ጦርነት እና ግጭት የፈተነው ትምህርት
የጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም
በጦርነት እና ግጭት ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት ከሚደርስባቸው ዘርፎች ትምህርት አንዱና ዋነኛው ነው። ከግጭት እና ጦርነት አዙሪት አለመውጣት ከሥርዓት ትምህርት ጥራት ችግር ጋር ተዳምሮ የትምህርት ዘርፉን ክፉኛ ጎድቶታል። ያለፉትን ዐሥር ዓመታት ብንመለከት የነበረው ግጭት እንዲሁም ጦርነት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ጫና በማሳደር የተማረ ትውልድ የማፍራት ጥረቱን ሲፈታተነው ኖሯል፡፡ በ2007 እና 2008 አካባቢ በተለይም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በተካሄዱ ሕዝባዊ አመፆች የተነሳ የመማር ማስተማር ሂደቱን በሰላም ለማስኬድ ሲያስቸግር ቆይቷል። ይህም ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሸፈነ ስለነበር ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጠባሳ ነበረው።
የተለየ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ተማሪዎች ተረጋግተው በመርሃ ግብራቸው መሠረት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንዳይወስዱ የተለያዩ ጫናዎችን አሳድረዋል፡፡ ይህም የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት እንዲሁም የመምህራንን የማስተማር ሥነ ልቡና በመጉዳት በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝም ሌላው የትምህርት ሥርዓቱን ሂደት ያስተጓጎለ ክስተት እንደ ነበር አይዘነጋም።
ከሁሉም በላይ የሰሜኑ ጦርነት በዘርፉ ላይ ያደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው። በጦርነቱ ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ የትምህርት ተቋማቱ ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል፡፡ የሰሜኑ ጦርነት ለተከታታይ ሦስት ዓመታት በአማራ ክልል የመማር ማስተማር ሥራ ይህን መሰል ጫና ፈጥሮ ቆይቷል። በእነዚህ ዓመታት ውስጥ የተከሰተው የተማረ ትውልድ ክፍተትም በቀላሉ የሚካካስ አይደለም።
በዚህ ሁኔታ ውስጥ የቆየው የአማራ ክልል የመማር ማስተማር ሥርዓት ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ የባሰ ስብራት ደርሶበታል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በክልሉ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ግጭት ነው። ትምህርት ቤቶችም ተማሪዎ ቻቸውን በትምህርት መርሃ ግብር መሠረት እየመዘገቡ ማስተማር ተቸግረዋል።
የትምህርት ሥርዓት የዛሬን ብቻ ሳይሆን የወደፊቱ ትውልድ እጣ ፋንታ ላይ የሚወሰንበት በመሆኑ በልዩ ትኩረት መገንባት ያለበት ዘርፍ በመሆኑ ይህን ለማሻሻል በርካታ ስራወች እየተሰሩ ነው።
በችግር ውስጥ ሆነውም የተማሪዎችን ምዝገባ ከማስቀጠል ጎን ለጎንም የማካካሻ መርሃ ግብር በማውጣት ተማሪዎችን ለማገዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ከበኩር ጋር ቆይታ ያደረጉ የዞን የትምህርት አመራሮች ነግረውናል። ከበኩር ጋር ቆይታ ያደረጉት የምዕራብ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ መኩሪያው ገረመው ዞኑ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምንም አይነት የመማር ማስተማር ሥራ አለመካሄዱን አውስተዋል። ይህም ተማሪዎችን ሀገር አቀፍ እና ክልል አቀፍ ፈተናዎች እንዲያልፏቸው ስለማድረጉ ገልፀዋል።
በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ደግሞ ሰላም ባለባቸው በተለይም በከተሞች አካባቢ ትምህርት ለማስጀመር ምዝገባ ተካሄዷል ብለዋል። በትምህርት ዘመኑ ከ396 ሺህ በላይ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ታቅዶ እንደነበር ያስታወሱት ምክትል ኃላፊው መመዝገብ የተቻለው ግን ከ19 ሺህ አምስት መቶ የማይበልጥ መሆኑን አሳውቀዋል። ተመዝገበው መማር ከነበረባቸው ከ269 ሺህ በላይ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ውስጥ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም የተመዘገቡት ከ13 ሺህ አምስት መቶ የማይበልጡ ናቸው። ስልሳ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የሚጠበቁበት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ውስጥም የተመዘገቡት ሦስት ሺህ 700ዎቹ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ግጭቱ የመማር ማስተማር ሂደቱን እየጎዳው ነው የሚሉት አቶ መኩሪያው
ዞኑ ከአሁን በፊት በትምህርት የተሻለ ውጤት ከሚመዘገብባቸው አካባቢዎች ውስጥ አንዱ ነው። ይሁን እንጂ አሁን ይህንን ፀጋውን በሚያሳጣ ሁኔታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ ገልፀዋል። ከመማር ማስተማሩ መቋረጥ በተጨማሪ 167 ትምህርት ቤቶች በግጭቱ ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ቤተ መፅጻሕፍትን እንዲሁም ቤተ ሙከራዎችን ጨምሮ ቁሶቻቸው እንደወደሙ ነግረውናል። የወደመው ንብረትም ከ639 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነው ብለዋል።
የመማር ማስተማር ሂደቱ በተረጋጋ ሁኔታ አለ መቀጠሉ የተማሪዎችን፣ የወላጆችን እና የዘርፉን ባለድርሻዎች የሚጎዳ ስለመሆኑም ይናገራሉ። የትምህርት ሥራ ውጤቱም ጉዳቱም በአጭር ጊዜ የማይታይ በመሆኑ አሁን እየደረሰ ያለው ጫና ከዓመታት በኋላ የትውልድ ክፍተት የሚፈጥር ነው ብለዋል። ዘርፉ የሁሉንም ትብብር የሚጠይቅ በመሆኑም ሁሉም ከፖለቲካዊ እሳቤ በወጣ መልኩ የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል። አሁንም ምዝገባዎች እንደሚቀጥሉ እና መዘግየታቸውን የሚያካክስ መርሃ ግብር እንደሚወጣላቸው ገልፀዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ የትምህርት ስታትስቲክስ፣ ስልጠና፣ ዕቅድ ዝግጅት እና ሀብት ማፈላለግ ቡድን መሪ አቶ አህመድ አደፋ በበኩላቸው የዞኑ የመማር ማስተማር ሥራ በተከታታይ ዓመታት በተካሄዱ ጦርነቶች እንዲሁም ግጭቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ገልፀዋል። እንደ ቡድን መሪው ገለጻ በዞኑ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ከሚያስተምሩ አንድ ሺህ 241 ተቋማት ውስጥ እየሠሩ ያሉት 790ዎቹ ናቸው። አንደኛ ደረጃ ትምህርት ከሚሰጡ አንድ ሺህ 211 የትምህርት ተቋማት ውስጥ እያስተማሩ ያሉት 833 ናቸው። በቅድመ አንደኛ 24 ሺህ ተማሪዎች፣ በአንደኛ ደረጃ ከአንድ መቶ 88 ሺህ በላይ፣ በሁለተኛ ደረጃ ከአንድ መቶ ሰባት ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ እንደሆኑ ቡድን መሪው ገልዋል። ዞኑ ከሰሜኑ ጦርነት ጠባሳ ሳያገግም ሌላ ግጭት መፈጠሩ የመማር ማስተማር ሥራው ከፍተኛ ጫና እንዳደረሰበትም ተናግረዋል።
በችግር ውስጥ ተሁኖም ታዲያ አሁንም ድረስ የምዝገባ ሂደቱን በዙር በማድረግ እና መርሃ ግብሩን በማመቻቸት ተማሪዎችን ለመደገፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አስረድተዋል።
ከበኩር ጋር ቆይታ ያደረጉት የምዕራብ ጎጃም እና የደቡብ ወሎ ዞን የትምህርት አመራሮች ዘርፉ ከፖለቲካዊ ፍላጎት ውጪ የሆነ ትኩረት የሚሻ በመሆኑ ሁሉም እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።
(ዘመኑ ታደለ)
በኲር የጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም