#መከራን_ማሸነፊያ_7_ጥበቦች
የብፁዕ ወቅዱስ #አቡነ_ሺኖዳ_ሳልሳዊ ምርጥ መጽሐፍት በገበያ ላይ መዋላቸውን ምክንያት በማድረግ መከራን ማሸነፍን በተመለከተ ከመጽሐፍቶቹ የተወሰዱ 7 ትምህርቶችን እነሆ ብለናል፦
#ትምህርተ_ሺኖዳ አዲስ መጽሐፍ
#አቡነ_ሺኖዳ_መልስ_አላቸው አዲስ መጽሐፍ
#ሰይጣንን_አስርቡት 2ተኛ ዕትም አዲስ መጽሐፍ
#እስከማዕዜኑ 3ተኛ ዕትም
#ጠይቁ_ይመለስላችኋል 4ተኛ ዕትም
#1_ዓለም_የመከራ_ብቻ_አይደለችም
መከራ ባለበት ስፍራ ሁሉ አዳኙ መድኃኒተዓለም ደህንነትንና መጽናናትን የሚሰጠን መለኮታዊ ኃይል እንዳለ ማመን አለብን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ “በፃድቃን ላይ መከራ ይበዛል” ብቻ አይደለም የሚለን፤ ነገር ግን ስናስተውል፣ “ፃዲቁን አምላክ ከገባበት መከራ ይታደገዋል” እንጂ፡፡ “ዓለም የመከራ ነች” ብቻ አይደለም የሚለን፤ ይልቁንም “ነገር ግን በመልካምነት ውስጥ መከራን ተወጥቸዋለሁ” ይለናል እንጂ፡፡
#2_በአንበሶች_ጉድጓድ_ብንጣልም_አንፍራ
ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ በተጣለ ጊዜ አንዳች አልፈራም፡፡ ሦስቱ ብላቴኖችም ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ከቶውንም አል ወደ ሞት ሲነዱ ወይም ልዩ ልዩ መከራ ሲደርስባቸው አልፈሩም... ዳዊትም የአቤሴሎምን አመጽ በሰማ ጊዜ፡- “እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ ብርታት ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው?” ነው ያለው። (መዝ. 27፥1) እኛም እንደዚሁ እንበል፡፡
#3_መከራ_ቢበዛም_የሚታደገን_ደግሞ_አለ
ለዳዊት ህይወት ቀላል አልነበረችም፤ በመከራና በወጀብ በጭንቀትም መካከል ተጓዘ እንጂ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ግን ታደገው፡፡ የጠየቀውን ሁሉ አብዝቶ ሰጠው፡፡ ዳዊት በመዝሙሩ እንዲህም አለ፡- “የፃድቃን መከራቸው ብዙ ነው፤ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል፡፡ እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል ከእነርሱም አንድ አይሰበርም፡፡” (መዝ. 34፥19-20)
#4_ፍርሃትን_በማሸነፍ_ከፍ_እንበል
ቅዱስ አውግስጢኖስ፡- “ምንም ነገር እንደማልፈልግ ሳስብ ወይም ምንም እንደማልፈራ ከውስጤ ሲሰማኝ ያን ጊዜ በዓለም ከፍታ ላይ ተቀምጫለሁ፣” ያለው የማይታበል ሀቅ ነው። ፍርሀታችን ድል በመንሳት ከፍ ማለት አለብን።
#5_በመከራ_ውስጥ_ደግሞ_በረከት_አለ
በረከት አንድ ሰው ሊፈልገው ከሚችለው ሁሉ በላይ የሆነ ነገር ነው፤ በውስጡ ሁሉንም ነገር ተሸክሟልና።
በዚህ ረገድ ጠቢቡ ሰሎሞን “የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች…” (ምሳ. 10፥22) ብሏል። በረከት የሌለው ግን ህይወቱ ፍጹም ባዶ ትሆናለች፣ እናም በሁሉም ነገር የማይሳካለት ይሆናል።
#6_የተረጋጋ_መከራን_ያንበረክካል
የተረጋጋ ልብ እንደ ጥልቅ ባህር ነው። ችግሮች በላዩ ላይ ሊንሳፈፉ ይችላሉ፡፡ እርጋታውን ግን አይረብሹበትም፡፡ ወደ ጥልቁ ቢወርዱ ግን ይሟሟሉ፣ ይጠፋሉም፡፡ ለተረጋጋ ሰው ደግሞ መከራ ራሱ ተሸናፊ ሆኖ እጁ ስር ይወድቅለታል።
#7_ሰይጣንን_ተስፋ_እናስቆርጠው
ፈተናዎቻችን ከእግዚአብሔር እንዳልመጡ እንወቅ - ከቀናብህን ከሰይጣን እንጂ፡፡ አባታችን ሐዋሪያው ያዕቆብ እንዲህ ብሏል፡ “ማንም ሲፈተን በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈትንምና፤ እርሱ ራሱ ማንንም አይፈትንም፡፡” (ያዕ 1፥13)
ስለሆነም ፈተናዎች ሲገጥሙ እንታገስ፤ መልካም ነገሮችን በበለጠ ሁኔታ በመስራት ሰይጣን በእኛ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ እናድርገው፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምርጥ መጽሐፍት በገበያ ላይ
👇👇👇
#ትምህርተ_ሺኖዳ አዲስ መጽሐፍ
#አቡነ_ሺኖዳ_መልስ_አላቸው አዲስ መጽሐፍ
#ሰይጣንን_አስርቡት 2ተኛ ዕትም አዲስ መጽሐፍ
#እስከማዕዜኑ 3ተኛ ዕትም
#ጠይቁ_ይመለስላችኋል 4ተኛ ዕትም
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛሉ።