"ሂድና ውደዳት!"
በአንድወቅት አንድ ሰው ሚስቱ እንድትወደው ብዙ ነገር አድርጎ ስላልተሳካለት ሚስቱም ስላልወደደችው ተበሳጭቶ ወደሰባኪው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይሄዳል፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
"ሚስቴእንድትወደኝ ብዙ ለፋሁ ፤ ያላደረኩት ነገር የለም ፤ምንም ልትወደኝ አልቻለችም፡፡ እንድትወደኝ ማድረግ የምችለው በምን መንገድ ነው?"ሲል በሀዘን ተሰብሮ ይጠይቀውና የሚነገረውን ጥበባዊ መንገድ በጥንቃቄ ለመረዳት እዝነልቦናውን አዘጋጅቶ የአባቱን ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ የአንደበቱን ጥኡም ቃል ይጠባበቃል፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
ቅዱስዮሐንስ ግን የነገሩት በአጭሩ በሁለት ቃል ብቻ የተዋቀረ ነበር፡፡ "ሂድና ውደዳት!"
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
ሰውየው'ያልኩትን አልተረዳኝ ይሆን እንዴ?' እያለ እያሰበ ጥያቄውን ደግሞ አቀረበ። "ሚስቴ አልወደኝ አለች ምንም ባደርግ ልትወደኝ አልቻለችም ነው ያልኩት" አለ በድጋሜ፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
"ሂድናውደዳት" አለው ሰባኪው በድጋሜ፡፡
አሁንም ለሶስተኛጊዜ ሰውየው "ልትወደኝ የሚገባት ሚስቴ አልወደደችኝም ነው ያልኩዎትኮ!"አለ፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
ሰባኪውምመልሶ "ሂድና ውደዳት!"አለው፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
በዚህጊዜ ሰውየው እርሱ እንደሚወዳት ለመናገር 'እኔማ...'ብሎ ጀምሮ ራሱን መፈተሽ ጀመረ፡፡ እሱ ውስጥ ያለው፣ እርሱ የሚወደው፣ የእርሱ ፍላጎት የእርሱን የራሱን በእርሷ መወደድ እንጅ እርሷን መውደድ አልነበረም፡፡ ጊዜውን ለመወደድ በመጣር ብቻ አሳልፎታል፤ ጥረቱ ሁሉ እንድትወደው እንጅ እንዲወዳት አልነበረም፡፡ አዘነ፡፡ እርሷን መውደድ ሲገባው ራሱን በርሷ ለማስወደድ ሲጥር ኖሯል፤ አልተሳካለትም፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
ፍቅርየሚመጣው በራሱ በፍቅር እንጅ በሌላው ሁሉ ጥረት አይደለም፡፡ በሌላ ጥረት የሚመጣ ሰው ሰራሽ "ፍቅር" ካለ ግን ፍቅሩ ሀሰተኛ ነው፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
ራስንከመውደድ አልፈን ራስን ወደማስወደድ ከመሄድ ይልቅ ሌላውን በመውደድ መወደድን አናጣውም፤ ፍቅር ሌላውን የሚወድ ከሆነ ፍቅርንማ እንደምን አይወድ!
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
እርሷንስትወዳት ፍቅሯን ታገኛለህ እንጅ ፍቅሯን ያለፍቅርህ አትሞክረው!አንዳንዶቻችን እኔ ላደረኩት ነገር ለምን አልተደነቅሁም ለምንስ አልተወደድኩም እንላለን። እንደዚህ ካልን ያደረግነውን ላደረግንለት ሳይሆን ለራሳችን ነው ማለት ነው ያደረግነው፤ ይህ ደግሞ የፍቅር ባህሪ አይደለም፡፡ እኛ ለሌሎች የሌለንን ፍቅርም ሌሎች ጋ ወደኛ መጠበቅ የለብንም፡፡ ለባለቤቴ ባደረኩላት ነገር ከእርሷ ምስጋናን የምሻ ከሆነና ካልተመሰገንኩ ከከፋኝ እኔ ከፍቅር የነፃሁ ምስኪን ነኝ፡፡ በርግጥ ሚስቴ ደስ ስትሰኝ ማየት ሊያስደስተኝ ይገባል፤ ይህ ማለት ግን እንደዋጋ አድርጌ ልወስደው ሳይሆን መደሰቷን ስለምመርጥላት ስለእርሷ ደስታ ስል ነው፡፡ ስለእኔ በደስታዋ መደሰት ያይደለ፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
"ሂድናውደዳት!" የሁልጊዜም መርሃችን ልትሆን ይገባል፡፡ እንድትወደን ሳይሆን እንድንወዳት ስንወዳት የምር ትወደናለች፡፡ ስንወድ ከተወዳጁ በምንጠብቀው ነገር መመስረት የለብንም የፍቅራችን መሰረት መመስረት ያለበት ፍቅራችን ላይ እንጅ በሚጠበቅ በሌላ ፍቅርም ሆነ ሌላመሰረት ላይ መሆን የለበትም፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
አምላክእኛን ስለወደድነው አይደለም የወደደን፤ በራሱ ፍቅር ተመስርቶ ወደደን እንጅ፡፡ እኛም በራሳችን ፍቅር ተመስርተን ልንወደው ወይም ስለማይናድ በራሱ ፍቅር ተመስርተን ልንወደው ይገባል፡፡
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
ሰውላይ ግን መመስረቻው የሰው ፍቅር አይደለም፤ አያስተማምንም፡፡ በራስ ፍቅር መሠረት ላይ የተተከለች ፍቅር በራስ ይዞታ ላይ እንደተሰራች ቤት ናት፡፡ ማንም መጥቶ አያፈርሳትም፡፡ ወዳኝ ከምንዋደድ ወድጃት ብንዋደድ ይሻለኛል፡፡ መሰረቱን ራሴ ላይ ራሴ ብይዘው!
👉 t.me/mezgebehaymanot👈
አዘጋጅ:-በለጠከበደ (የጣፈጡልጅ)✍አላቲኖስ
╔✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╗
❀#መልካም_የበረከት_ቀን❀
╚✞═┉✽🌹✥🌹✽┉═✞╝ አላቲኖስ
የተሣተውን ፤ የተረሳው፤ የተገደፈውን፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት🙏🙏🙏
በቴሌ ግራም
👉 " መዝገበ ሃይማኖት" t.me/mezgebehaymanot
ወስብሐትለእግዚአብሔር