የግብጽን ጥቅም ለማስከበር ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉት አሜሪካዊው ሴናተር የ11 ዓመት እስር ተላለፈባቸው
ሴናተሩ ከህዳሴው ግድብ ጋር በተገናኘ የግብጽን ጥቅም እንዲያስከብሩ እና በሌሎች ጉዳዮች ከ600 ሺህ ዶላር በላይ ሙስና ወስደዋል በሚል ክስ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል
የግብጽን ጥቅም ለማስከበር ጉቦ ተቀብለዋል የተባሉት አሜሪካዊው ሴናተር የ11 ዓመት እስር ተላለፈባቸው።
ባለፉት 40 ዓመታት በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ የነበሩት ቦብ ሜነንዴዝ ለዓመታት የሀገሪቱ ውጭ ግንኙነት ስራዎች ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰውም ነበሩ፡፡
የዘር ሀረጋቸው ከኩባ የሚመዘዘው ሜኔንዴዝ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት የኒው ጀርሲዋ ዩኒየን ሲቲን በከንቲባነት መርተዋል፡፡
እኝህ ጉምቱ ፖለቲከኛ በፈረንጆቹ 2020 ላይ የወቅቱ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ጫና አድርገዋል ተብሏል፡፡
እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ከሆነ ፖለቲከኛው ይህን ያደረጉት ከግብጽ ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጉቦ ከተቀበሉ በኋላ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት በማድረግ ላይ የነበሩ ሲሆን የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ውይይት ወደ ዋሸንግተን እንዲመጣ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡
Via @mussesolomon