ክፍል አስራ አምስት (15)
"ጤዛዉ ፍቅሬ"
የመጨረሻዉ መጨረሻ
(ኑዕማን ኢድሪስ)
.
.... ሆስፒታሉ በትራፊክ ፖሊሶችና ቆመዉ ክስተቱን በሚመለከቱ ሰዎች ተሞልቷል። ሁሉም ጭንቅላታቸዉን በሁለት እጃቸዉ ይዘዉ የተጎጂዉን መትረፉን ይሁን መሞቱን በጉጉት ይጠባበቃሉ። ... ከሰዎቹ መካከል ግን የፎዚያ የተለየ ነበር። ከዚያ ሁሉ ሰዎች ጉልበቷ ሀይሎ የድገተኛ ክፍሉን በር ገንጥላ ለመግባት ትታገላለች። እሷን ለመያዝና ለማረጋጋት የተወሰኑ ሰዎች እየታገሏት ነዉ። ከነዚያ ሰዎች መካከል ግን መኪያ የለችም። ለባሏ ጓደኛዉ ምን እንደሆነ ለመንገር ሀምዛ ወደተኛበት ጠባቧ ክፍል ሩጫ በቀረዉ ሶምሶማ ደረጃዉን ሽቅብ እየወጣች ነዉ። ባሏ ያለበት ክፍል ገብታ ጉዱን ልታረዳዉ ተቻኩላለች። ስትሮጥ እንኳ ምንም አልደከማትም። ክፍሏ ጋር እንደደረሰች የበሩን እጀታ ይዛ በሀይል ከፈተችዉ። ትንሽ እንቅልፍ ቢጤ ሸለብ አድርጎት በሰሰመን ዉስጥ የነበረዉ ሀምዛ የበሩን በሀይል አከፋፈት ሰምቶ ተዘግተዉ የነበሩ አይኖቹን ወደ በሩ በለጠጣቸዉ ። በሩን በሃይል ገፍታ ፤ ከፍታ የገባችዉ መኪያ ነበረች። ነገር ግን ስትለየዉ በሰላም የወጣችዉ መኪያ ሳትሆን ሁሉ ነገሯ ተቀያይሮ ፤ ድንጋጤና ፍራሃት ግንባሯ ላይ ሸንተር ሰርተዋል። ልቧ በአፏ ልትቀጣ ደርሳ ድዉ ድዉ ትላለች። በአይኗቿ እንባ እያዘነበች ነበር።
.. " እህ እህ..." እያለች ልትናገር የፈለገችዉን ትንፍሿ ይዉጥባታል። ሀምዛ ጋደም ካለበት አልጋ ከወገቡ ቀና አለና ተቀምጦ... "መኪ ምን ሆነሽ ነዉ?" ብሎ የድንጋጤዉን ጮኸ። መኪያ እየተከታተለ የሚወጣዉን ትንፋሿን ገታ አድርጋ... "ሀቢብ ... ሀቢብ..." ስትለዉ የሀምዛ ፊት ባንዴ ተቀያየረ ፊቱን ቅጭም አድርጎ ..." ሀቢብ ምን ሆነ?" አላት።
.... "የመኪና አደጋ ደርሶበት ... እዚህ" እያለች ጣቷን ወደኃላዋ እንደመቀሰር ስታደርግ ሀምዛ ከተኛበት አልጋ ላይ ምንጥቅ ብሎ ተነሳ። መኪያ ባለችበት እንደቆመች ክፍሉን ለቆ ወደ ድንገተኛ ክፍል በቸርኬዉ ተፈተለከ። መኪያም የባሏን በእግሩ መራመድ ሳታስተዉል ከኃላዉ ተከታትላዉ ሀቢብ ወደተኛበት ድንገተኛ ክፍል ተሯሯጡ። የሆስፒታሉን ደረጃ ተንደርድረዉ ወረዱት ከማለት ይልቅ ዘለዉ ባ'ንዴ ከሰዎቹ አጠገብ ደረሱ ማለት ይቀላል። ሀምዛ የእግሩን መጎዳት ረስቶት በሩጫ ከድንገተኛ ክፍል ሲደርስ የተሰበሰቡት ሰዎች የጸጥታ አዋጅ የታወጀ ይመስል ጸጥ ብለዋል። ከሰዎቹ መካከል ግን በሴቶች ተከባ ማልቀስ የምትችልበት ሀይል አጥታ አይኗ እንደፈጠጠ በደረቁ የምትንሰቀሰቅ ፤ ከናፍሮቿ ዉሃ ካገኙ ሳምንታት ያስቆጠሩ ይመስል ዝናብ ጥሎበት እንደደረቀ ዋልካ መሬን የተሰነጣጠቀባት ሴት ተመለከተ - ፎዚያ ነበረች።
... ሀምዛ ሰዉነቱን በሞላ ከዚህ በፊት ተሰምቶት የማያዉቅ የሀዘን ስሜት መላ አካላቱን ሲያዳርሰዉ ተሰማዉ። ፎዚን በተቀመጠችበት አለፍ አለና ወደ ድንገተኛ ክፍሉ ተጠግቶ በመስተዋት የተገጠመዉን በር ወደ ዉስጥ ያሳየዉ ዘንድ አይኖቹን ቀረብ አድርጎ ሲመለከት በነጭ ጨርቅ መላ አካላቱ የተሸፈነ አስክሬን ተመለከተ። - ሀቢብ ስለመሆኑ አልተጠራጠረም። ምንም እንኳ ሁሉም አካሉ የተሸፈነ ቢሆንም ቁመቱ ሀቢብ መሆኑን ይናገራል። "ሞቷል?" ሲል ከአንደበቱ ቃል አወጣ። አጠገቡ ቆሞ የነበረ አንድ ሰዉ እሱን የጠየቀዉ መስሎት "አዎ ሞቷል" ብሎ መለሰለት። ሰማይ ፤ ምድሩ የተቀላቀሉበት መሰለዉ። አይኑ ፍጥጥ ፤ ደሙ ቀጥ አለበት። የስንት ጊዜ ጓደኛዉ ፤ ክፉ ደጉን አብረዉ ያሳለፉ ፤ ደስታንና ሀዘንን በጋራ አብረዉ የወጡት ፤ እንደ'ራሱ የሚወደዉ ጓደኛዉ እሱን ለመጠየቅ ወደ ሆስፒታል ሲመጣ መንገድ ላይ ቀረ። ላይመለስ ምድርን ተሰናበተ።
.
.... ፎዚያ ትእግስት አሳጥቷታል። የህይወት አጋሯ ፤ ከራሷ አስበልጣ የምትወደዉ ሀቢብ ሞቷል። ሳትወድ በግዷ አምና ተቀብላለች። ከዚህ በኃላ ሀቢብን በድጋሜ አታገኘዉም። ፍቅሯ እንደ ጧት ጤዛ ሆኖ ቀረ። ያ እንክብካቤና ደስታ በጅምር ቀረ። ዉስጧ ተብሰከሰከ ፤ ያ የዉበት ጸዳል የሆነዉ ፊቷ ሀዘን የሚባል መጥሮ ነገር ፤ ሞት የሚባል የማይለመድ ክስተት ጥላዉን አጥልተዉበት ከጥቀርሻም በላይ ጠቆረ። እንደ ማለዳ ወፍ ዜማዎች የሚያምረዉ ድምጿ ተኩረፈረፈ ፤ ልሳኗ ተዘጋ። ሀቢብን በስስት የምታይበት አይኖቿ .. በርበሬ የተቦካበት ሙሃቻ ይመስል ቀይ ሆነ። ...
... በዚህ ምድር እጅግ ከባዱ ነገር የሚወዱትን ሰዉ መለየት ነዉ። ፎዚያ ግን ያን ሁሉ የችግር ወቅት ከሀቢብ ላለመለየት ታግሳና ችላ ኖራ ነበር። የሰቆቃዉ ህይወት አልፎ የደስታዉ ዘመን ሲመጣ ደስታዋን የሚያጠፋ ፤ ፍቅሯን የሚያከስም ነገር ተፈጠረ።... ሀቢብ ሞተ!!!
.
.
.
