ወድሰኒ dan repost
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ
ቂርቆስ ማለት ቀለም ማለት ሲሆን አባቱ ቆዝሞስ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ኢየሉጣ ማለት ምልእተ ሃይማኖት ማለት ሲሆን ሀገሯ ሮም ነው፡፡ እለእስክንድሮስ በነገሠ ጊዜ በሃይማኖት ምክንያት በምእመናን ላይ ስደት ደረሰባቸው፤ ኢየሉጣም የሦስት ዓመት ሕፃኑን ቂርቆስን ይዛ ከሮም ወደ ጠርሴስ ተሰደደች፡፡ ንጉሡ ክርስቲያኖችን እያደነ ወደ ሸሹበት ሀገር ደርሶ አገኛቸው፤ ቅድስት ኢየሉጣንም ይዞ ‹‹ሀገርሽ የት ነው? ስምሽ ማን ይባላል? ወገንሽ ማን ነው?›› ብሎ ጠየቃት፡፡ እርሷም ‹‹ስሜ ክርስቲያን ሀገሬ ሮም ነው፤ ከአንተ ሸሽቼ ብመጣ አገኘኸኝን?›› አለችው፡፡ መኰንኑም መልሶ ‹‹ለጣዖት ስገጂ ስምሽን ግለጪ እንዳትሞቺ›› አላት፤ እርሷም ‹‹ሞት የሚሽረው ስሜ ኢየሉጣ ነው›› አለችው፡፡ ‹‹ለአማልክት መሥዋዕት አቅርቢ›› ብሎ ባዘዛት ጊዜ እርሷ ‹‹እውነትን ማወቅ ከፈለክ ወደ መንደር ልከህ የሦስት ዓመት ሕፃን አስመጣና የምናመልከውን እርሱ ይንገረን›› አለችው፡፡
ንጉሡም ወታደሮችን አስልኮ ቂርቆስን አመጡለት፤ ከዚያም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ከሐዲው መኰንን ይዞ ‹‹ስምህ ማነው?›› ብሎ በጠየቀው ጊዜ ‹‹ከንጹሕ ምንጭ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው እናቴ የሰየመችኝ ሞክሼ ስም ቂርቆስ ነው›› በማለት መለሰለት፡፡ መኰንኑም ‹‹ስታድግ ሹመት ሽልማት እሰጥሀለሁ በወርቅ በብር አከብርሃለሁና ለአማልክት ስገድ ክርስቶስን ካድ›› ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን ‹‹የሰይጣን ወዳጅ ለእውነትም ጠላቷ የሆንክ ከእኔ ራቅ›› አለው፡፡ በዚህም መኰንኑ ተቆጥቶ መከራ አበዛበት፤እንደገናም በእናቱና በእርሱ አፍንጫ ጨውና ሰናፍጭ አስጨመረባቸው፡፡ ሕፃኑ ግን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ስለጠነከረ ‹‹ነገርኽ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ሆነ፤ ከማርና ከስኳርም ለአፌ ጣመኝ›› እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ መኰንኑ በዚህ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ የብረት ችንካሮችን እንዲሰኩባቸው አደረገ፤ ሆኖም ግን በጌታችን ፈቃድ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ጉዳት አላደረሰባቸውም፡፡
ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ወሰዷቸው፤ በኋላም በደረቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ስቃያቸውን አራቀላቸው፡፡ የሕፃኑ ምላስ እንዲቆረጥ አዝዞ ቢያስቆርጠውም ክብር ይግባውና ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ ከዚያም በታላቅ ጋን ውኃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውኃ ድምጽ የተነሳ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ አገኛት፤ ሕፃኑም ‹‹እናቴ ጨክኚ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል›› እያለ ወደ ፈጣሪው ጸልዮላት ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ ቅዱስ ገብርኤል ውኃውን አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል፤ ይህም የሆነው ሐምሌ 19 ቀን ነው፡፡
በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚቀዳጅበት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ሁሉ ቃል ኪዳን ሰጥቶት ጥር 15 ቀን ከእናቱ ጋራ አንገቱን ተቆርጦ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል፡፡ በዚህ ዕለትም ብዙ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ የሰማዕታቱ በረከት ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መድበለ ታሪክ ፣ ስንክሳር ዘጥር 15