የሱና መስጂድ ቻናል


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


♨{هل يستوي الذين يعلمون والذين لا يعلمون}♨
💥{የማያውቁ እና የሚያቁት እኩል ይሆናሉን}💥
💫ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ በመስጂደ ሱና የሚሰጡ:--
🔊የተለያዩ የኪታብ ደርሶች
🔊 የተለያዩ ሙሀደራዎች
🔊የጁምአ ኹጥባዎች
🌕የሚለቀቅበት ቻናል ነው አላህ ለኸይሩ ይወፍቀን🌕
✍️ሀሳብ አስታየት✍️
@mesjid_Al_sunnahbot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




قناة أبي المسيب حمزة بن رشاد الحبشي dan repost
هنيئا لمصطفى الولوي هذه السفاهة والطيش التي يغبطه عليها فساق الشوارع

فلقد لطم نفسه بنفسه وظهرت حقيقته لكل ذي عينين


كيف حال الدعوة في تنزانيا والحبشة.


للشيخ أبي عبد الرحمن محمد الزعكري الحجوري حفظه الله ورعاه


https://t.me/JOvnXjni/47457


🌷ከምንም ያልሆነ ጭንቅላት የሼጣን መጫወቻ ይሆናል❗️

   ✔️አንድ ሰው ወይ ለዲኑ ወይ ለዱንያው ካልተንቀሳቀሰ የሸይጧን መጫወቻ መሆኑ የማይቀር ነው።

📌እንደ እድሜ የላቀና ውድ የሆነ ነገር የለም❗️
እድለኛ ብሎ ማለት እድሜውን ዱንያ ላይ በሚጠቅመው ነገር አኼራ ላይ ደግሞ ከፍ ሊያደርገው በሚችል ነገር ላይ ያዋለው ነው።

   👉አስተዋይ ሰው ብሎ ማለት እድሜውን አሳሳቢና ዋሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚያውል ነው። በርግጥ ብዙ አሳሳቢ ነገራቶች አሉ ነገር ግን እድሜያችን አጭር ነች❗️ሁሉንም መፈፀም አንችልም። ግን ዋና ዋናውን
 
📌 ደስተኛ ሰው ማለት ሁሌ ነፍሱን በመልካም ነገር ፣ በሀቅ የወጠራት ነው
ነፍሱን በመልካም ነገር ካልወጠራት እሷ በመጥፎ( በባጢል  ) ትወጥረዋለች ይህ የማይቀር ጉዳይ ነው ።
👉ወደ ሚጠቅምህ ነገር ካልተጓዝ ወደ ሚጎዳህ ነገር ልትጓዝ ትችላለህ እናም ተጠንቀቅ❗️

📌አሁን ያለንበት ወቅት በተለይ በሀገራችን እንደ ጊዜ ርካሽ ነገር የለም እንደውም እንደ ጀብድ ጊዜያችንን እንግደል ሁላ ይባል አይደል❓።
  👉 በርግጥ ጊዜ ሊገድሉ የሚችሉ ነገራቶች በስፋት ተበትነዋል ተበራክተዋል ፣ ግማሹ በኳስ ፣ግማሹ በፊልም፣ ግማሹ በሙዚቃ ፣ ከፊሉ በደባል ሱሶች ተጠምዶ ጊዜውን እየገደለ ይገኛል አላህ የሰጠህን ይህን ውድ ስጦታ አላህ በማመፅ የምታሳልፈው ሰው ሆይ! ነገኮ ጥያቄ አለብህ ነገ አላፊት ቆመህ እነዚህን ጥያቄዎች ትጠየቃለህ

أَبِي بَرْزَةَ الأَسْلَمِيِّ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: لَا تَزُولُ قَدَمَا عَبْدٍ يَوْمَ القِيَامَةِ حَتَّى يُسْأَلَ عَنْ عُمُرِهِ فِيمَا أَفْنَاهُ، وَعَنْ عِلْمِهِ فِيمَ فَعَلَ، وَعَنْ مَالِهِ مِنْ أَيْنَ اكْتَسَبَهُ وَفِيمَ أَنْفَقَهُ، وَعَنْ جِسْمِهِ فِيمَ أَبْلَاهُ رواه الترمذي (2417)، وقال: ” هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ”
ነብዩ እንዳሉት አንድ ባሪያ የቂያማ እለት እነዚህን ነገራቶች ሳይጠየቅ ወዴትም አይንቀሳቀስም👇

📌እድሜውን በምን እንደጨረሰው
📌በእውቀቱ ምን እንደሰራበት
📌ገንዘቡን ከየት እንዳመጣውና ምን ላይ እንዳዋለው
📌ሰውነቱን በምን እንደጨረሰው


👉ኢብን መስዑድ አላህ ስራውን ይውደድለት እንዲህ ይላል፦
ابن مسعود رضي الله عنه يقول: "إني لأبغض الرجل أن أراه فارغا، ليس في شيء من عمل الدنيا، ولا عمل الآخرة" [حلية الأولياء:1/130].

