በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ጫማ ጠራጊዎች ያለ ደረሰኝ ግብር እየከፈልን ነው አሉ
በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ወዴሳ ወረዳ በጫማ መጥረግ ሥራ ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች ያለ ደረሰኝ በወር 2,700 ብር ግብር በመክፈል ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ጽሕፈት ቤት በበኩሉ ስለጉዳዩ የማውቀው ነገር የለም ብሏል፡፡
በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ወዴሳ ወረዳ መናኸሪያ አካባቢ ጫማ በመጥረግ ሥራ የተሰማራና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ግለሰብ እንደተናገረው፣ ቀደም ባሉት ጊዜያት በቦታው ላይ ራሱ ባዘጋጀው ወንበር የጫማ መጥረግ ሥራ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ሆኖም ከስምንት ወራት ወዲህ ከቀበሌ መጣን ያሉ ሰዎች በላሜራ የተሠሩ ሼዶችን በመትከል እዚያ ሆነው እንዲሠሩና በቀን 90 ብር እንዲከፍሉ ማድረጋቸውን ይገልጻል፡፡
ግለሰቡ ሼዱ ከተቀመጠ ጊዜ አንስቶ እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ በወር 60 ብር ይከፍሉ ነበር፡፡ ካለፈው ወር ጀምሮ ግን ክፍያው በቀን ወደ 90 ብር ማደጉንና ለሚከፍሉትም ክፍያ ደረሰኝ እንደማይሰጣቸው ተናግሯል፡፡
Via @mussesolomon