ወድሰኒ dan repost
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ጾመ_ሰብአ_ነነዌ
ይህ ጾም የነነዌ ሰዎች የጾሙት ሦስቱ ዕለታት ማለትም ሰኞ፣ ማክሰኞና ረቡዕ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የሚጾም ጾም ነው፡፡ በመባቻ ሐመር የጾሙ ወቅት ከፍና ዝቅ ይላል፤ ማለትም አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል፡፡
የነነዌ ከተማ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የተመሠረተችና ከጥንት ጀምሮ ጣዖት ይመለክባት የነበረች ጥንታዊት የአሶራውያን ዋና ከተማቸው ነች፡፡ በተጨማሪም በከተማዋ ጣዖት የሚያመልኩና እግዚአብሔርን የሚዘባበቱ ሕዝብና ነገሥታት ነበሩባት፡፡ (ለምሳሌ የንጉሥ ሰናክሬምና የእስራኤል ንጉሥ ሕዝቅያስን ታሪክ 2ኛ ነገ ምዕ 19 ያንብቡ)፡፡
ይህች ከተማ በዚህ ሁኔታ ቀጥላ በ770 ቅ/ል/ክ የሕዝቡ ኃጢአት ከፈጣሪ ሲደርስ እግዚአብሔር ‹‹ነነዌ በዚህ ሦስት ቀን ትገለበጣለች ብለህ ንገራቸው›› ብሎ ነቢዩ ዮናስን ላከው፡፡ ዮናስ ግን የዋህ ስለነበረ ‹‹አንተ መሐሪ አምላክ ነህና እኔ እናገራለሁ አንተም ትምራቸዋለህ በመጨረሻም እኔ ውሸተኛ እባላለሁና ስለዚህ ወደ ነነዌ ሔጄ አልሰብክም›› በማለት ወደ ተርሴስ ለመሔድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በአውሎና በወጀብ መካከል መንገድ ያለው ፍጥረታቱም ሁሉ የሚታዘዙለት አምላክ መሆኑ ይታወቅ ዘንድ በባሕሩ ላይ ወጀብ አስነሳ፡፡ ዮናስ የተሳፈረበት መርከብም ታወከች፤ በመርከቢቱ የተሳፈሩ ሌሎች ተሳፋሪዎችም ‹‹ከእኛ መካከል በደለኛ ማን ነው?›› ሲባባሉ ዮናስ ግን በመርከቡ አንደኛው ክፍል ገብቶ ተኝቶ ነበር፡፡ እነርሱም ቀስቅሰው ማንነቱን ሲጠይቁት ‹‹እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የማመልክ ሰው ነኝ፤ በእርሱ ላይ በማመጼ ይህ ሁሉ መከራ በእኔ ምክንያት አግኝቷችኋል፤ ስለዚህ እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› አላቸው፡፡ መርከበኞቹም እውነቱን ለማረጋገጥ እጣ ቢጣጣሉ በተከታታይ ሦስት ጊዜ በዮናስ ላይ ስለወጣ ዮናስን ከመርከባቸው አውጥተው በባሕር ላይ ጣሉት፡፡ ፍጥረታቱ ሁሉ ለእግዚአብሔር ይታዘዙለታልና ትልቅ ዓሣ ዮናስን ውጦ በባሕር ላይ እየተጓዘ በሦስተኛ ቀኑ በባሕር ወደብ ላይ በነበረች በነነዌ ከተማ ተፋው፡፡ ዮናስም ከዓሣው ሆድ ከወጣ በኋላ ስለከተማዋ በጠየቀ ጊዜ ነነዌ መሆኗን ነገሩት፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር በል እንዳለው ‹‹ይህች ከተማ በሦስት ቀን ትገለበጣለች›› ብሎ ሰበከ፤ (ሙሉ ታሪኩን ትንንቢተ ዮናስ አራቱንም ምዕራፎች ያንብቡ)፡፡