📌እኔ አንድ ሰው ከዱንያ ስራ እንዲሁም ከአኼራ ስራ ውጪ ሆኖ ማየት ያስጠላኛል።


🌷ኢብኑል ቀይም አላይ ይዘንለት እንዲህ ይላል፦
👉"ነፍስን በሃቅ ካልጠመድካት በባጢል ትወጥርሃለች።
🫀 ልብህ ውስጥ የአላህ ውዴታ ካልኖረበት ያለጥርጥር የፍጡራን ውዴታ ይኖርበታል።

👅 ምላስህን አላህን በማውሳት ካልወጠርከው  በውድቅ ንግግርና በማይጠቅምህ ነገር መጥመዱ አይቀርም።
☝️ለነፍስህ ከሁለቱ የተሻለውን መስመር ምረጥና ከአንዱ ማረፊያ ላይ አሳርፋት።

📚አልዋቢል አሰይብ

✔️ኢብን አልቀይም እንዲህ አለ፦

(ከስራ) ነፃ ከመሆን ብዙ ብልሽት ይመጣል።
📌በባሪያው ላይ አውዳሚ እንደሆነ ሰንሰለት  ወንጀል ይከታተልበታል።
📌ኢማን ልቡ ውስጥ ይደክምበታል ከጌታውም ታርቀዋለች።
📌ከሚጠቅመው ስራ ነፃ የሆነ ሰው በሚጎዳውና በማይጠቅመው ነገር መወጠሩ አይቀሬ ነው።

👉ኢማሙ ሻፊዒ እንዲህ ብለዋል፦
"ነፍስህን በሃቅ ካልወጠርካት በባጢል ትወጥርሃለች።


👉https://t.me/AbuEkrima
https://t.me/mesjidalsunnah/16615


🎁የጁማዓ ስጦታ ለቤተሰቦቻችን

📖سورة الكهف | القارئ: الشيخ 
عمر الدريويز



☑️ዛሬ ጁመአ ነው ሱረቱል ክህፍ የቻለ ይቅራ ያልቻለ ያድምጥ።

🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16614


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
{ ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى
النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا
عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ }

💎 ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ,ﷺ 💎

#የሱና_መስጂድ_ቻናል

🕌የጁምዓ ግብዣ

🤲 اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم في العالمين إنك حميد مجيد...


🤲اللهم فرجا قريبًا عمن لا يسمع أنينهم
إلا أنت ....غزة


🕌ከጁሙዓ ቀን ሱናዎች💧

🛁ገላን መታጠብ
ጥሩ ልብስ መልበስ
☘ ሽቶ መቀባት(ለወንዶች ብቻ)
🕰በጊዜ ወደመስጂድ መሄድ
💐 በነብዩ - ﷺ - ላይ ሰለዋት ማብዛት
📖ከቻሉ ሱረቱል ከህፍን መቅራት
🤲ዱዓ የሚያገኝበትን ሰአት መጠባበቅ

🌸 በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ
🎙ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ,

🌸ሌላ ሰው ቢያወራም ዝምበል አለማለት


🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16613


إن من أفضل أيامكم يوم الجمعة'
فيه خلق آدم' وفيه قبض' وفيه النفخة' وفيه الصعقة' فأكثروا علي من الصلاة فيه فإن صلاتكم معروضة قالوا:يارسول الله كيف تعرض عليك صلاتنا وقد أرمت ـ أي بليت ـ قال: إن الله حرم على الأرض أن تأكل أجساد الأنبياء .
رواه أبو داود والنسائي وأحمد عن أوس بن أوس الثقفي وصححه الألباني

اللهم صل على محمد وأزواجه وذريته كما صليت على إبراهيم وبارك على محمد وأزواجه وذريته كما باركت على إبراهيم إنك حميد مجيد

https://t.me/Abu_Muhammed_MuhammedSed/4664
https://t.me/mesjidalsunnah/16612


قال شيخنا الشيخ أبو يوسف حبيب

للمرور علىٰ الصراط الحسي يجب الإستمرار علىٰ الصراط المعنوي.


