🌻 መንፈሳዊ ሥነ-ጹሑፎች🌻


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ያን አስተምሮን እና ሥርዓትን የጠበቁ መንፈሳዊ ግጥሞችን፣ መነባንቦችን፣ ትረካዎችን፣ ዜናዎችን ፣ደብዳቤዎችን፣ ትምህርታዊ ጹሑፎችን፣ ብሂለ አበው፣ ከመጽሐፍት ዓለም እና ሌሎችም ''መንፍሳዊ ሥነ-ጹሑፎችን'' ያገኛሉ።
.
.
.
ሃሳብ አስተያየታቹን ወይም ቻናሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ-ጹሑፎች ለመደገፍ @kal002 ላይ አድርሱን።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱


📕'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>✞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት የሰርግ ደግሶ የነበረው  ማን ነበር ?
     




#ኪዳነምህረትእጠራሻለሁ*

በኃጢአት ብወድቅም ባንቺ እነሳለሁ
ስላለሽ ኪዳነ ተሰፋ አደርጋለሁ
ገብቶልሻል ኪዳነ ኪዳነምህረት
ባንቺ ምልጃ ሊምር ይሁን ሁሉ ፍጥረት
በአንቺ ንፅህና ዓለሙን ታርቆታል
ያንቺን ስጋ ለብሶ እኛን አድኖናል
ባጠባሸው ጡትሽ ማር በይው ይማረን
አሳስቢው ድንግል ሆይ ረሃብ ጥምሽን
ዛሬም ይምረናል በሰጠሽ ኪዳን
ከእግርሽ ስር ወድቀናል ድንግል አሰታርቂን
ኪዳን ቃልኪዳንሽ ዘውትር ይጠብቀን።

➴ከእህተ ማርያም

#እንኳን ለቃል ኪዳኗ እመቤት መታሰብያ በአል በሰላም አደረሳቹ

➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴
@MENFESAWItsufoche
👆👆👆👆👆👆👆👆👆




ትንቢተ ዮናስ
ምዕራፍ ፬
የተናገረው ቃል ስላልተፈጸመ
ዮናስ ተቆጥቶ እያጉረመረመ
እንደዚህ እያለ ጸለየ ወደ አምላከ
እኔን መጀመሪያ ነነዌ ለመላክ
አሰብህ በታዘኝ ይህንኑ አውቄ
ወደ ተርሴስ ልሄድ ጠፋሁ ተደብቄ
ምሕረት የበዛ መሓሪና ታጋሽ
በደል የምትረሳ ከቁጣ ተመላሽ
የቁጣህን ያህል ምሕረትህ የጸና
መሆንክን ጥንቱን እኔ አውቃለሁና
እኔን ግን ግደለኝ ልሙት ልቀበር
ሐሰት ተናግሬ የማይሆን ነገር
አልፈልግምና ቆሜ ለመኖር
ከከተማ ወጥቶ በምስራቅ በኩል
ከወደ ዳር ሆኖ ነነዌን ሲያሰተውል
ምን እንደሚያገኛት ለማየት ዮናስ
ሠርቶ ተቀመጠ አንድ ትንሽ ዳስ
እግዜር በጥበቡ አንድ ቅል አብቅሎ
ቅሉም እንደገና ከፍ ከፍ ብሎ
የዮናስ እራስ እንዲያገኝ ጥላ
ለጸሓዩ ንዳድ ሆነለት ከለላ
በዚህ ብቅል ነገር ዮናስ ደስ አለው
እንዲህ ቶሎ ደርሶ ሲያገለግለው
እግዜር በማግስቱ ጧት በማለዳ
ቅል የሚበላ ትል ፈጣሪ አሰናዳ
ትሉ ቅሉን በልቶ በፋጥነት ደረቀ
ፀሐይ ወጣችና ጊዜው በጣም ሞቀ
እግዜር አዘዘና ትኩስ ንፋስ መጣ
የሚከለከልበት መጠጊያ ስላጣ
ቅሉ ደረቀና ንዳድ ቢያቃጥለው
ዮናስ ተበሳጭቶ ለአምላክ እንዲህ አለው
እንደዚህስ ሆኜ ቆሜ ከምኖር
እባክህ ግደለኝ ልሙት ልቀበር
ደረቀበኝ ብልህ ይህን ቅል ለመጣት
እውን ይገባል ወይ ያንተ አሁን መቆጣት?
ብሎ እግዜር ቢጠይቅ መለሰ ዮናስ
በንዴት ብዛት እስክሞትም ድረስ
አዎን ይገባኛል መናደድ መጨስ
እግዜርም መለሰ ለምን ጠፋ ስትል
ይህ ያልለፋሕለት ያልደምክለት ቅል
አንተ ስትናደድ ፈጥራያት እኔማ
ሳጠፋት ሳፈርሳት ነነዌን ከተማ
መቶ ሃያ ሺህ ነው የህዝቧ ብዛት
ለምን ትቆጣለህ እኔ ባዝንላት
ብሎ በምሳሌ ሲያስተምር ይቅርታ
ለዮናስ ነገረው የምሕረት ጌታ
ለእግዚአብሔር ቸርነት ምስጋና ይደረስ
በዚህ ተፈጸመ ትንቢተ ዮናስ።
\= ተፈፀመ = /