... የሀቢብ የቀብር ስነ ስርአት ከተፈጸመ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን አስቆጠረ። ፎዚያ ሊያስተዛዝኗት በሚመጡ ሰዎች ተከባለች። ሁሉም 'አብሽሪ' ይሏታል። ሞት በሁሉም ሰዉ ላይ ያለ ነዉ። እኛም ተራችንን ጠባቂዎች እንጂ ይህችን ምድር ለዝንታለም አንኖርባትም። አድርን የማንዉልባት ፤ ዉለን የማናድርበት ጠፊ አለም ናት!። እያሉ ይመክሯታል። እሷ እንደሆነ ሀቢብን ብቻ ሳይሆን ፍቅሯንም ከባሏ ጋር አብራ ቀብረዋለች። አንድ ቀን በትክክል ያጣጣመችዉን ፍቅር በድጋሜ ሳታገኘዉ መንገድ ላይ ቀርቶባል። የሚደፈያስተዛዝኗት ሰዎች ያወራሉ እንጂ እሷ ሀሳቧ ሁሉ ከሟች ባሏ ጋር ነዉ።
.
.
... ሀምዛና መኪያ ከአንድ ጥግ ተቀምጠዉ ፎዚያን አሻግረዉ ይመለከቷታል። ዉበቷ ሀያ አራት በሙሉ እንደ ጨረቃ ሲያበራ የነበረችዉ ፎዚ ሳትሆን ሀዘን እንዳይሆኑ አድርጓታል። ሀምዛ ወደ ፎዚያ ተጠግቶ ሊያስተዛዝናት ፤ ሊያጽናናት ድፍረቱን አጣ። እሷ ዘንድ ሂዶ ስለ ሀቢብ አንስቶ 'አብሽሪ' ቢላት ሁለታቸዉም አይኖቻቸዉ በእንባ እንደሚሞሉና ትዕግስት እንደሚያጡ ዉስጡ ነግሮታል።
በተቀመጠበት ሆኖ አሻግሮ እያያት ስለ'ሷ የወደፊት ህይወት 'ብቸኝነትና ሀዘን' እንደሚበረታባት ሲያስብ እንዴት አድርጎ ሊረዳት እንደሚችል ማስተንተን ጀመረ። ... የሱ ህይወት አያስጨንቀዉም። ምክንያቱም ቤቱ በደስታና በፍቅር የተሞላ ነዉ። እግሩም ቢሆን ደህና ነዉ። ለተወሰነ ጊዜ ክራንች ተጠቅሞ ይበልጥ ደህና ሲሆን የእስከዛሬዉን ሙሉዉን ሀምዛ እንደሚሆን ተነግሮታል ~ አልሐምዱሊላህ!!። አሁን የሚያስጨንቀዉ ጉዳይ የፎዚያ ነዉ። ስለሷ ያስባል... ያስባል.... 'ብቸኝነቷን እንዴት እንደሚያስወግድላት ፤ ከዚህ በኃላ እንዴት ደስተኛ እንደምትሆን እያሰላሰለ በሃሳብ ነጉዷል።... ጭል.....ጥ ብሏል።.....። በዚህ መሃል መኪያ ዘወር ብላ ስታየዉ ትካዜ ዉስጥ እንደሆነ አስተዋለች።
... "ሀምዚ .. ሀምዚ የነሰ..." ብላ ጠራችዉ።
... "ወይዬ መኪዬ.." ሲል መለሰላት።
... "ምን እያሰብክ ነዉ?" ብላ ከአይኖቹ ስለምን እንደሚያስብ ታዉቅ ይመስል ትክ ብላ አየችዉ።
... "መኪዬ የፎዚ የወደፊት ሁኔታ ግን አላሰሳሰበሽም?" ብሎ መልሶ እሷኑ ጠየቃት። መኪያም ስለፎዚያ ሁኔታ እያሰበች ነበር። ነገር ግን መፍትሄ ሳታገኝ ቀርታ ዝምታን መርጣ ነበር።
... "እኔምኮ አስቤዉ ነበር ሀቢቢ?" አለችዉ።
... "ብቸኝነት እንዳይሰማትና ደስታ እንዳይርቃት ምን እናድርግ የኔ ቆንጆ?" እያለ መፍትሄ ትነገረዉ ዘንድ በአይኖቹም ጭምር ተማጸናት። መኪያ ዝም አለች። ሀምዛም የሚስቱን አይን አይኗን እያየ ዝም ብሎ ከሷ መልስ ይጠባበቅ ጀመር።... በመካከላቸዉ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ዝምታ ከሰፈነ በኃላ መኪያ በሷና በሀምዛ አጠገብ የሚያወሩትን ፤ የሚነጋገሩትን የሚሰማቸዉ ሰዉ አለመኖሩን ካረጋገጠች በኃላ