🌺 እህቴ ሆይ አፈር አይደለሽምን ??? አስታውሺ !!

✔️ሀሩነ ራሺድ) ሊሞት ሲል ጊዜ በዙሪያው ለነበሩ ወንድሞቹ እንዲህ አላቸው ፦

« ቀብሬን ማየት እፈልጋለሁ » ቀብሩን ካየ በኋላ ዞር አለና ወደ ሰማይ እያየ በማልቀስ እንዲህ አለ ፦

🔸አንተ ንግሥናክ የማይወገደው አምላክ ሆይ ንግሥናው ለተወገደው ባሪያክ እዘንለት !

👈إِذَا الشَّمْسُ كُوِّرَتْ, وَإِذَا النُّجُومُ انكَدَرَتْ , وَإِذَا الْجِبَالُ سُيِّرَتْ , وَإِذَا الْعِشَارُ عُطِّلَتْ , وَإِذَا الْوُحُوشُ حُشِرَتْ , وَإِذَا الْبِحَارُ سُجِّرَتْ , وَإِذَا النُّفُوسُ زُوِّجَتْ , وَإِذَا الْمَوْؤُودَةُ سُئِلَتْ , بِأَيِّ ذَنبٍ قُتِلَتْ , وَإِذَا الصُّحُفُ نُشِرَتْ , وَإِذَا السَّمَاء كُشِطَتْ , وَإِذَا الْجَحِيمُ سُعِّرَتْ ,

🔰ፀሐይ በተጠቀለለች ጊዜ ፤ ከዋክብትም በረገፉ ጊዜ ፤ ተራራዎችም በተነዱ ጊዜ ፤ የዐሥር ወር እርጉዞች ግመሎችም (ያለጠባቂ) በተተዉ ጊዜ ፤ እንስሳትም ሁሉ በተሰበሰቡ ጊዜ ባሕሮችም በተቃጠሉ ጊዜ ፤ ነፍሶችም (በየአካሎቻቸው) በተቆራኙ ጊዜ ፤ በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ ፤ በምን ወንጀል እንደ ተገደለች ፤ ጽሑፎችም በተዘረጉ ጊዜ ፤ ሰማይም በተገሸለጠች ጊዜ ፤ ገሀነምም በተነደደች ጊዜ ፤ ገነትም በተቀረበች ጊዜ ፤ ነፍስ ሁሉ (ከሥራ) ያቀረበችውን ታውቃለች .

☑️መካሪና ገሳጭ የሆነ ምክር ለሁላችንም ለየት ባለ መልኩ ለሴት እህቶቻችን .

🎙በታላቁ ሸይኽ ዐብዱልገኒይ አል-ዑመሪ

https://t.me/amr_nahy1
🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16610


📶ሙሳ (አለይሂ ሰላም) ህፃን እያለ ደካማ በነበረበት ጊዜ አልሰመጠም።

🌀ፊርአውን ግን ሀይለኛ በነበረበት ጊዜ ከነ ጉልበቱ ሰመጠ!! ።

👌አላህ ወደሱ ያስጠጋው ደካማነቱ አይጎዳውም!!

⛔️አላህ የተወው ሀያልነቱ አይጠቅመውም!! ።

🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16609?single




🚨 የነብዩላሂ ሙሳ ታሪክ 🚨

📮 በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መደመጥ ያለበት ገሳጭ እና መካሪ የሆነ ጣፋጭ ሙሓደራ።

🎙️ በኡስታዝ አቡ ሙሓመድ ሙሓመድሰዒድ ቢን በድሩ አላህ ይጠብቀው።

📅 ዕሮብ 17/04/2017E.C 🗓️

🕌 በሱና መስጂድ አ/አ ካራ-ቆሬ 🕌

ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇
📎https://t.me/mesjidalsunnah/16606


🔊🔈 የፈጅር አዛንን ስትሰማ
ሁለት አማራጮች አሉህ...

📢ህልምህን መቀጠል ወይም
ህልምህን ለማሳካት ተነስተህ  ወደ መስጅድ መሄድ።

🔉ፈጅር ሶሏት ልክ እንደ ጦርነት ነው በውስጧ ጀግና ጀግና ወንዶችን እንጂ አታዪም......

ለኡማዉ ሚበቃ እንቅልፍ ተኝቶ ስህር ተደረገብኝ  ይላላ ………………ህ

👍የኔ_ጀግና በጊዜ ተኛ በጠዋት ተነሳ


🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16605


#جديد

🔊 گلمة قيِّمة بعنوان:

📜 مشابهة الغِرباني: لبولس الطرطوسي في تفكيك الدَّعوات 📜

🎙️لفضيلة شيخنا الغيور:
أبي بلال الحضــــــــرمي
    - حفظه اللّٰه تعالـى -

⏳ المدة | 23:12

🗒 الثلاثاء 𝟤𝟥 جمادىٰ الآخرة  𝟣𝟦𝟦𝟨 هــ

📲 للتـحـميل عـبر تيليجـرام ↶:
🎥https://t.me/abubilalhami/13363


 📚 ተይሲሪል ከሪሚ-ረህማን ፊ ተፍሲር ከላም አል-መናን  {ተፍሲረ ሰዓዲ}

  
    📖 የሱረት አል-ዱሓ ተፍሲር 📖
      📖 የሱረቱ አል-ለይል ተፍሲር
📖

📚
  ﺗﻴﺴﻴﺮ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﻓﻲ ﺗﻔﺴﻴﺮ ﻛﻼﻡ ﺍﻟﻤﻨﺎﻥ
{ﺗﻔﺴﻴﺮ العلامة ﺍﻟﺴﻌﺪﻱ رحمه الله}

🎙 በኡስታዝ አቡ ሙሓመድ ሙሓመድሰዒድ ቢን በድሩ አላህ ይጠብቀው።

📅 እሮብ 16/04/2017E.C 📅

🗓የደርስ ቁጥር 012

🕌 በሱና መስጂድ {ካራቆሬ-ወታደር ሰፈር}

📚 የኪታቡን pdf ለማግኘት 📚
🔗
https://t.me/mesjidalsunnah/15612

🎧 ደርሱን በድምፅ ለማግኘት 🎧
🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16603


ኒቃብ ያደረገች ሴት ከሌሎች ሴቶች ግድ ልትለይባቸው የሚገቡ ጉዳዮች

📌 አደብ( ስርኣት) ሊኖራት ይገባል
📌ንግግሯ የተስተካከለ መሆን አለበት
📌አካሄዷ በእርጋታ የተሞላ መሆን አለበት
📌ከሀሜት ልትርቅ ይገባል
📌ወሬ ምታበዛ መሆን የለባትም
📌አለባበሷን የማይመጥን ቦታ መገኘት የለባትም ወዘተ…

👉 አንዳንድ ኒቃብ ለባሾች ግን ለምን እንደለበሱት ሁላ የሚያውቁ አይመስሉም።
አሳፋሪ ይሆኑብሃል❗️
ታክሲ ውስጥ በል መንገድ ላይ …ሀረካት በሀረካት እንዴ? ተረጋጉ እንጂ ❗️ሰከን በሉ❗️

👉ሲጀመር ለሌላ አላማ የተለበሰ በሚመስልክ መልኩ እንዲህ መንቀልቀል ተገቢ አይደለም❗️
🥀ሴት ልጅ ባጠቃለይ ረጋ ስትል ያምርባታል ኒቃብ ያደረች ከሆነ ደግሞ በተለየ መልኩ ሀያት(እፍረት) እንዲሁም እርጋታ ያስፈጋታል። ካልሆነማ የኒቃሙ ጥቅም ምኑ ጋር ነው ❓
እራስሽን ከሃራም ካልደበቅሽበት ሰዎችንም ከፈተና ካልጠበቅሽበት ትርጉም አልባ ነው ሚሆነው እንደውም ሌሎች ይህን የተከበረ ልብስ ሊለብሱ አስበው እንደአንቺ አይነቷን ሲያዩ እስልምናን ከማሰድብ ብለው ይተውታል በርግጥ ልክ አይደሉም ዑዝርም አይሆናቸውም አላህ ዘንድ ከመጠየቅም አያድናቸውም።
🫵 አንቺ ግን ሰዎችን ከመልካም ነገር አባራሪ ንፁህ የዲን ሴቶችን አሰዳቢ ነሽ።
እውነት እውነቱ ይወራ ከተባለ በጣም ጋጠወጥ ሴቶች አሉ ምንም እፍረት የሌላቸው ቅብዥብዥ ያሉ ።
📌 እናም አንዳንዱ ዋልጌ እንደዚህች አይነቷን ስርኣት አልበኛ አይቶ ሁሉም ኒቃም ለባሽ ዝርክርክ ይመስለዋል ሊተናኮል ሊያናግርም ይቃጣዋል።
እንዲህ አይነት ሰው በየታክሲው ሌላም ቦታ ሲያጋጥማችሁ ጠንካራ የሚያስደነግጥ መልስ መልሱ ፀጥ ብላችሁ ወሬውን አታዳምጡ❗️
አሏህ ሷሊሆችን ይጠብቅልን🤲

ለሁሉም ነገር ወሳኙ ተቅዋ ነው።❗️አላህም እንዲህ ይላል፦
وَلِبَاسُ ٱلتَّقْوَىٰ ذَٰلِكَ خَيْرٌ
አላህን የመፍራትም ልብስ የተሻለ ነው
   وَلِبَاسُ ٱلتَّقْوَىٰ
አላህን የመፍራት ልብስ ሲባል ሙፈሲሮች የተለያየ ገለፃን አስቀምጠዋል እሱም፦ ኢማንእፍረትአላህን መፍራት ወዘተ…

    📌ከምንም በላይ አስፈላጊው ጉዳይ አላህን መፍራት ተቅዋ ነው። ተቅዋ የሌላት እንስት መጀመሪያ ያሉባትን መጥፎ ባህሪያቶች፣ መጥፎ ጓደኞቿን ርቃ ጥሩ ሁኔታ ላይ ስትሆን ጊዜ ኒቃሟን ብትለብስ ጥሩ ይመስለኛል ካልሆነ ግን ከሷ አልፎ ሌሎችን በሚያስተች ሁኔታ ላይ ሆኗ መልበሷ ካልተቀየረችበት መጥፎ ባህሪዋን ለሌሎች ታጋባለች።
ውስጧ የተበላሽለ ቀልቧ የደረቀባት ሴት ቶሎ ብላ ወደ አላህ ካልተመለሰች አደጋው ከባድ ነው። በዱንያ ጭንቀት በአኼራ ደግሞ ውርደትን ትከናነባለች።
  
👉 አንድ ጊዜ ከመድረሳ ወጥቼ እየሄድኩኝ ሳለ አንዲት ኒቃብ ያደረገች ሴት ድምፇን ከፍ አድርጋ ታወራለች የምታወራው ነገር ወላሂ ልቤን ትርክክ ነው ያደረገው አላመንኩም ጮክ ብላ ማንቼ እንዴት ሆነ ተሸነፈ አሸነፈ ትላለች لاإله إلا الله ድርቅና ወላሂ አሁን እንዲህ አይነቷ ምን ትባላለች❓

📌አንቺ ሙተነቂብ እህቴ ሆይ አስተውዬ ይህ ልብስ ተራ ልብስ አይደለም ይህ ልብስ ለውበት ፣ለአይነናስ፣ ለትዳር ማምጫ ተብሎ በተበላሸ ኒያ የሚለበስ ነገር አይደለም።   ይህ ልብስ የነብዩ ባልተቤቶች ይለብሱት የነበረ የክብር የጥቡቅነት መገለጫ ነው።  ግዴታም ጭምር ነው።

👉ዛሬ የምንሰማቸው ነገራቶች ግን ወላሂ ልብ ይሰብራሉ❗️ በጥቂት ሰዎች ምክንያት የነዛ ድምፃቸው እንኳ የማይሰማ ጥቡቅ እንስቶች ስም አንድ ላይ ሲነሳ ልብ ያደማል ❗️
ቆይ ግን ምን ማለት ነው ኒቃብ አድርጋ ለወንድ ፎቶ መላክ ❓
👉 ኒቃም ስትለብሺ እኔ ጥቡቅ ነኝ እያልሽ እኮ ነው አልገባሽም እንዴ ❓ሲጀመር እንኳን ፎቶ መላክ ይቅርና ማውራት ራሱ መች ተፈቅዶልሽ
ብልሽትሽ የጀመረው ፎቶ የተነሳሽ ቀን ነው። በጣም ነውር ወላሂ በጣም አሳፋሪ ድርጊት ነው።
ነገ አላህ ዘንድ እርቃንሽን የምትቆሚበት ቀን ይመጣል
በአፈር የተከበበውን ጨለማውን የቀብር ቤትሽንም አትዘንጊው

📌ስህተት የቅፅበት ነች ፀፀት ግን የእድሜ ልክ ነው።
📌 ወደ መጥፎ ሊገፋሽ የሚችልን ነገር በሙሉ ራቂ በተለይ ስልክና መጥፎ ጓደኛን❗️

እኔ ይህን ብያለው እናንተ ብዙ ልታውቁ ትችላላቹ አላህ ደግሞ ሁሉምን አዋቂ ከሱ የሚደበቅ ነገር ፈፅሞ የለም❗️

አንዳንዴ ላለመታመም ለራሴ የምላት ነገር አለች ካፊሮች ይሆናሉ አውቀው ወንጀልን ለማለማመድ ልብሱን ለማጠልሽት ሲሉ
ግን… ምኞት ነው።

اللهم استرنا اللهم أصلح شبابنا وشباب المسلمين 🤲

👉https://t.me/AbuEkrima
🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16577


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
☑️ለመልካም ነገር  የመወፈቅ በር የተዘጋበት ሰበብ🔻
ሸቂቅ ቢን ኢብራሂም  እንዲህ ብለዋል

💎"የመልካም ነገር በር ከሰዎች የተዘጋው ከስድስት ነገር ነው።

1⃣በአላህ ፀጋዎች ቢዚ ሆነው - ማመስገንን በመተዋቸው
2⃣እውቀት ይፈልጋሉ -ግን ባወቁት መስራትን በመተዋቸው
3⃣ወደ ወንጀል እየፈጠኑ -ተውበትን በማዘግየታቸው
4⃣ደጋጎችን በመቀማመጥ ብቻ መታለላቸው -ስራቸውን ከመከተል መተዋቸው
5⃣ዱንያ ችላ ብላቸው እየሄደች - እነሱ ግን እሷን መከተላቸው
6⃣አኼራ በነሱ ላይ እየመጣች - እነሱ ከሷ ቸልተኛ መሆናቸው።ትርጉም ከአቡ ሰለማ


📚ፈዋኢድ  ከኢብኑል ቀይም ኪታብ 258

🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16576


📚 ወሳኝ ሊደመጥ ሚገባ ደርስ ⤵️

📙 شرح "مــسـائـل الـجـاهـلـيـة"
📙 ሸርሁ መሳኢሊል ጃሂሊያ


✍ تأليف:معالي الشيخ الأستاذ الدكتور بقية السلف وعمدة الخلف:صالح بن فوزان الفوزان حفظه الله تعالى.

🎙️️ በኡስታዝ አቡ ሙሀመድ ሙሀመድሰዒድ ቢን በድሩ አላህ ይጠብቀው።

📅 ከሰኞ- ማክሰኞ ከመግሪብ-ዒሻ በሱና መስጂድ ሚሰጥ ደርስ።

📆ማክሰኞ 15-04-17

    👉 ደርስ ቁጥር 22👈

📚 የኪታቡን pdf ለማግኘት 📚
🔗
https://t.me/mesjidalsunnah/15582

ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ👇👇👇
🎧 ደርሱን በድምፅ ለማግኘት 🎧
📎
https://t.me/mesjidalsunnah/16575


📚አል እስትድላል አላ ከንዝ አል አጥፋል

📚  كتاب " الإستدلال على كنز الأطفال على طريقة السؤال والجواب "

📚 የተሰኘው የታላቁ ሸይኽ ⤵️⤵️

✍️ لفضيلة الشيخ الدكتور فيصل بن مسفر الوادعي حفظه الله.

🎙 በኡስታዝ አቡ ሙሓመድ ሙሓመድሰዒድ ቢን በድሩ አላህ ይጠብቀውና

🕰️ ዘወትር ከሰኞ እስከ ማክሰኞ ከመግሪብ ሰላት በኋላ።

🗓ማክሰኞ 15-04-2017

📆የደርስ ቁጥር 10

📚 የኪታቡን pdf ለማግኘት 📚
🔗
t.me/mesjidalsunnah/16098

🎧 ደርሱን በድምፅ ለመከታተል 🎧
🔗
https://t.me/mesjidalsunnah/16574


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በመልካም ነገር ማበሰር ያለው አጅር

✍أجر التبشير بالخير

🎙 لشيخنا العلامة يحيى الحجوري حفظه الله تعالى ورعاه

https://t.me/AbuKhlid3320/53464
🔗https://t.me/mesjidalsunnah/16566

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.