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

* ከክቡር አቶ ከበደ ሚካኤል" የቅኔ አዝመራ" የተወሰደ 1956 ዓ.ም
➴➴➴ እንሆ የነነዌ ፆምም ተፈፀመ የነነዌን ሰዎች ልመና ተቀብሎ በምሕረት እንደጎበኛቸው እኛንም በምሕረቱ ይጎበኝን ለሀገራችንምም ሰላም ለህዝቦቿም ፍቅር አንድነትን ቁጣውን እና መአቱን መልሶ በምሕረቱ ብዛት ይመልከተን ይቅር ይበለን!!!
አሜን 🙏🙏🙏

➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴
@MENFESAWItsufoche
➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴


ትንቢተ ዮናስ
ምዕራፍ፫
ይህንን የኔን ቃል ስማና በቶሎ
ሄደህ ለነነዌ እንድትነግራት ብሎ
ደገመና እግዚአብሔር ዮናስን አዘዘ
ነነዌ ሊገባ ዮናስም ተጓዘ
ድምጹን ከፍ አድርጎ ነቢዩ ዮናስም
ከዛሬ ጀምሮ አርባ ቀን ድረስ
ነነዌ ጠፊነች ከስር ተገልብጣ
አለና ለፈፈ የእግዚአብሔርን ቁጣ
ሳያንገራግሩ ሁሉም ቢለምኑ
የነነዌ ሰዎች ተጨንቀው አዘኑ
ከትልቅ ጀምሮ ሕፃኑ ድረስ
ሕይወቱ የቆመች በሥጋ በነፍስ
ሰውም ሆነ እንስሳ ይቀበል ንስሐ
ፍጡር ሁሉ ይጸልይ ይጹም ከእህል ውሃ
ሁሉም ከልብ አዝኖ ማቅ እየለበሰ
ከክፉ ወደ ደግ እየተመለሰ
መቼም ወሰን የለው የእግዚአብሔር ምሕረቱ
ይጸልይ አለና ይለምን በብርቱ
ንጉሡ አሳወጀ ከነ መኳንንቱ
የነነዌ ሰዎች በእውነት ከልቦና
መፀፀታቸውን እግዚአብሔር አየና
ፍጡር ቢለምነው እምባ እያፈሰሰ
ምሕረቱን አውርዶ መአቱን መለሰ።
ይቀጥላል...

➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴
@MENFESAWItsufoche
👆👆👆👆👆👆👆👆👆


ትንቢተ ዮናስ
ክፍል ፪
ዮናስም ተውጦ በእግዚአብሔር ፍቃድ
ሶስት ቀን ሶስት ለሊት ሊያድር በዓሣ ሆድ
ተቀይመህ ኖረህ ከላይ ብትቆጣ
እንዲህ ያለ መአት በራሴ ላይ መጣ
የባሕሩ ሞገድ እኔን አዋከበኝ
ውኃና ጨለማ ሲኦልም ከበበኝ
እያለ በአሳ ሆድ ዮናስ ሲቀመጥ
አምላኩን ለመነው በመለማመጥ
የታዛዥነትም ጠባይ እያሳየ
አዝኖ ተጸጽቶ ከልቡ ጸለየ
ምንጊዜም ቢቆጣ ነውና መሓሪ
ፊቱን መልሶለት ታረቀው ፈጣሪ
ዓሣውም ዮናስን ውጦ ሳያስቀረው
ከባሕር ተፋና መሬት ወረወረው

ይቀጥላል.....

➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴

@MENFESAWItsufoche
➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴


፨ትንቢተ ዮናስ፨
ክፍል ፩
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በሕዝቡ መካከል አመጽ ስለ ጸና
በጣም ተቆጥቼ አዝኛለሁ እና
ይህንን ለነነዌ ንገራት በአዋጅ
አለና ለዮናስ ለአሚታይ ልጅ
እግዚአብሔር አዘዘው እንዲሄድ በቶሎ
ዮናስ እቢተኛው አሰበ ኮብልሎ
ከአምላኩ ተደብቆ አምልሎ ሊጠፋ
ወደ ተረሲስ ሲጓዝ የሄደ ወደ ያፋ።
ዋጋ ክፍልና ከመርከብ ተሳፍሮ
እያጉረመረመ ባሕሩን ተሻግሮ
ዮናስ ተደብቆ ሲሄድ በግስገሳ
ከእግዚአብሔር ተልዕኮ ማዕበል ተነሳ
ታላቅ ሞገድ ሆነ ባሕሩ ተቆጣ
መርከበኞች ፈሩ ታላቅ ሽብር መጣ
መርከቡ እንዲቃለል እናድርግ እያሉ
አንስተው ብዙ ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉ
ባህሩም ባሰበት በጣም ተናወጠ
መረከቡ መሰለ የተገለበጠ
ሰው ሁሉ ተነሳ ጸሎት ለማድረስ
ይኽ ሁሉ ሲሆን ተኝቷል ዮናስ
ወደ ዮናስ ሄዶ የመርከቡ አለቃ
ቀሰቀሰው እና ከእንቅልፉ ሲነቃ
እግዜር እንዲያድነን ከዚህ ክፉ ጥፋት
ተነስ ጸልይ አለው ይብቃህ ማንቀላፋት
በመርከቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ተሰብስበው
ተመካከሩ እና ቢናገሩ አስበው
አለው ኃጢአት ሰርቶ ከእኛ ጋር የመጣ
ለይተን ለማወቅ እንጣጣል ዕጣ
አለዚያ አንድንም ስለተባባሉ
ተሰባሰቡና ዕጣ ቢጣጣሉ
እውነትም እንዳሉት አጥፊው ሰው ታወቀ
በእንቢተኛው ነብይ በዮናስ ወደቀ
በዮናስ ተረዳና እጁ እንደ ተያዘ
ያጠፋውን ጥፋት ገልጦ ተናዘዘ
ምነው ባትመጣ ተጣልተክ ከጌታ
እየው መርከባችን እንደሚንገላታ
ቁጣውን እንዲታገስ ለማግኘት ጸጥታ
በል አንተው ፍረደን ምን ይበጃል ቢሉ
ዮናስ መለሰና እዚህ ያለ ሁሉ
ስለምን ይጠፋል በእኔ የተነሳ
ወደ ባሕር ጣሉኝ አለብኝ አበሳ
ተመልከቱ እንሆ ስራውን ዐወቀ
ጥፋቱን ገለጠ ይኽው መች ደበቀ
እሱ ከፈረደ መልሶ በራሱ
ምን እናድርግ ብለው ሊጥሉት ተነሱ
ከደሙ አንጻን ሲሉ ለእግዜር አመልክተው
ወደ ባሕር ጣሉት ዮናስን አውጥተው
በዮናስ ላይ ኖር የመጣው ይህ ጥፋት
ባሕሩ ጸጥ አለ ልክ በዛው ሰዓት


ይቀጥላል.....

➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴

@MENFESAWItsufoche

➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴


፨ፆመ ነነዌ፨
የነነዌ ፆም በነገው ዕለት ይጀመራል ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደ ነነዌ ህዝቦች መዓቱን በምህረት እንዲለውጥለን ስለሀገራችን ስለቤተክርስቲያናችን አብዝተን እንፀልይ!
ለነነዌ ህዝብ የተለመነ አምላክ ለእኛም ይለመነን አሜን!!!
⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅
@MENFESAWItsufoche
👆👆👆👆👆👆👆👆👆


አስተርዮ ማርያም

አስተርዮ ማርያም ስልሽ ደስ ይለኛል
የመገለጥ ሚስጥር ተከናውኖልኛል
ገና ልጅም ሆኜ አሰተርዮ ሲባል
እሰማ ነበረ እስኪደርስ ያጓጓል።
አሁን ትልቅ ሆኜ ታሪኩ ሲገባኝ
የመድሃኔ ምክንያት ተስፋዬ የሆንሽኝ።
የሆነውም ሆነ እሱ የወሰነው
የአምላክ እናት ሆነሽ ሞትን እንድትቀምሽው።
የአዳም ልጆች ጠላት አስደናቂው ሞትም
ወረደ ወደ አንቺ ግዳጁን ሊፈጽም
እረፍት እንጅ ላንቺ ሞት ባይስማማም።
ሞተች ሲባል ሰምተው የአንቺ አሟሟትሽ
መጡ ከያሉበት በእሳት ሊያቃጥሉሽ።
መሆንሽን እረስተው የፈጣሪ እናት
ክብር እንደ መስጠት በስህተት ላይ ስህተት።
ነገሩንም ጭረው ወደ ኋላ ሲሉ
ቅደም ታውፋኒያ አንተ ጀግና እያሉ
ታውፋንያ ሞኙ በእሳት ሊያቃጥላት
የተዘጋጀውን ስጋዋ እንዲያርፍበት
የአልጋውን ሸንኮረ ሲነካ በድፍረት
ምንም ሳያስበው መላኩ በቅፅበት
ሁለቱን እጆቹን በሰይፍ ቆረጠለት።
ይህ ነው መጨረሻው ማን አለብኝ ማለት
ያ ሁሉ ፉከራ መሬት ገባ ድንገት
አይ የሰው ልጅ አቅም ያሳዝናል በእውነት።
እጆቹ እንዲድኑም አማልጅኝ ማለት ነው።
እሱ መቼ አወቀ የእሷን ሕያው መሆን
ሞተች ሞተች ሲሉ ሲሰማ ወሬውን
መጣ እንጅ ዝም ብሎ ሲሰማ ወሬውን
መጣ እንጅ ዝም ብሎ ሊያቃጥል ስጋዋን።
የእኛም እናት ድንግል የማታሳፍረው
የሞተች ብትመስልም ህያው የሆነችው
አማላጅነቷን አሳያችው ወዲያው
እጆቹን ቀጥላ ስለ ሆኑ ህያው።
እንዲህ ናት የእኛ እናት ጠላቶቿን የምትወድ
ማርያምን ይወቃት የማያውቃት ትውልድ
በጦር የወጋውን አይኑን እንዳበራ ልጇ መድሃኔዓለም
ልጇ እንዳደረገ አደረገች እሷም
ስሟ ማር ወለላ ፍቅር ናት የእኛ እናት
የማያውቅ ይወቃት የሚያውቅም ያክብራት።

ስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።

✧✧✧ ሞት በጥር ነሃሴ መቃብር እንዴት ይደንቃል✧✧✧


እንኳን ለአስተርዮ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ አደረሰን !


➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴

@MENFESAWItsufoche

➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴


*የቃናዋ እመቤት*
ወይን ጠጁ ሲያልቅባቸው፤
የሚያደርጉት ሲጠፋቸው፤
መች ዝም አለች እናታቸው፤
እመብርሃን መውጫቸው።
የዶኪማስ ባለውለታ፤
የአገልጋያቹ ትዝታ፤
የእድምተኞቹ እርካታ፤
የሓዋርያት አለኝታ።
የምልክቶች መጀመርያ፤
ሲያደርጋት ልጇ አክብሮ፤
ለእኛ እንድትሆን አዘክሮ፤
ሲለመነን በእሷ ላይ አድሮ፤
ፈጥኖ ሰማት በአንክሮ።
የቃናዋ እመቤት አማላጅዋ፤
የማይቋረጠው እርዳታዋ፤
የማይቆጠረው ስጦታዋ፤
የማይለካው ዋጋዋ፤
ልጆቼ ትለናለች፤
በፍቅሯ እየሳበች፤
በክንዷ እያቀፈች፤
ልታወጣን ከዓለም፤
ወድቀን እንዳንሰምጥ፤
ልትመራን ደግፋ፤
ልትሆነን የኛ ተስፋ፤
ልትታደገን እንዳንጠፋ።
ከተፍ አለች ፈጥና፤
መላእክተ ብርሃንን አስከትላ፤
እየመራች ልታደርሰን፤
የገነትን ደጃፍ ልታሳየን፤
አይ እመቤቴ እሩህሩሃ፤
መቼ ያልቃል ደግነቷ፤
ይፈውሳል መድሃኒቷ፤
ለአመነባት በአማላጅነቷዋ።
ተራው ውሃ ተለውጦ፤
ስም ተሰጥቶት ፀብል ተብሎ፤
እውሩን እያበራ፤
ጎባጣውን እያቀና፤
አንካሳውን እየረታ፤
ለምፃሙን እያነጻ፤
ዲያብሎስን እየቀጣ፤
መግቢያ መውጫ እያሳጣ፤
የቃናው ውሃ ዛሬም አለ፤
የድንግልን ትዕዛዝ እየተቀበለ፤
እስከ ምጻት ሳይቋረጥ፤
ድህነት ሰላምን ለኛ ሊሰጥ።

✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
✨✨✨✨✨✨✨✨✨
@MENFESAWItsufoche
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤


፨እናምናለን በምስጢረ ጥምቀቱ፨
በመጋቤ ምስጢርነቱ
በመንግሥተ ሰማይ በርነቱ
ሰው ካልተወለደ ከውኃና ከመንፈስ
ሕይወት እንደሌለው ርስት እንደማይወርስ
ያመነ የተጠመቀ ይድናል
በጥምቀቱ ልጅነት ያገኛል
ባያምን ባይጠመቅ ከልጅነቱ ይወጣል
ኢጥዮጵያዊው ባኮስ በሐዋርያው በፊሊጶስ
ከነቤተሰቦቹ እስጢፋኖስ
ቅዱስ ጳውሎስ ከደማስቆ መልስ
በጥምቀት ተወልደዋል ከመንፈስ ቅዱስ
ሔዋን በሰማንያ አዳም በአርባ ቀኑ
ገነት እንደገቡ ልጅነት እንዳገኙ
ሴቶች በሰማንያ ወንዶች ደግሞ በአርባ
ልጅነት እንዲያገኝ ተጠምቆ እንዲገባ
እናምናለን በእውነት
ያለጥርጥር በእምነት፡፡
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤
@MENFESAWItsufoche
✤✤✤✤✤✤✞✤✤✤✤✤✤


፨ዮርዳኖስ፨

...የቀጠለ
እየሱስ ሲጠመቅ በዮሐንስ እጅ
ሰማያት ተከፍተው ቃል ሲመጣለት
መንፈስ ቅዱስ መጥቶ በራሱ ላይ ሲያርፍ
የምወደው ልጄ ይህ ነው ስሙት
ተብሎ ሲነገር ከእግዚአብሔር አብ
የስላሴ ምስጢር በዮርዳኖስ ባህር
ተገልጾ ነበር የአንድነት ምስጢር
አንድነት ሶስትነት ያለመከፋፈል
ሰዎች ሲጠመቁ በስላሴ ስም
የእግዚአብሔር ልጅነት ያገኙ ነበር
ታዲያ ምን ይባላል የአሁኑ ትዕቢት
ስላሴ ምንድ ነው ብሎ መደንፋት
ኢየሱስ አንድ አካል ፍጡር ነው ማለት
ልበ ቆሻሻዎች የክርስቶስ ጠር
ጆረአቸው ተደፎኖ ልባቸው ቢዝል
በዮርዳኖስ ታይቷል የአንድነት ምስጢር
የወደደ ይምጣ የጠላ ይመለስ
አይከለስ እንደው የዮርዳኖስ እውነት
ከባህሮች ተመርጠሽ ዮርዳኖስ የታደልሽ ምስጢር ስላሴ የተገለፀብሽ
አንቺ ሰፊ ምድር ዮርዳኖስ መስክሪ
የተጠመቀብሽ የዓለም ፈጣሪ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳቹ!

➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴
@MENFESAWItsufoche
➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴


፨መንፈሳዊ ዜና፨
🔖 የጥምቀት በዓል በመምጣቱ ጫማዎች ደስተኛ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
ዝርዝሩ እንደሚከተለው ይቀርባል።
ከተለያየ አይነት ከኤርገንዶ እስከ አንበሳ ጫማ ያሉ ጠቅላላ ጫማዎች ባካሄዱት ስብሰባ እና ባወጡት የአቋም መግለጫ እንደገለጹት ከሆነ የጥምቀት በዓል በመምጣቱ በጣም ደስተኞች ነን ለአባቶቻችን ለሰው ልጆች እንኳን መላ አካላችሁ ከኃጢአት ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ለሚያርፍባት የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ማለት እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
የጉባኤው አስተባባሪ የሆኑት ሸራ ጫማ ጉባኤውን ለማካሄድ ያነሳሳችሁ አቢይ አላማ ምንድን ነው ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡ እኛ ይህን ስብሰባ እንድናካሂድ እና ደስታችንን እንድንገልጽ ያደረገን ዋናው ምክንያት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የምንመጣበት ጊዜ የለንም አለቆቻችን ከጽድቅ ይልቅ ኃጢአትን፣ወደ ቅድስና ስፍራ ከመሄድ ወደ ጭፈራ መሄድን ስለሚመርጡ እኛ አምላካችንን የምናመሰገንበት ጊዜ አጥተን ጨንቆን ነበር ነገር ግን በዚህ በጥምቀት ወቅት ምእመናኑ በወረት ወደ ቤተ ክርስቲያን ስለሚመጣ እኛም በዚያው በረከት ስለምናገኝ ነው ብለዋል፡፡በስተመጨረሻም አቶ ሸራ በሰጡትሁ አስተያየት እባካችሁ የሰው ልጆች አምላካችሁን አትዘንጉት ቅድስናችሁን አታርክሱት እግሮቻችሁ ሁሌም እኛን ተጠቅመው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ይገስግሱ ከኃጢአት ይሽሹ ለኛም በረከት ይትረፈን ሰሉ አስተያየታቸውን አጠናቀዋል፡፡

➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴
@MENFESAWItsufoche
➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴


"ዮርዳኖስ"
/መነባንብ/

አንቺ ሰፊ ባህር ዮርዳኖስ መስክሪ
የተጠመቀብሽ የአለም ፈጣሪ
ትንቢት መነገሩ በዳዊት ነብይ
ድምፅ በውኖች ነው ብሎ መመስከሩ
በውኖች ይታያል ብሎ መዘከሩ
በዩርዳኖስ መሸሽ ትልቁ ሚስጥር
የዩርዳኖስ ባህር አምላኩን ማክበሩ
በጥልቅ ውሃዎች ላይ ስልጣን አለው ሲሉ
አምላክን ማክበሩ ፈርቶ መንቀጥቀጡ
ሰዎች ሳይረዱ ወንዙ መረዳቱ
የዳዊት ትንቢት ትውልድ መዘንጋቱ
ምን ይባላል አሁን እውነትን መሣቱ
ሰው መዳኑን ንቆ እንዲህ መቅበዝበዙ
ዳዊት ለምን ሸሸ ብሎ የጠየቀሽ
ባህረ ዮርዳኖስ ፈጣሪሽን አወቅሽ
ኧረ አንቺ ዮርዳኖስ ኢያሱየከፈለሽ
ሕዝበ እስራኤን በአንቺ ያሻገረብሽ
ከዕለቱ ክርስቶስ ውሃ ያጠጣብሽ
ኤልሳና ኤልያስ ደግሞ የቆሙብሽ
ለመጎናፀፍያ ከፍለው ያለፉብሽ
ንዕማር ሲጠመቅ ከለምጹየነፃብሽ
ሰው የሆነ ንጉስ ባንቺ ሲታይብሽ
ይህ ሁሉ ሲደረግ ትግሉ ሲሰምርብሽ
ዩሐንስ ሲያጠምቅ መድህን ሲመጣብሽ
እራሱን አዋርዶ ባንቺ ሲታይብሽ
ወልድ አምላክ በክብር ሲጠመቅ በውስጥሽ
እርጥበትሽ ሳይደርቅ እሳቱ ሳይፈጅሽ
ዮርዳኖስ ድንቅ ነው ጸንተሽ መገኘትሽ
ይመሰክር ጀመር ዩሐንስ ተረድቶ
የእግዚአብሔር በግ መጣ ይኽው ብሎ
እኔ አላውቀውም ጥንትም ነበር ደግም
አለ መስከር እውነት ተናገር
በእሳት የሚያጠምቅ ይመጣል እያለ
ታዲያ እንዲህ ሰዎች ሲጠመቁ
መድሐኒት ብቅ አለ ከወደ ጥምቀቱ
በዮሐንስ እጆች ሊጠመቅ ፈልጎ
ዩሐንስ አዘነ እጅግ ተፀፀተ
አምላከ ሰማይን እንዴት ላጥምቅ ብሎ
ፅድቅን ለመፈፀም ወዲህ መጣሁኝ
ብሎ ሲያስተምረው መድሐኒዓለም
ያጠምቀው ጀመረ በእሽታ መንፈስ
ይቀጥላል...

እንኳን ለከተራ በዓል መዳረሻ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!

➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴
@MENFESAWItsufoche
➴💝➴💝➴💝➴💝➴💝➴


፨መንፈሳዊ ዜና፨

ለዘመናት በሰው ልጆች እና በዲያብሎስ መካከል የቆይው የትግል ውድድር በክርስቶስ መወለድ ምክንያት ትግሉ በሰው ልጆች አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ይህም የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ንጽሕት ከሆነች ከድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር በቤተልሔም በከብቶች ግርግም በመወልዱ ነው።በዚህም የነገስታት ንጉስ ኢየሱስ ክርስቶስ ለ5500 ዘመን በዲያብሎስ ቁጥጥር ስር የነበረውን ሪከርድ ሙሉ በሙሉ ሰባብሮ አዲስ ሪከርድ በትህትናው፣ በሃያል ፍቅሩ እና በቸርነቱ አስመዝግቧል። ይህም በመሆኑ የሰው ልጆች እና መላዕክት በአንድነት በደስታ የዘመሩ እና ያመሰግኑ ሲሆን በተቃራኒው ደግሞ ዲያብሎስ እና ዘረማንዘሮቹ በሙሉ በጥልቁ ሲኦል ሃዘን ተቀምጠዋል።
*ከቃልኪዳን ተፈራ

💝💝💝💝💝💝💝💝💝💝
@MENFESAWItsufoche
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


፨እልል የምስራች ክርስቶስ ተወልዷል፨
በተባረከችው በዚያች በውብ ምሽት
እረኞችም ሁሉ እደጅ ባደሩበት
ህፃን ተወለደ በከብቶች ግርግም ውስጥ
ቤዛ ሊሆን ኋላ ለዓለም ነፍሱን ሊስጥ
ጌታ ተወለደ የእስራኤል ንጉስ
ከአለም እርኩሰት ትውልድን ሊመልስ
እልል..!የምስራች ክርስቶስ ተወልዷል
ከእናቱ ከማርያም ከማህፀኗ ወጥቷል።
በዚያች ቅድስት ለሊት በከብቶች በረት ውስጥ በጨርቅ ተጠቅልሎ
በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን ለሰው ልጅ አድሎ
ሊያኖረን ተወልዷል የሠራዊት አምላክ አልፋና ኦሜጋ
ከእናቱ ከማርያም ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ከስጋዋ ሥጋ
እልል... የምስራች ኢየሱስ ተወልዷል
አለምን ከጥፋት ሊያድን ምድር ወርዷል
ከእግዜር የተላኩት ቅዱሳን መላዕክት ብሥራት አብስረዋል
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ሲሉም መዝሙር ዘምረዋል።
እኛም እስቲ እንዘምር እናሸብሽብላት በምሥጋና ዜማ
የጌታን መወለድ ያልሰማ እንዲሰማ የሰማ እንዲያሰማ።
እልል... የምስራች ክርስቶስ ተወለዷል
ከእናቱ ከማርያም ከማህፀኗ ወጥቷል።
❄❄❄❄❄❄❄❄❄
@MENFESAWItsufoche
👆👆👆👆👆👆👆👆👆


# ስንት ቀን ፈጀብህ?
/መንፈሳዊ መነባንብ /
-----------------✞-------------------
ለአዳም ኪዳን ሰጠህ
እንደምትወለድ ወደ ምድር ወርደህ
እንዴት ነበር ያኔ..?
ወደ እኛ ስትመጣ መላእክትን ትተህ?
………
የሔዋን እርግማን
የባሏም የውርስ ኃጢአት መዘገን
እንዲያ አሳሰበህና
መጣህልን ሁሉን አደረግህ በፅሙና
.........
እንዴት ነበር ያኔ..?
ያችን ንጹሕ ለመፈለግ የወሰደብህ ጊዜ
አድርገህ የሰጠኸንን ፈውስ በበድልን ጊዜ
ግን ምን ያህል ነው ልፋትህ?
ድንግልን ስትፈልግ የፈጀብህ?
.........
ከሰማያት ስትወርድ አጀቡህ መላእክት?
ዓለሙስ ተናወፀ በይባቤ በስብሐት?
ያ ምቀኛ ዲያቢሎስ ግን ምን አለ?
ወደ እኛ ስትመጣ አለ አይደል ኮበለለ?
ነው ሥጋ ለብሶ ጉድ ሠራኝ አለ?
........
እንዴት ነው እርቀቱ
የሰማይ ምጥቀቱ
የምድርስ ሥፋት
ከሷ እስክታርፍባት?
ግን ጌታ...?ሰማያት ምን አሉ
ትትሀቸው መጠህ ባንተ አጉረመረሙ?
ፍጥረታትስ ቢሆን ማሕሌት አቆሙ?
.......
ምሥጢረኛው ጌታ
መንገድህ በየት ነው ወደ እኛ ስትመጣ?
ቤተ ልሔም ስትደርስ
ማን አገለገልህ?ምን አለች ምድሪቱስ
እያቄም ወሐናን እንዴት መረጥሃቸው
አንተ እንድትወለድ ምክንያትህ ናቸው
.......
ሰማዩ ሰፊ ነው
ምድርንም ታውቃለህ
እንዴት እንድትሰፋ ሆና መረገጫህ
ግን እና ጌታ ሆይ ምኑ ነው የቻለህ?
የድንግል ማሕጸን እሳት መሸከሙ
ምድርም መልኮት በእሷ ላይ መቆሙ
..........
እንዴት ነበር ያኔ
በቤተ ልሔም ውስጥ
አንተን የሚያሞቅ ከእንስሶች ስትሰጥ?
........
ዮሴፍ ምን አለ
አንተን በማየቱ እርጅናው ታጎለ?
አንተን የጠበቀህ አዳምስ በግርማህ ምን አለ?
........
እንዴት ነው ስጦታው
የሰብአ ሰገሉ ወርቅ እጣን አምኃው
የእረኞቹ ደስታ
የመላእክት ብሥራት የልደትህማታ
.........
እንዴት ነበር ያኔ
የልደትህ ማታ
የዝማሬው ለታ
የእናትህ ደስታ
የፍጥረት እልልታ
ሚዳቋ ስትዘል ከኢትዮጵያ አይታ
ግን ጌታ እረቂቁ አምላክ
በየትስ መጠህ ነው ከኛ የተወለድክ


✞ስብሐት ለእግዚአብሔር ✞


*ከሮቤል ጌታቸው
💝💝💝💝💝💝💝💝💝💝
@MENFESAWItsufoche
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


፨ያኔ ጥንት ነበረ፨
በዱር በገደሉ በዓለም ዙርያ ሁሉ
አምላክ ይወለዳል ብለው ተናገሩ
የነቢያት ተስፋ የነበለአም
አምላክ ተወለደ መድሃኒዓለም
ያኔ ጥንት ነበር...
ይወለዳል ሲሉ በመንፈስ ሲመሩ
አምላክ አዶናይን ለማየት ሲጥሩ
እንደው ኩርምት ብለው በተስፋ ሲኖሩ
ድንግል ትፀንሳለች ብለው ሲናገሩ
ቀናትን ሲቆጥሩ ሳምንታት ሲሠምሩ
ሳምንታት በግንድ ላይ ወራትን ሲሠሩ
ወራት ተቀናጅተው ዓመትን ሲሰጡ
ዓመታት ተቆጥረው ዘመናት ሲመጡ
እናያለን ሲሉ ለማየት ሳይበቁ
በመንፈስ ሲሰክሩ እንዲውል ሲሳለቁ
ያኔ ጥንት ነበር....
ያኔ ጥንት ነበር በመንፈስ መሰከሩ
አምላክ ይወለዳል ብሎ መዘከሩ
በርቀት ተሳልሞ ለዓለም ማብሰሩ
ያኔ ጥንት ነበር የመውደቅ ሚስጥሩ
ሃጢአትን መፀነሱ የመውደቅ ሚስጥሩ
ሃጢያትን መፀነሱ ሞትንም መውለዱ
ከገነት ተባሮ እንዲያው መዋረዱ
ፀጋውን ተገፎ በለስ ማገልደሙ
ያኔ ጥንት ነበር...
አዳምን ሊጎበኝ አምላክ መጣራቱ
አዳም አዳም አዳም ብሎ መፈለጉ
አትብሉ ያልኩህን በላህው ማለቱ
አዳምን በመፍጠር እንዲያው መፀፀቱ
አዳምም አዘነ በሔዋን ፈረደ
ሔዋንም አዘነች እባቡ ነው አለች
እባብ ተረገመች አፈራ ባይሆናት
አዳም ተባረረ ሄዋን አለቀሰች
ምድር ተረገመች እሾህ አበቀለች
አቤት ያኔ ነበር ያኔ ጥንት ነበረ
አዳም መበደሉ ሰዎችን ለውድቀት ለሞት መደረጉ
ያኔ ነበር ፅንሱ ሰዎችን ለሽንፈት ለሞት መፈለጉ
ዛሬ ግን ዛሬ ያ የጥንቱ ቀረና
እራሱን አዋርዶ አዳም ከበረና
ሲወለድ በቤተልሔም በነብዩ ተፅፎአልና
አምላክ ተወለደ በከብቶች መና
ታሪኩ ሲተርክ የሰማህ ወንድሜ
ራስክን መርምረው ና ይልሃል ዛሬ
አቤት ያኔ ጥንት ነበር....
ያኔ ጥንት ነበር የአዳም ውድቀቱ
ዛሬ በክርስቶስ ሕይወትን ማግኘቱ
ዛሬስ እኛ ወገን
የያኔ የጥንቱ ትተን ለንስሐ ቀርበን
ስጋውንም በልተን ደሙንም ጠጥተን
በድያለሁ ብለን ከፊቱ ላይ ወድቀን
መመለስ ይሻላል ክርስቶስን ብለን
መመለስ ያሻል ኪዳነ ምህረትን ብለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳቹ አደረሰን!
ልደቱ ልደታችን ነው
መልካም በዓል

❄❄❄❄❄❄❄❄❄
@MENFESAWItsufoche
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.