🌸ክፍል አስር (10)🌸
🌿🌿"ጤዛዉ ፍቅሬ"🌿
✍✍(ኑዕማን ኢድሪስ)✍✍
-----------------((()))----------------
..... ፎዚያ ከወትሮዋ ይበልጥ ደምቃለች። ሰሞኑን በትካዜ ከስሞ የነበረዉን ዉበቷን በአዲስ መንፈስ እንዳዲስ ወደ ቀድሞ እሷነቷ መልሰዋለች። ፊትለፊቷ በተገተረዉ መስታወት ራሷን እየተመለከተች ከዉበቷ ጋር ሙግት ይዛለች። 'ለሀቢብ ከዚህ የበለጥኩኝ ሆኜ መጠበቅ አለብኝ' በማለት የምትቀባባዉ አይነቱ በልክ ፤ አለባበሷ ስልክክ ያለች ወጣት ኮረዳ አስመስሏታል። እዉነታዉም ቢሆን ሀቢብ የተዘበራረቀ ህይወትን እንድትኖር ፈረደባት፤ ኑሮን እንድትጠላዉ አደረጋት እንጂ እሷ ገና አንዲት ፍሬ ነበረች።
.... ቅንድቧን ስትኳለዉ አይኖቿ የሷን ዉበት ብቻ ሳይሆን ቤቱን ጨረቃ የወጣበት እስኪመስል ድረስ ግርማ ሞገስ አላበሰችዉ። ከንፈሮቿ እንኳን ስመዋት በማየት ብቻ ጣፋጭ እንደሆኑ መገመት እስኪያስችል ድረስ .... ጉንጮቿ ፤ መላ አካላቷ ነፍስን የሚጠግን የዉበት ቁንጮ ሆናለች። የቀራት የለም ቤቱን አድምቃ ፤ ራሷን አሸብርቃ ዉድ ባሏን መጠባበቅ ይዛለች።
.
.... ሀቢብ የግቢዉን በር ኪሱ በነበረዉ ቁልፍ ከፍቶ ገባ። ሙቤ የነገረዉ ነገር በልቡ ዉስጥ መንታ ሀሳቦች እንዲፈጥሩ አድርጎታል። 'ለማን ለመዋብ ነዉ የገዛችዉ?' ሲል መጥፎ ጥርጣሬን ፈጥሯል። ይሄን ከንቱ ሀሳብ የሀቢብ ልብ ሳይሆን ፍቅረኛሞችን ለመለያየት ፤ ትዳርን ለመበተን የሚወጥነዉ የርኩሱ ሰይጣን ሀሳብ ይመስላል። "አላህስ (ሱ.ወ) ጠላታችን እንደሆነ ነግሮን የለ?"
.
.... ፎዚ የዉድ ባሏን መምጣት በጉጉት እየጠበቀች ሳሎኑ ዉስጥ መንጎራደድ ይዛለች። ሀቢብም የግቢዉ በር አልፎ ከቤቱ ዋናዉ በር ስር ቆሞ በሩን ለማንኳኳት እጁን ሲዘነዝር አንዳች ሀይል አፍንጫዉን ጎትቶ የሸሚዙን ኮሌታ አንቆ ወደ ዉስጥ የሚያስገባዉ መሰለዉ። የቤቱ ጠረን ገና በሩቁ ይጣራ ነበር። ድግሱ ለሱ እንደሆነ ገባዉ። ፎዚያ በጥሩ መንፈስ ፤ ልቧንም ቤቷንም በፍቅር ሞልታ እየጠበቀችዉ እንደሆነ ተረዳ።
ይሄን የመሰለ ልዩ ዝግጅት እጅና እግሩን (እሱነቱን) ብቻ ይዞ ሊገባ አልፈለገም። ይሄን የመሰለ ልዩ ዝግጅት በተኮሳተረ ፊት ገብቼ ሊደፈርስ አይገባም ብሎ ተጠናዉቶት የነበረዉን አጉል ጥርጣሬ አስወግዶ ፊቱን በፈገግታ ሞልቶ ወደ ቤት የመግባት ሀሳቡን ቀይሮ ወደ ኃላ ዞሮ መንገድ ጀመረ።
.
.... በጉጉት የምጠብቀዉ ሀቢብ (ባሏ) አልመጣላትም። ዘገየባት። ስልኳን አነሳችና ደወለችለት።
"ነህኑ ቀዉሙን አዓዘነላህ
ነህኑ ቀዉሙን አዓዘነላህ
ህዝቦች ነን ያላቀን አላህ...." የሚለዉ የአልፋቲሁን ነሽዳ ከከሱ ዉስጥ እንደሆነ የሀቢብ ስልክ አቃጨለ።
...."ምንድን ነዉ የምሰጥህ?" አለዉ ሙቤ።
...."ቆይ አንዴ ሙቤ...." ብሎ ስልኩን ከኪሱ አዉጥቶ ለማነጋገር የሚያስችለዉን ቁልፍ ተጭኖ ማነጋገር ጀመረ።
ፎዚያ ሰላምታዉን ካስቀደመች ቡኃላ ... "ምን ሁነህብኝ ነዉ ሀቢቢ ሀምዛ አልተሻለዉም'ዴ?" አለችዉ።
.... "መኪያ መጥታለታለች ፎዚ?" ስሟን ሲያቆላምጥላት ዉስጧ በደስታ ማእበል ተናወጠ።
.... "እና አንተ...." ብላ ንግግሯን ሳትጨርስ "ደርሻለሁ ፎዚዬ እየመጣሁኝ ነዉ" አላት።
.
...."አንተ አትናገርም እንዴ? ምንድን ነዉ የምሰጥህ?" አለዉ ጮኾ። ስልኩ ተዘግቶ ስለነበር ፎዚያ የሙቤን ድምጽ አልሰማችዉም።
...."እስኪ ለቆንጆ ሴት የሚሆን ቆንጆ ስጦታ...." ብሎ ትእዛዙን ሳይጨርስ ቀድሞ የሀቢብን አመል የሚያዉቀዉ ሙቤ..."አንተ አሁንም ሌላ ሴት ጋር ትሄዳለህ? ፎዚን የመሰለች ቆንጆ የት ትተህ ሌላ ቆንጆ ትፈልጋለህ??" ብሎ ጮኸበት። የሙቤን ቁጣ ሲሰማ ፈገግ አለና ..."ሙቤ እስኪ ተረጋጋ!" አለዉ።
.... "ምን ያረጋጋኛል? ሚስትህ ቆንጆ ሆና...." ሀቢብ አላስጨረሰዉም።
.... "እኮ ስጦታዉ'ኮ ለሷ ነዉ" ብሎ ቶሎ አፉን አዘጋዉ። ሙቤ ሀቢብን ከፎዚያ በፊት ያዉቀዋል። ያለፈ አመሉ ቤቱ ሴት ማመላለስ ነበር ስራዉ። ዛሬ የያዛትን እስከ ነገ አያቆያትም ነበር። እሷን አባሮ ሌላ ሴት መተካት የሚታወቅበት ተግባሩ ነበር። ይሄንን ስለሚያዉቅ በሚስኪኗ ፎዚ ላይ እንዲህ አይነት የዘቀጠ ትግባር እንዲፈጽም አልፈቀደለትም።
.
.... ከአንድ አይሉ ሁለት ስጦታዎችን ገዝቶ ይዟል። ታፍኖ የኖረዉን የፎዚን ልብ ሊያስቦርቃት ሽቷል። በዚሁ አጋጣሚም ዉስጡ የሚብሰለሰለዉን ጥያቄ ሊያፈርጠዉና በትዳሩ ዉስጥ ግልጽነት የሚባለዉን መርህ ሊያሰፍን አንግቦ ተነስቷል። "የክብረ ንጽህናዋን ጉዳይ...." ይሄ ነገር ዉስጡን ሰላም እንዲነሳዉ አልፈቀደም። መፍትሄ ሊያበጅለትና የጥላቻዉና የመቃቃሩ ጉዳይ ዛሬ እንደሚያበቃለት በዉስጡ ደምድሞ ጨርሷል።
.
..... "ኳ ኳ ኳ" በሩን አያንኳኳ ነዉ። የ'ሱን መምጣት በጉጉት ስትጠባበቅ የነበረችዉ ፎዚያ ተቀምጣበት ከነበረችበት ሶፋ ምንጥቅ ብላ ተነሳችና እየተንደረደረች ወደ በሩ አመራች።
..."ማን ነዉ?" አለች። ሀቢብ ስለመሆኑ አላጣችዉም መጠየቅ ስላለባት ብቻ ጠየቀች። ሀቢብ ፎዚንና እሱን የጋረዳቸዉ በር ስር እንደቆመ በተስረቅራቂ ድምጿ ልቡ ራደ። ያ ማራኪ ድምጿ እሱነቱን ገዛዉ ፤ እጅ ወደ ላይ አስባለዉ።
...."እኔ ነኝ ፎዚ...!" አላት። ፎዚያ የሀቢብ ድምጽ መሆኑን ስታዉቅ ሰዉነቷን አንዳች ስሜት ነዘራት። በሩን እንደከፈተች ጥምጥም ብላበት ከንፈሮች ልትገምጣቸዉ ተመኘች። ሀሳቧን እንደገና መለስ አደረገችና 'ሀቢብ ለዚህ ዝግጁ ባይሆንስ?..' ብላ እያሰበች በሩን ቀስ ብላ በቄንጥ ከፈተችዉ።
"አሰላሙዓለይኩም ሀቢቢ" ፈገግታዋና ፈገግታዉ አንድ ላይ ሲጋጩ ጸሐይ ከመዉጫዋ መንታ ሆና የወጣች መሰለ።
ሰላምታዋን መለሰላትና በጀርባዉ ደብቆት የነበረዉን ቀይ አበባ ለስጦታ ዘረጋላት። "የኔ ቆንጆ... " ብሎ አይኖቹን ሲያቅለሰልሳቸዉ ፎዚ ማመን አቃታት። በድንጋጤ እጆቿን ወደ ከናፍሮቿ አድርቃ "ያ አላህህህህ.... " አለች።
.... እሷም በምላሹ "ሀቢቢ..." ብላ የተዘረጋላትን የፍቅራችንን እናድስ ዉብ አበባ ተቀበለችዉ።
ሀቢብም ወደ ፎዚ አንድ እርምጃ ቀረብ አለና እቅፉ ዉስጥ አስገባት። በእግሩ በሩን ገፋ አድርጎ ከከረመዉ በኃላ ዉብ ከንፈሯን በስሱ ሳም አደረጋት። ፎዚ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳመች እስኪመስላት ድረስ ስልምልም አለችና ከደረቱ ላይ ልጥፍ አለች።
...."ፎዚዬ የኔ ዉድ....." ከእቅፉ ዉስጥ እንዳለች እያንሾካሾከ ሲጠራት ህልም እስኪመስላት ድረስ ወደ ላይ ቀና አለችና አይን አይኑን እያየች "ወይዬ ሁቢ..." አለችዉ።
ይቀጥላል....
https://t.me/maraki_lyrics
በፍጥነት እንዲቀጥል like ፈጠን አድርጉት ውዶቼ