ዛሬ ጥር 10 የከተራ በዓል ነው እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን💙🙏
ከተራ ማለት?✍️ከተራ ማለት "ከተረ" ከምለው ከግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ዙርያውን ከበበ፣ አጠረ፣ ገደበ ማለት ነው።
🥀ከተራ ማለት ከተረ፣ አጠረ፣ ሰበሰበ ማለት ሲሆን ይኸውም ወራጁን ውሃ ሰብስቦ ወይም ገድበው በየሰበካው ተለይቶና ተከልሎ ለጥምቀት የምዘጋጁበት ዕለት ነው።
➻ታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረዳቸው - ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን አስከትሎ ሊጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ የመወረዱ ምሳሌ ነው። ታቦታቱ የጌታችን ምሳሌዎች ናቸው።
✍️ታቦታቱን ያከበሩ ካህናት የመጥምቁ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ምሳሌዎች ናቸው።
ባህረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ምሳለ ነው።
🥀ታቦታቱን አጅበው የምሄዱ ምዕመናን ወደ መጥምቁ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ እየሄዱ ንሰሃ እየገቡ የንሰሃን ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩ የእኔሱ ምሳሌዎች ናቸው።
መልካም የከተራ በዓል💚💛❤️✝️🙏
@Mezmure_tewahdo