አንዱ ሲራራ ነጋዴ ለንግድ ከሄደበት ሀገር ተመልሶ መንገድ ላይ ያገኘውን
የሀገሬውን ሰው ይጠይቀዋል
"እንደው እንደዛ እየፎከሩ ሀገሩን ሲያምሱት የነበሩት የቀኝ አዝማች እገሌ እና
የግራ አዝማች እንቶኔ ጦርነት መጨረሻው ምን ሆነ?" ይለዋል
"ወዴት ከርመህ ነው ጃል አልሰማህም ወይ?"
"አልሰማሁም ለንግድ ወጥቼ ከርሜ ዛሬ መምጣቴ ነው"
"አይይይ ጉድ አምልጦሃላ ጦርነቱማ ቀኝ አዝማች እገሌም ሸሹ ግራ አዝማች
እንቶኔም ተማረኩ" ብሎ ሲመልስለት ግራ ተጋብቶ
"አሃ እንዴት ያለ ነገር ነው ጃል?! በወግ በወጉ አድርገህ ንገረኝ እንጂ"
"ኧሯ እነሱ በወግ በወጉ ያልተዋጉትን እኔ እንዴት ብየ ላውጋህ?!"