የነነዌ ሰዎች አስቀድሞ በሰናክሬምና በወታደሮቹ ላይ የደረሰውን ጥፋት እና ‹‹ኃይሌ ጉልበቴ አንተ ነህ›› ያለውን ሕዝቅያስን ከነሕዝቡ የመዳኑን ታሪክ ሰምተዋልና እግዚአብሔር ይቅርባይ መሐሪ መሆኑን አምነው ወደ እርሱ ተጠግተው ከአዋቂ እስከ ልጅ ከንጉሥ እስከ አገልጋይ ተስማምተው ጾምን አወጁ፤ በአንድ ልብ በአንድ መንፈስ ሆነውም አለቀሱ፡፡ እግዚአብሔርም መመለሳቸውን ተመልክቶ ይቅር አላቸው፡፡ ዮናስ ግን መደሰት ሲገባው በየዋህነቱ አዘነ፤ ቀድሞውኑ እኔ የተናገርኩት ሳይሆን ቢቀር ውሸተኛ እባላለሁ ብሎ ነበርና፤ (ዮና 4፥1)፡፡
ይህን ጾም የምንጾምበት ዐቢይ ምክንያት አብርሃም ሶርያዊ ሊቀ ጳጳስ የሠራው ሥርዓት በመሆኑ ነው፡፡ አብርሃም ሶርያዊ ከክርስቲያን ወገን የተወለደና አስቀድሞ ገንዘብ ያለው ነጋዴ ነበር፡፡ እየነገደም ምስር (ግብፅ) አገር ደርሶ በዚያው መኖር ጀመረ፡፡ ለድኆችና ለችግረኞች ርኅራኄን የሚያደርግ በመሆኑና በዚህም ብዙ ትሩፋቶቹ በመገለጣቸው የእስክንድርያ ኤጲስ-ቆጶሳት በፈቃደ እግዚአብሔር በእስክንድርያ ሊቀ-ጵጵስና ሾሙት፡፡ ከዚህ በኋላ ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች መጽውቶ የሊቀ-ጵጵስናውን ሥራ መሥራት ጀመረ፡፡ በሹመቱም ወራት ክፉ ልማድን ሁሉ አስወገደ፤ ኤጲስ-ቆጶሳቱንም ስለ ክህነት ሹመት መማለጃ እንዳይቀበሉ አወገዛቸው፤ ውግዘቱንም በሰሙ ጊዜ ሁሉም ፈርተው ክፉ ልማዳቸውን በመተው በደላቸውን ያስተሰርይላቸው ዘንድ ለመኑት፡፡
እግዚአብሔርን ከማይፈራ አንድ የንጉሥ ጸሐፊ ከሆነ ሰው በስተቀር ሁሉም ግዝቱን አክብረውታል፡፡ አብርሃም ግን ያን ክፉ ሰው ስለ ራሱ ድኅነት ብዙ ጊዜ ቢለምነውም ከክፋቱ አልተመለሰም፡፡ ጻድቁ አብርሃም ማስተማሩንና መገሠጹን ሳይሰለች ለሌሎች ዕንቅፋት እንዳይሆን ወደዚያ ክፉ ሰው ቤት ሄደ፤ ሆኖም ግን ይህ ክፉ ሰው የሊቀ-ጳጳሱን መምጣት በሰማ ጊዜ ደጁን ቢዘጋበትም አብርሃም ደጁን እያንኳኳ ለተወሰነ ሰዓት ቆመ፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹የዚህ ሰው ደም በራሱ ላይ ነው፤ እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ›› ብሎ የእግሩን ትቢያ አራግፎ ተመለሰ፡፡ ያም ክፉ ሰው በክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ ይህን የተመለከቱ ብዙዎችም ንስሐ ገብተዋል፤ (ስንክሳር ዘታኅሣሥ 6)፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአብርሃም ሶርያዊ የሊቀ-ጵጵስና ዘመን ለምስር (ግብፅ) ንጉሥ የጭፍራ አለቃ የሆነ አንድ አይሁዳዊ ሰው ነበር፡፡ ለዚህም የጭፍራ አለቃ አብሮት ወደ ንጉሥ የሚገባ ሌላ አይሁዳዊ ወዳጅ ነበረው፡፡ ይህ አይሁዳዊ ከጭፍራ አለቃው ጋር ወዳጅ በመሆኑ ከንጉሥ ጋር ይነጋገራል፤ ከንጉሥ ዘንድ ባለሟልነትን ባገኘ ጊዜም ንጉሡን ‹‹ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ሊቀ-ጳጳሳት