🌿ክፍል አራት (➍)🌿
🌿🌿"ጤዛዉ ፍቅሬ"🌿🌿
🌹🌹(ኑዕማን ኢድሪስ)🌹🌹
ጢርርር ... ጢርርርር..." ጥሪዉ (ደዋዩ) ማን እንደሆነ ለማየት ስልኩን ከሱሪዉ ኪስ አወጣና አየ፡፡ "Hamza" ይላል፡፡ ስልኩን ሳያነሳዉ ድምፁን ቀነሰና ጥሪዉን ድምፅ አልባ አደረገዉ፡፡ ንዴቱ ዉስጡን እያላወሰ ነበርና አይኑን ማጉረጥረጡን ቀጠለ፡፡...
..."ማን ነዉ የደወለዉ?" አላት፡፡ እጆቹን ጨብጦ ለቡጢ እያዘጋጃቸዉ፤ ሁኔታዉ ከሚስቱ ፊት ሳይሆን ከደመኛዉ ሊበቀለዉ ከሚፈልገዉ ሰዉ ፊት የቆመ ይመስላል፡፡ ፎዚያ ፈራችዉ፡፡ በዚህ ንዴቱ መምታት ከጀመራት እንደማያቆም ታዉቋት ትርበተበት ገባች፡፡ ወደ'ሷ ጠጋ እያላት ጥያቄዉን ደገመዉ፡፡
..."ማን ነዉ የደወለዉ?... እ...?..." ፡፡ ምን ብላ ትመልስ?፡፡ ተደዉሎላት ሳይሆን ደዉላ ነዉ፡፡ 'ሀምዛ ነዉ ብለዉስ?.. ከ'ሱ ጋር ይጠረጥረኝ ይሆን?... የሚዋደዱ ጓደኛሞች በ'ኔ ምክንያት ቢጣሉስ?" እያለች ዉስጧን በስጋት ሞላችዉ፡፡ በዚሁ መካከል ሀምዛ ቅድም ደዉሎ ስላልተነሳለት በድጋሚ ለሀቢብ ደወለ ... "ጢርርርር... ጢርርርር...." የፎዚን ንዴት ስልኩ ላይ ሊወጣዉ ይመስል እጆቹን በሃይል ወደ ኪሱ ልኮ ስልኩን አወጣና አረንጓዴዉን ተጭኖ..." ሄሎ ..." አለ፡፡
..."ሄሎ ... ሃቢብ ብደዉልልህኮ አታነሳም" የሀምዛ ድምፅ ነበር፡፡ ከመበሳጨቱ የተነሳ ያሁኑ ደዋይ ማን እንደሆነ አላወቀዉም ነበር፡፡
..."እ... አንተ ነህ እንዴ ሃምዛ..."
..."ስልክ ቁጥሬ ቢጠፋህ መቼም ድምፄ አይጠፋህም!" እሱ ራሱ ሃምዛ መሆኑን እያረጋገጠለት ነበር፡፡
..."እ...ለማንሳት አልተመቸኝም ነበር" አለዉ፡፡
..."ከፎዚ ጋር በምን ተጋጭታችሁ ነዉ?"
..."ማን ነገረህ?" ብሎ በቤቱ ዉስጥ አንገቱን አዟዙሮ ተመለከተ፡፡ 'ይሄ ሰዉዬ ተደብቆ እያየኝ ነዉ እንዴ?' ብሎ አሰበ፡፡
መጥፎ የሚሰራ ሰዉ እንኳን ሌላ ሰዉ ራሱንም ይጠራጠራል፡፡ ስራዉ እንደ ቂል አደረገዉ፡፡
..."ፎዚ አሁን ደዉላልኝ ነበር፡፡"
ስልኩን ከጆሮዉ ስር 'ራቅ እያደረገ ወደ ኃላ እንደማፈግፈግ ብሎ ፎዚን በቆመችበት ትቷት ወደ መኝታ ክፍሉ ተመለሰ፡፡
..."እና... ምን አባቷ ወደ አንተ አስደወላት..." አለዉ፡፡ የተጠራጠረ ይመስላል፡፡ 'ግንኙነት አላቸዉ ማለት ነዉ' ሲል አሰበ፡፡ 'በዚህ አይነትማ እስከዛሬ የምነግረዉን ለሷ ይነግራት ነበር ማለት ነዉ!' ... 'ቆይ ግን... ምንድን ነዉ ግንኙነታቸዉ?'፡፡ ሀምዛ ማሜን እየመከረዉ ነዉ፡፡ 'አትጣሉ...' እያለ የጓደኝነቱን ይነግረዋል፡፡ ሀቢብ ግን አልሰማዉም፡፡ እንደዉም ይባስ ብሎ ሀምዛን ከፎዚ ጋር መጠርጠር ይዟል፡፡ ካፉ አላወጣዉም እንጂ 'እሰራለሃላችኃለሁ' እያለ ከንፈሩን በቁጭት ይነክሳል፡፡
..."እሺ በቃ አንጣላም ... ስንገናኝ እናወራለን!" ብሎት ስልኩ ተዘጋ፡፡ ሀቢብ ፎዚን ጠልቷታል እንዳይባል ይቀናባታል፤ ይወዳታል እንዳይባል ደግሞ ያሰቃያታል፡፡ ነገረ ስራዉ ሁሉ 'እሱ እንዲህ ነዉ!' ብሎ ለመወሰን ይከብዳል፡፡
.... ፎዚያ እራሷን ማስጨነቁን ተያያዘችዉ ..'ቆይ ሀቢብ ሊጠላኝ የቻለበት ምክንያት ምን ይሆን?' ብላ እርግጠኛ ሁና መመለስ በማትችለዉ ጥያቄ ራሷን ታፋጣለች፡፡ 'ያ የበፊቱ ፍቅርስ የት ገባ?' ...'ሶፊ ስለ ሀቢብ ጥሩነት እንጂ አንድም ቀን መጥፎነቱን አዉርታኝ አታዉቅም ነበር፡፡ ፍቅር መስጠት እንደሚችል እንጂ ልቡ በጥላቻ የጠቆረ መሆኑን አልነገረችኝም ነበር፡፡' ነበር...
ነበር ...
ነበር... እያለች እራሷን ወደ ኃላ እየጎተተች ሀቢብን የተዋወቀችበትን የምርቃን ጊዜዋን አማረረች፡፡ ያን በደስታ የተፍነከነከችበትን ቀን ረገመችዉ፡፡ 'ቆይ ግን ምን አጉድየበት ተቀየረ?'.... ጥያቄ በጥያቄ ላይ ብቻ መልሱን አታዉቀዉም፡፡ ብታዉቀዉ ግን ደስ ይላታል፡፡ ምክንያቱም ራሷን በራሷ ያፋጠጠችበትን ጥያቄ መልስ ከተመለሰላት ትዳሯ ይሰምራል፤ ፍቅሯ ያብባል ስለዚህ ለራሷ ለህይወቷ ስትል መሆን ያለባትን ሁና፤ መክፈል ያለባትን መስዋእትነት ከፍላ ደስታዋ እንደገና መለምለም አለበት፡፡
.
... ሀቢብና ሀምዛ ሁሌም ከሚገናኙበት ዘቢብ ካፌ ተገናኝተዉ እየተጨዋወቱ ነዉ፡፡ ሀቢብ ዉስጡ ልቡ በጥላቻ ከመጥቆሩም በላይ ከርፍቷል፡፡ የገዛ ጓደኛዉን ሀምዛን በፊት በሚወዳት ዛሬ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ከሚጠላት ሚስቱ ጋር ጠርጥሮታል፡፡ በጨዋታቸዉ መካከል እየተሳሳቁ ቢያወሩም የሃቢብ ሳቅ የማስመሰል ግልፈጣ፤ የሀምዛ ግን ከልቡ የሚመጣ ነበር፡፡ ሀምዛ ቀስ እያለ ወደ ቁምነገሩ እየተንደረደረ ነዉ፡፡
..."ታዉቃለህ ግን ሀቢብ?"
..."ምኑን ነዉ የማዉቀዉ?" አለዉ፡፡ ግንባሩን አጨማዶ፡፡ ሀምዛም ቀጥታ ስለ ፀቡ አንስቶ ይበልጥ ከሚያበሳጨዉ ምናልባት ያንን ጣፋጭ የፍቅር ጊዜዉን አስታዉሸዉ ልቡ ቢለዝብ ብሎ አሰበ፡፡
..."ያንን የፍቅር ጊዜህን፡፡ በፍቅር ክንፍ ብለህ ከፎዚ ዉጭ ማሰብም ሆነ ማለም ያቆምክበት..." እያለ ስለ መልካም የፍቅር ጊዜዉ ሊያስታዉሰዉ ሲሞክር ሀቢብ የሃምዛን ወሬ አቋረጠና...
..."እ... አዎ ትዝ አለኝ!" ብሎ ወሬዉን ከመቀጠሉ በፊት ተንፈስ ሲል ሀምዛ ወደ በፊት አቋሙ ሊመለስልኝ ነዉ በማለት ልቡን ደስታ ተሰምቶት ጥርሶቹ ታዩ፡፡ ፈገግ አለ፡፡ ሀቢብም ያዘዉን ማኪያቱ ፉት ብሎ አፉን በማኪያቶዉ ቃና ካጣጣመ በኃላ ወሬዉን ቀጠለ...
..."እርካሽ መሆኗን ባዉቅ ኑሮ በፍቅር ቅልጥ ባላልኩላት ነበር፡፡" ብሎ ፈግጎ የነበረዉን የሀምዛን ፊት ወዲያዉ አከሰመዉ
╔═══❖•🌺🌺•❖═══╗
ይ ቀ ጥ ላ ል
╚═══❖•🌺🌺•❖═══╝
❥............🍃💐💐🍃..............❥