የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ደረሰ፡፡
• ባንኩ በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 58.3 በመቶ መሰብሰብ ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድሥት ወራት ብር 245 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ጠቅላላ የተቀማጭ የገንዘብ መጠኑን ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል፡፡ ይህ አፈፃም ከእቅድ አንፃር 147.6 በመቶ አፈፃፀም የተመዘገበበት ነው፡፡
ዛሬ በተጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው ባንኩ በግማሽ ዓመት ያሰባሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በተመሳሳይ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሰበሰበው ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 423.1 ቢሊዮን ብር ውስጥ 58.3 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው ያስቻለ ነው፡፡
በባንኩ የተመዘገበው ይህ ውጤት ደንበኞች ከባንኩ ጋር ያላቸው ግንኙነት እና የባንኩ የአገልግሎት ጥራት መሻሻል ማሳያ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ ባንኩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማንቀሳቀስ የተጣለበትን ትልቅ ኃላፊነት ለመወጣት እንደሚያግዘውም ተመላክቷል፡፡
Via @mussesolomon