አባ አብርሃምን እንድታስመጣውና በፊትህ እንድከራከረው ተመኝቻለሁ›› አለው፡፡ ንጉሡም ልኮ አባ አብርሃምን አስመጣው፤ ከርሱም ጋር የእስሙናይን ኤጲስ-ቆጶስ አባ ሳዊሮስ ነበረ፡፡ ይህ አይሁዳዊም ከሊቀ-ጳጳሳቱ ጋር ተከራክሮ በመረታቱ ንጉሡ ሊቀ-ጳጳሳቱን አክብሮ በሰላም ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡ የጭፍራ አለቃውና አይሁዳዊ ወዳጁም አፈሩ፡፡ ሆኖም ግን ሊቀ-ጳጳሳቱንና የክርስቲያን ወገኖችን የሚያሸንፉበት ሌላ ነገር መሥራት ጀመሩ፡፡ በአንዲትም ቀን የጭፍራ አለቃው ወደ ንጉሡ ገብቶ ‹‹ጌታዬ ንጉሥ ሆይ የማስረዳህ ነገር አለ፤ እነዚህ ክርስቲያኖች ሃይማኖት የላቸውም፤ ወንጌላቸው፡- የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ሃይማኖት ካላችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ተነቅለህ ወደዚያ ሂድ ብትሉት ይሄዳል የሚሳናችሁ የለም›› ይላልና አለው፡፡ ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ መጠየቅ ሽቶ ሊቀ ጳጳሱን ሲያገኘው ነገሩን ያጣዋል፤ ነገሩ ትዝ ሲለው ሊቀ ጳጳሱን ያጣዋል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ግን እርሱ ባለበት ነገሩ ትዝ ይለውና ‹‹አባቴ የምጠይቅህ ኑሮኝ አንተን ሳገኝህ ነገሩን እየዘነጋሁት ነገሩ ትዝ ሲለኝ አንተን እያጣሁህ ቆየሁ፤ አሁን ግን ነገሩም ትዝ ብሎኛል አንተም መጥተሃል›› አለው፡፡ ከዚያም በወንጌል ‹‹የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም›› (ማቴ 17፥20 ፣ ማቴ 21፥21 ፣ ሉቃ 17፥6) ተብሎ ተጽፏል፤ ወንጌል እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለህ የምታምን ከሆንህ ይህን ፈጽመህ አሳየን አሉት፡፡ አብርሃም ሶርያዊም ሦስት ቀን እንዲሰጡት ጠይቆ ሦስቱን ቀን በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ተማጸነ፤ ከዚያም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጣለት ጫማ ሰፊ ተብሎ የሚታወቀው ስምዖን ግብጻዊ ጋር እንዲሄድና ከእርሱ ጋር ሆነው አይሁድ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኙ ነገረችው፡፡ በመጨረሻም በሊቀ ጳጳሱ አስተባባሪነት፣ በስምዖን መሪነት፣ በምእመናን ጸሎትና በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ 41 ኪራላይሶን አድርሰው ሰግደው ሲነሡ ተራራው ተነሣ፤ በውስጡም ተያዩ፡፡ ተራራውንም አፍልሰው በኢ-አማንያን ፊት ድንቅ ተአምር አሳይተዋል፡፡ ይህ ተአምር የተደረገበት ወቅት ደግሞ ጾመ ነቢያት ከመግባቱ በፊት ስለነበር የተደረገውም ተአምር ቤተ ክርስቲያን ዘወትር