወደ ሜዳ ገባ ።
ሴኔ ገና ወጣት ነው፣ እየተማረም ነው። ልምድ እያገኘ በየቀኑ ይበልጥ እየተሻሻለ ይሄዳል ።”
@man_united_ethio_fan@man_united_ethio_fan